2014-10-17 15:13:17

የሲኖዶስ የአሥር ንኡሳን የውይይት ቡድን የድኅረ ውይይት ሰነድ


RealAudioMP3 በየዕለቱ በመካሄድ ላይ ስላለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ልዩ ሦስተኛው ሲኖዶስ ውሎው መሠረት የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በመቀጠል ይኸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የተካሄደው የሲኖዶስ ውሎ፣ ንኡሳን የውይይት ቡድን ሰነድና እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ ሊያካትተው ይገባዋል ተብለው የቀረቡት አስተያየቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መገለጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።
ቤተሰብ የሚያጋጥመው ችግር በተለያየ ቀውስ የተጠቃው ቤተሰብ ጉዳይ መምከሩና ተከስቶ ያለው ቀውስ ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ የተገባ ኃላፊነት ሲሆን ለዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወንጌልና የቤተሰብ አወንታዊ ግጽታው ማጉላት ወሳኝ ነው። ስለዚህ ምሥጢረ ተክሊል በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸና የማይሻር መሆኑ የንኡሳን ቡድን የድኅረ ውይይት ሰነድ አበክሮ ስለዚህ ይኽ ምስጢር ተከባሪ መሆን እንዳለበት ማብራራቱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘው፣ ወላጅ አልባ የሆኑትን ሕፃናት እንደ ልጅ ተቀብሎ ማሳደግ ያለው አስፈላጊነት፣ ወላጅ አልባ የሆኑትን ለማሳደግ የሚቀርበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚጠይቀው ያሠራር ሂደት እንዲሻሻልና ዓመታት የሚያስጠብቀው አሠራር እንዲሻሻል ይኽ ሲባል የሚደረገው ክትትልና ጥናቃቄ ጽኑ መሆን እንዳለበት የሚል ሃሳብ ጭምር የቀረበበት ውሎ እንደነበር ገልጠዋል።
በቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩት አረጋውያንን ጥበቃና እንክብካቤ ያለው አስፈላጊነት፣ በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙት ቤተሰቦች፣ በዓለም የሚታየው የሰው ልጅ ክብር የሚሰርዘው ባመንዝራነት መተዳደር ተግባር፣ ብዙ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተገደው ለዚህ ክብር ሰራዥ አደጋ የሚጋለጡት ከወደቁበት ችግር እንዲላቀቁ ጥረት ማድረግ፣ ሴቶች ልጆችን የመግረዙ ጎጂ ልማድ እንዲወገድ ለአቀመ አዳም ያልደረሱት ሕፃናት ለሥራ ዓለም መዳረግ፣ በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ላመንዝራነት አደጋ የሚጋለጡት ሕጻናት አቢይ ትኵረት ሰጥቶ ከወደቁበት አደጋ እንዲላቀቁ መደገፍ የሚል ሃሳብ የጎላበትና እምነት በማስተላለፉ እንዲሁም በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ቤተሰብ ያለው ማእከላዊ ኃላፊነት ፈጽሞ እንዳይዘነጋና ይኸንን የቤተሰብ ሓዋርያዊነት ጥሪው ማበረታታት ያለው አስፈላጊነት በውይይት ድኅረ ሰነድ ተመልክቶ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ቤተሰብ የሚያጋጥመው የተለያየ ችግር በቤተሰብ ላይ ለመፍረድ የሚገፋፋ ሳይሆን ቤተሰብ እንዲስተናገድና እንክብካቤ እንዲደረግለት የሚያሳስብ ነው። ቤተ ክርስቲያን አድልዎ የምትቃወም የሁሎም ቤት ነች። በቤተ ክርስቲያን የተሠራው ምስጢረ ተክሊል ይፈታልኝ ባዮች ምእመናን የሚያቀርቡት ጥያቄ ለማጤን የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት የሚፈጀው የጊዜ ገደም የተስተካከለ እንዲሆንና ከዚሁ ጋር በማያያዝም ይፈታ ወይንም አይፈታ ተብሎ የሚሰጠው የውሳኔ መልስ ተገቢ መልስ ለመሆኑ በጥልቀት መመልከት እንደሚያስፈግ ብሎም የተፋቱት በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ይኑራቸው አይኑራቸው የሚለው ጥያቄ በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት የሚለው እንዲታቀብ በሚል በሌላው ረገድ ደግሞ በንስሃና በጸጸት ጎዳና የሚገኝ ከሆነ በስቃዩ ተካፋይነትና በመሃሪነት መንፈስ በቅዱስ ቁርባን ማሳተፍ የሚል አስተያየት የቀረበም ሲሆን፣ እንደ ሦስተኛ አማራጭ ሃሳብ ደግሞ የተፋቱት ዳግም በቅዱስ ቁርባን ማሳተፍ የሚለው ጉዳይ የሚያጠና ልዩ ውስጠ ድርገት እንዲመለመል የሚል መሆኑ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አመለከቱ።
ንኡሳን የሲኖዶስ የውይይት ቡድን በሌላው በኩል በምሥጢረ ተክሊልና በምሥጢረ ጥምቀት መካለው ትስስር እርሱም ክርስቶሳዊ ማአክልነተ ሥር በለለጠ ለይቶ መመልከት እንደሚያስፈግል ባወጡት የድኅረ ውይይት ሰነድ ሥር እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ገልጠው፣ ምሥጢረ ተክሊል በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚል ይኽ ጋብቻ በተመሳሳይ ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ከሚጸናው የአብሮ መኖር ምርጫ ጋር አስተካክሎ ማስቀመጥ የማይገባና እነዚህ የተመሳሳይ ጾታዊ ስሜት ዝንባሌ ያላቸው ብቃት ባለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት በመደገፍ ይኽም ክብራቸው እንዲጠበቅ ማነቃቃት እንዲህ ሲባል ግን ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚጸናው ጋብቻ እውቅና ሰጥታበታለች ማለት እንዳልሆነና ከአንድ ሚስት በላይ ያገቡት ክርስትና እምነት ከተቀበሉና ከተለወጡ በኋላ በቅዱሳታ ምሥጢራት ሱታፌ እንዲኖራቸው ለሚሹት የተሟላ መልስ ለመስጠት በዚህ ጉዳይ ሥር ልዩ ኵላዊ ጥናት እንዲካሄድ የሚል ሃሳብ በድኅረ ውይይት ሰንድ ተመልክቶ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ንኡሳን የውይይት ቡድን የቅድስት ድንግል ማርያምና እንዲሁም የቅድስት ቤተሰብ አብነት አቢይ ትኵረትና አስተንትኖ እንዲደረግበት በማሳሰብ፣ ይኽ ቅዱስ አብነት ለሁሉም ቤተሰቦች አርአያ እንዲሆን ለመደገፍ ያለመ ሲሆን፣ በመጨረሻ የዚህ የንኡሳን ቡድን የውይይት ሰነድ የሲኖዶሱ የፍጻሜ ሰነድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. ወደ ሚካሄደው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚሸኝ ነው የሚል ሃሳብ እንደሰፈረበት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.