2014-10-15 18:39:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ
በዚህ ሳምንታት ስለ እናታችን የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስትያን በጉዞ ስላለው የእግዚአብሔር ተናግረናል፣ ዛሬ ደግሞ ይህንን ጥያቄ ለማቅረብ እፈልጋለሁ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብ መጨረሻው ምን ይሆን? የእያንዳንዳችን መጨረሻስ ምን ይሆናል? ምንስ እንጠባበቃለን? ሓዋርያው ጳውሎስ ይህንን ዓይነት ጥያቄ ላቀርቡለት ለነበሩ ለተሰሎንቄ ማኅበረሰብ ብዙ ትንታኔ ካቀረበ በኋላ እነኚህን በአዲስ ኪዳን ከሚገኙ አንዳንድ ቆንጆ ቃላት ያቀርባል፣ “እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን” (1ተሰ 4፤17)፣ እንዲያው ስታነባቸውና ስትሰማቸው ቀለል ያሉ ቃላት ይመስላሉ ነገር ግን ታላቅ የተስፋ ይዘት አላቸው፣ “እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን” የሚለውን ታምናላችሁ ወይ? እስቲ በአንድነት ለሶስት ጊዜ እንደጋግመው፣
በራእዩ ለዮውሓንስ እንደምናገኘው አነጋገሩ የነቢያትን ቃላትና አቋም በመጠቀም ትእምርታዊ ነው፣ “ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።” (ራእ 21፡2) ይላል፣ የምንጠባበቀው ይህ ነው፣ የቤተ ክርስትያንችን መጨረሻም እንዲሁ ነው፣ የእግዚአብሔር ሕዝብም እንዲህ ባለ መንገድ ከቀን ወደ ቀን ከሙሽራዋ ጋር ለመገናኘት እንደምትዘጋጅ ሙሽራ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ለመገናኘት እየተዘጋጀ ነው፣ ብሂል ወይም የአነጋገር ዘይቤ አይደለም እውነተኛ ሰማያዊ ሰርግ በደምብ ይከናወናል፣ ምክንያቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኛ ሰው ሆኖ በሞቱና በትንሳኤው ከእርሱ ጋር አንድ አድርጎን እንደ አንድ ሕዝብ እኛ ሁላችን ሙሽራዋ ማለትም ቤትክርስትያኑ ነን፣ ይህም እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ ያቀደው የደህንነት ዓላማ ሆኖ በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክና በእያንዳንዳችን ታሪክ እውን የሚሆን አጠቃላይ የደህንነት ታሪክ ነው፣ ይህንን ወደ ፊት የሚያራምደው ደግሞ ጌታ ራሱ ነው፣
ከዚህ ባሻገር የሚያጽናንና ልባችንን የሚከፍት ሌላ ነገርም አለ፣ በዚችው የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ በሆነቸው ቤተ ክርስትያን “አዲስቷን ኢየሩሳሌም” ይሳየናል፣ ይህንም የሚያመለክተን ቤተ ክርስትያን ሙሽራ ከመሆን ባሻገር በምሳሌያዊ አነጋገር የፍጽምና ምልክት የሆነቸው የሰው ልጅ ሁሉ በሰላምና በደስታ በፍጹም ፍቅር አብሮ የሚኖርባት ከተማ መሆንዋን ነው፣ ዮሓንስ በራእዩ አያይዞ የሚያቀርብልን ምሳሌም አለ፣ ሁላቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ በአንድ ድንኳን በዚች ከተማ እንደሚቀመጡ ለማመልከት “ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤(ራእ 21፡3)” ይላል፣ በዚችው ድንኳን ደግሞ ምንም ዓይነት የዘር የወገን የሃይማኖት መለያየት መገለል እንደማይኖር “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” (4) በማለት ሁላችን በክርስቶስ አንድ እንደምንሆን ያረጋግጥልናል፣
በዚሁ አስደናቂ ትእይንት ልባችን ኃያል በሆነ ተስፋ መጽናናት ይሰመዋል፣ አስተውሉ የክርስትያን ተስፋ የሆነ ምኞት ወይም ከንቱ ፍላጎት አይደለም ለአንድ ክርስትያን ተስፋ ማለት መጠባበቅ እንዲያው በብርቱ ጉጕትና የጋለ ስሜት የአንድ ምሥጢር የእግዚአብሔር የፍቅር ምስጢት ለአንዴና ለመጨረሻ እውን የሚሆንበትን ፍጻሜ መጠባበቅ ነው፣ ይህንን ምሥጢር በምሥጢረ ጥምቀት ዳግም በመወለድ እንኖረዋለን፣ ይህ መጠበባቅ መምጣት ያለበትን ጌታ ኢየሱስን መጠባበቅ ነው ይህ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ በየዕለቱ ቅርባችን እንዲሆን ያደርገዋል፣ በመጨረሻም በአንድነቱና በሰላሙ ወደ ፍጽምናና ቅድስና ያደርሰናል፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያንም እንደ የደህንነት እርግጠኛ ምልክት ሆና ለአጠቃላይ የሰው ልጅ ዘር ብርሃን ሆና ርኅሩኅና ይቅር ባይ ከሆነው እግዚአብሔር ጋር ሊገናኝ ይችል ዘንድ ይህንን የተስፋ ሻማ አብርታና በደምብ በምትታይበት ሁኔታ መጠበቅ አለባት፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች የምንጠባበቀ ይህ ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለስ፣ ሙሽራ የሆነቸው ቤተ ክርስትያን ሙሽራዋን ትጠባበቃለች፣ ነገር የሚከተለውን መጠየቅና ማስተንተን አለብን፣ የዚህ መጠባበቅ የዚህ ተስፋ እውነተኞች ብርሃን የለበስንና ታማኝ ምስክሮች ነንን? ማኅበረ ክርስትያኖቻችን የጌታ ኢየሱስን መመለስ በመጠባበቅ እርሱ በመካከላቸው እንዳለ ሆነው ይኖራሉን? ወይስ የደከሙና የተሰላቹ ሆነው የድካሙና የተስፋ መቍረጥ ጫና የከበዳቸው ሆነው ይኖራሉ? ምናንልባት እንደ ሞኞቹ ደናግሎች እኛም የእምነት ዘይታችን የደስታ ደስታችን ያልቅ ይሆን?
የተስፋ እናት እና የሰማይ ንግሥት የሆነችን እመቤታችን ድንግል ማርያምን ጌታን በማዳመጥና እርሱን በመጠባበቅ ለመኖር እንድንችልና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር በመሞቅ መጨርሻ በሌለው ደስታው እንድንደርስ ታስችለን ዘንድ እንለምናት፣ ይህንን ደግሞ ከጌታ ጋር በሙላት አንድ መሆን ነው፣ በመግብያው ላይ ያልክህዋችሁን እንዳትረሱት አሁንም እንደገና ለሶስት ጊዜ እንድገመው፣ “እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን” እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.