2014-10-15 14:44:45

ሲኖዶስ፦ የድኅረ ውይይት ሰነድ ጊዚያዊ ነው


RealAudioMP3 በአገረ ቫቲካን ቤተሰብ ዙሪያ በመካሄ ላይ ያለው ሦስተኛው ልዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያረቀቀው Relatio post disceptationem- የድኅረ ውይይት ሰነድ” ለገዛ እራሱ የሚከለስ እንጂ የፍጻሜ ሰነድ አለ መሆኑ የስብከተ ወንጌል ለአሕዛብ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ እንዲሁም የዱርባን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዊልፍሪድ ናፒር በጋራ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጥዊ መግለጫ እንዳብራሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።
የብፅዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ የዚህ ሦስተኛው ልዩ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከመጀመሩ በፊት ቅድመ የውይይት ሰነድ በማስደገፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. የሲኖዶስ የድኅረ ውይይት ሰነድ አስደገፈው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡ በኋላ የመገናኛ ብዙሃን የድኅረ ሲኖዶስ ሰነድ መሠረት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በማደገፍ እየሰጡት ያለው ዜናና ሃተታ የተሟላ ግንዛቤ ያላቸው እንደማይመስል፣ ይኽም የሚሰጡት ዜና የሚያረጋግጠው እውነት መሆኑ አብራርተው፣ የሲኖዶስ የመመሪያ ደንብ፣ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚካሄድ ሲኖዶስ ቀደም በማድረግ የማወያያ ሰነድ ይቅርበ የሚልና ሲኖዶሱ ከተካሄደ በኋላ የሲኖዶስ የኅድረ ውይይት ሰነድ እንዲቀርብ ያዛል፣ ቢሆንም ይኽ የድኅረ ውይይት ሰነድ የፍጻሜ ሰነድ አለ መሆኑ ያብራራል፣ በማለት ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ በሰጡት መግለጫ እንዳሰመሩበት ኢዛበላ አስታወቁ።
ብዙ የመገናኛ ብዙኃን ያተቱበት የድኅረ ሲኖዶስ ሰነድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወይንም የሲኖዶሱ ውሳኔ እንደሆነ አድርገው ሲያቀርቡት ይታያል፣ ሆኖም ሰነዱ ገና ውሳኔ እንዳልተሰጠበት የገለጡት ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ አያይዘው የድኅረ ውይይት ሰነድ ብፁዓን ጳጳሳት በቡድን ተከፋፍለው ውይይት እንዲያካሂዱት ይሰጣል፣ የሲኖዶሱ ሂደት እንዲህ ሲሆን ሆኖም በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. እንዲካሄድ ወደ ተወሰነው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሲኖዶስ የሚሸኝ ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.