2014-10-13 16:29:02

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ.12/10/2014)
የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ለሁሉም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. እኩለ ቅን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ፊት ከሚገኘው ከሐዋርያዊ መንበራቸው መስኮት ሆነው እንደ ተለመደው ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በለገሱት አስተምህሮ፦ “የእግዚአብሔር የማዳን እቅዱ አለ ምንም አድልዎ ለሁሉም ሰው ልጅ በማቅረብ ሁሉን ለመዳን የጠራ ነው፣ ቤተ ክርስቲያን በሮችዋን ከፍታ ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችን ክልሎች የምታመራ መሆን አለባት እንጂ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ተዘጋ የምገልጥ አንዲት ትንሽየ በሩችዋን የዘጋ ቤተ ክርስቲያን አስመስሎና አሳንሶ ማቅረብ አይኖሩ” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
ትእግስት የዋህነት ልክ ያለው ቢሆንም ቅሉ የእግዚአብሔር የዋህነትና ትእግስት ከዚህ ልክነት ባሻገር መሆኑ በላቲን ሥርዓት መሠረት የተነበበው የዕለቱ ቅዱሳን ንባባት በተለይ ደግሞ ወንጌል አስደግፈው ወደ ልጁ ሰርግ ምርጦች የሆኑት የታደሙት የቀረበላቸው ጥሪ ችላ በማለት እንዳውም መታደማቸው ያሰለቸቻቸው ያስቆጣቸው ነው የሚመስለው፣ ታዲዮ ያ ጌታ በልጁ ሰርግ የተገባ የማይባሉ ለመታደሙ ደረጃው የሌላቸው የሚባሉት ከምርጦቹ በላይ ክቡሩ ያላቸው ሆነው መገኘታቸው ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን ድንበር አልቦ ነች፣ ሁሉም ታድማለች ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር የማዳን እቅድ ሰፊ ሁሉን የምታቅፍ ኵላዊት ነች፣ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ምንም’ኳ የታደሙት አሉታዊ ምላሽ ቢሰጡበትም በምንም ተአምር የሚቋረጥ አይደለም፦ “ወደ ልጁ ሰርግ የጠራው ጌታ የታደመው ባለ መገኘቱ ተስፋ አይቆርጥም ወይንም ሰርጉን አይሰርዝም፣ በዓሉን አያቋርጥም፣ አድማሱን ሰፋ በማድረግ ኵላዊነት ባህርዩ በማረጋገጥ፣ ውስንነትን በመሻገር የሰርጉ አገልጋዮች ወደ ጎዳናዎች ሁሉ በመላክ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ አድሙ ሲል ይልካል፣ በዚያን ሰዓት በጎዳና የሚገኘው ቤት አልቦ ድኻው ከኅብረተሰብ የተነጠለው ቤት ንብረት የሌለው ነው። ያ የሰርጉ ዳስ በሕዝብ ተሞላ” እግዚአብሔር ለሚያቀርበው ጥሪ እያንዳንዱ ምላሽ ሊሰጥበት መጠራቱና፣ ማንም ለጥሪው የተገባሁኝ ምርጡ እኔ ነኝ የማለት የመብት ወይንም ይይገባኛል ጥያቄ የለውም፦ “የእግዚአብሔር ጥሪ ልክ ፈሪሳውይንና ሊቀ ካህናት ዋናውን መካከለኛውን ሥፍራ በመያዝ የተገቡ ሆነው ይሰማቸው የነበረው ዓይነት መንፈስ የሚያሸንፍ የሚያስወግድ ነው። ምንም’ኳ በውጭ ያለ ከበሩ አጠገብ ያለ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉም ዋና ሥፍራ ያለው ነው። ሁሉም በእግዚአብሔር ቤት ማእከል ነው” የእግዚአብሔር ደግነት የዋህነት ያ በኅብረተሰብ የማይታየው የተነጠለው የተረሳው ቅርብ የሚያደርግ ማንንም የማይዘነጋ የማይታውን የሚያይ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲገልጡ፦ ሁላችን የእግዚአብሔር መንግሥት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን አጥር ውስጥ የሚገለጥ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን አጥር ውስጥ የሚታጠር አድርጎ የማቅረቡ ፈተና ማሸነፍ አለብን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን አጥር ውስጥ ወስኖ መግለጥ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን እንደ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰፊ ኵላዊነት አድማስ ያላት መሆን ይገባታል፣ ሁላችን የሰርጉ ነጭ ልብስ ለብሰን መገኘት ይኖርብናል፣ ነጭ ልብስ ሲባል ሌላ ነገር ሳይሆን የሚሰዋ ፍቅር ምስክርነት ማለት ነው። ፍቅር ለእግዚአብሔር ፍቅር ለባለንጀራ ፍቅር ማለት ነው” ብለው በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ስላለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ በእምነታቸው ምክንያት ስለ ሚሰቃዩትን ለስደት ስለ ሚዳረጉት በማርያም አማላጅነት እንጸልይ፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚሰዋ ፍቅር ተጨባጭነቱ ለማረጋገጥ በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን የሚካሄደው መርሃ ግብር አመስግነው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ለሁሉ መልካም እሁድ ተመኝተው የለገሱት አስተምህሮ እንዳጠናቀቁ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.