2014-10-17 15:08:38

ሲኖዶስ፦ አወንታዊ የቤተሰብ አብነት ማስተጋባት ያለው አስፈላጊነት


RealAudioMP3 ቤተሰብ በሚያጋጥመው ችግር ሁሉ ለብቻው ሳይተው መሸኘትና መደገፍ ግዴታ ነው። ሆኖም ግን ስለ ቤተሰብ ሕይወት አወንታዊ የሆነው ሁሉ ማስተጋባት ያለው አስፈላጊነት የተበከረበት በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከውጭና ከውስጥ ለመጡት ልኡካን ጋዜጠኞች ቤተሰብ ዙሪያ በመወያየት ላይ ስላለው ሲኖዶስ አስመልከት በሰጡት መግለጫ የድኅረ ውይይት ሰነድ ጠቅሰው እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ በተለይ ደግሞ ሲኖዶሱ በአሥር ንኡሳን የውይይት ቡድን በመከፋፈል ያካሄደው ጉባኤ መሠረት የተጠናቀረውና ይፋ የሆነው የድኅረ ውይይት ሰነድ ግልጸንትና ሙሉ ሱታፌ የሚያንጸባርቅ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማብራራት፣ ሰነዱም በንኡሳን የውይይት ቡድን አማካኝነት የተካሄደው ውይይት ጽማሬ ሲሆን፣ ሆኖም ይኽ የጽማሬ ሰነድ የሲኖዶስ ጠቅላይ የፍጻሜ ሰነድ አለ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፣ እንዲህ በመሆኑም ለመላው የሲኖዶስ ሂደት ደጋፊ ሰነድ ነው እንዳሉ ደ ካሪሊስ አስታወቁ።
የድኅረ ውይይት ሰነድ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ የማጠቃለያ ይፋዊ ሰነድ ለማቅረብ የሚደግፍ በመሆኑም እንደሚከለስና ምናልባት የሚጠናቀረው የፍጻሜ ሰነድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ጸድቆ በይፋ ሊቀርብ እንደሚችል ከገለጡ በኋላ፣ የመጨረሻው የንኡሳን ቡድን ሰነድ አርቆ ለማቅረብ በተመረጠው ድርገት አፍሪቃን የሚወክሉ ብፁዓን ጳጳሳት እንዳልነበሩ ያስተዋሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዱርባን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ናፒየር እንዲሁም ኒው ዘላንድ የሚወክሉ ብፁዕ አቡነ ሃርት መምረጣቸው አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ ከዚህ ጋር በማያያዝ የዓንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሙለር በቅርቡ ከአንድ ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ያላሉት ሃሳብ ታክሎበት ለንባብ በመብቃቱ በዙ እያናገረ ስላለው ጉዳይ ብጹዕነታቸው እንዳስተባብል አደራ ስላሉኝ በርግጥ ብፁዕ ካርዲናል ሙለር ያልተጠቀሙበት ቃላት ማስፋፋት የተገባ አይደለም ሲሉ፣ በመቀጠልም የቪየና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦር በበኩላቸውም፦ ቤተሰብ ከግብረ ገባዊ ኃላፊነት ባሻገር ያለው አወንታዊ ሚና መመልከቱ አስፈላጊ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ በቤተሰብ ስለ ሚከሰተው ችግር ላይ ብቻ ያተኰረ ሳይሆን አወንታዊ ግጽታው በቤተሰብ ያለው ሕያውነት ውበቱ ባጠቃልይ ቤተሰብ ውበትና ውህበት መሆኑ የሚያረጋግጠው ጉዳይ ላይ ጭምር ያተኮረ እንዲሆን አደራ በማለት ያቀረቡት ጥሪ አስታውሰው፣ የቤተሰብ ሕያው ገጽታው ላይ ሲተኰር በርግጥ ቤተሰብ የሚያጋጥመው ችግር ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ ማቅረብ ይሆናል፣ ባጠቅላይ የቤተሰብ ተጨባጭ ሁኔታ የዳሰሰ ሲኖዶስ ነው” ሲሉ በሲኖዶሱ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ባለ ትዳሮች ውስጥ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት ፍራንኮ ሚያኖ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ ሲኖዶስ በታዛቢነትና በምስክርነት እንዲሳተፉ አንዳንድ ባለ ትዳር ምእመናን በመጋበዛቸው ሲኖዶሱ አርቆ የማሰብ ብቃቱ የሚያሳይል ነው፣ እርሱም የቤተሰብ አወንታዊ ገጽታው ለማጉላት ያለመ መሆኑ አብራርተው፣ በዚህ ሲኖዶስ በታዛቢነት መብት ባለ ትዳሮችን ማሳተፉ ለሲኖዶሱ ዓቢይ ደጋፍና ሃብት ጭምር መሆኑ አስታውሰው፣ የቤተሰብ ውበትና ውህበቱ በማጉላት ቤተሰብ የሚያጋጥመው ችግር በሚገባ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ የሚደግፍ ማስተዋል ነው ሲሉ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝ ብፁዕ ካርዲናል ሾንበርን፦ “በርግጥ አንዳንድ የሲኖዶስ አበው አደራ ከዓንቀጸ እምነት እንዳይወጣ የሚል ጥሪ አቅርበዋል፣ የተገባ ጥሪም ነው። ሆኖም ግን መቼም ቢሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዳሉት ቤተ ክርስቲያን ጦርነት በሚካሄድበት ሥፍራ እንደሚተከለው የጤና ጥበቃ መስጫ ድንኳን ነች፣ ስለዚህ ይኽ ጥሪ ችላ የማይባል ነው። ቤተሰብ የወደቀበት ችግር ለይቶ ከጎኑ በመሆን በሚገባ መሸኘትና መደገፍ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት እንዲህ ቢሆን ይሻላል ሲል እናት አባት ከሰጠው አስተያየት ለየት ያለ አይ እንዲህ ቢሆን ይሻላል ትላለች፣ ስለዚህ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ የቤተሰብ ባህርይ ያለው ነው እንዳውም ስለ ቤተሰብ የሚመክር በምሆኑም ቤተሰበዊ ባህርይ ሊኖረው ግድ ነው። የተለያየ ሃሳብ ቢቀርብ የሚያስገርም አይደለም። በተለያየ ችግር የሚገኙት ቤተሰብ ከጐኑ በመሆን መደገፍና ማስተናገድ ቤተ ክርስቲያን ከእያንዳንዱ ዜጋ ጾታዊ ስሜት በቅድምያ የሰው ልጅ ሰብአዊነት ላይ ነው የምታተኩረው፣ በቅድሚያ ጾታዊ ስሜት ከመመልከት በፊት ሰውን መመልከት ያስፈልጋል” በማለት ባሰሙት ሃሳብ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.