2014-10-13 19:50:51

ቤተ ክርስትያን ቆማ የቀረች እንደሆነ ትታመማለች!


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በትናንትናው ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ ቫዚሊካ የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉት ወቅት በዕለቱ በተነበበው ወንጌለ ማቴዎስ 22፤1 “ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ሰበሰቡ” በሚለው ቃል በመመርኰዝ ለምስጋናው ምክንያት ለነበረው እ.አ.አ ባለፈው ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓም ቅድስናቸው የታወጀው የ17ኛው ክፍለዘመን ፈረንሳውያን ልኡካነ ወንጌል ቅዱስ አቡነ ፍራንቸስኮ ደላቫል እና ቅድስት እናት ማርያ ዘኢንካርናስዮነ በማስታወስ “ሁሉንም ለመጥራት በመላው ዓለም ጐዳናዎች ወጡ” ብለዋል፣
ባለፈው እነኚሁ ሁለት የፈረንሳይ አገር ተወላጆች ለስከተ ወንጌል እስከ ካንዳ በመሄድ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የከበክ ቤተ ክርስትያን መሥርተዋል፣ የጌታን የምሥራች ዜና ወደ ሁሉም ለማዳረስ ብዙ ላእካነ ወንጌል ሕይወታቸውን መሥዋዕት እስከ ማድረግ ሰብከዋል፣ ዛሬም ቢሆን በዚሁ መስክ የጌታን ቃል ለመስበክ ቈርጠው የተነሱና በየቦታዊ ከስደትና እስር አልፈው በየዕለቱ ሰማዕታት የሚሆኑ አሉን፣
ቤተ ክርስትያንን ይህንን ከማድረግ የቆመችና በገዛ ራስዋ ብቻ ተዘግታ የቀረች እንደሆነ ትታመማለች በማለት ቤተ ክርስትያን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ሰምታ በመላው ዓለም ጐዳናዎች ለሚገኙት ለመጥራትና ለጌታ ለማቅረብ መንሳት እንዳለባትም አመልክተዋል፣
በሚስዮናውያን የሚታወቁት ሰባክያነ ወንጌል የጌታ ወንጌልን በሕይወት ለመኖር ብርታት ያላቸው ናቸው፣
“የቤተ ክርስትያን የስብከተወንጌል ተልእኮ በመሠረቱ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚነገርበት ዜና ሠናየ ሆኖ ይህም የእግዚአብሔር ርኅራኄና ይቅርባይነትን የሚገልጥ ነው፣ እነኚህ ደግሞ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት ሞትን ከሞት ተለይቶ መነሣት ለሰው ልጆች የተገለጡ ናቸው፣ ሰባክያነ ወንጌል ትኵረታቸውን በተሰቀለው ክርስቶስና በመስቀሉ በማድረግ ብዙ ጸጋ ተቀብለዋል ነገር ግን ይህንን ጸጋ ለገዛ ራሳቸው አምቀው አላስቀሩትም፣ ቅድሱ ጳውሎስ እንደሚለው በድህነትና በሃብት በጥጋብና በረሃብ መኖር ችለዋል ይህንን ሁሉ የቻሉት ደግሞ ጌታ በሰጠባቸው ጸጋ ነው፣
“በዚሁ የእግዚአብሔር ሃይል በመላው ዓለም ጐዳናዎች ወጥተው በጌታ በመተማመን በብርታት መሥራት ጀመሩ፣ የአንድ ሰባኬ ወንጌል ወይንም የአንዲት ሰባኪተ ወንጌል ሕይወት እንዲህ ነው፣ ከአገራቸው ከቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ወደ ሩቅ አገር ወንጌልን ሲሰብኩ በዚሁ ቀናት ለብዙ እኅቶቻችንና ወንድሞቻችን እያጋጠመ እንዳለው አብዛኛውን ግዜ ተገድለዋል፣ ዛሬ በቅድስናቸውን እግዚአብሔር የማመስገን ምክንያት የሆኑን የካናዳ ሰባክያነ ወንጌል ዝክር በምንደርግበት በተለይ ደግሞ የከበክ ቤተ ክርስትያን በበኵልዋ የሰባክያነ ወንጌል ምንጭ እንድትሆን እንጸልይ፣
“ይህ ተዝካር ቅንነትን እንዳንረሳ ያድርገን፣ እንዲሁም ብርታታቸውንም እንዳንተው ያድርገን፣ ዲያብሎስ ቀናተኛ ስለሆነ ይህንን የሰባክ ያነ ወንጌል ምንጭ የሆነውን ቦታ በቀላሉ እንዳይተወው ማወቅ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ የከበክ ቤተ ክርስትያን እንደቀድሞዋ ሰባክያነ የምታፈራ ትሆን ዘንድ እንጸልይ፣ ሰማዕታትዋም በደማቸው የዘርዋትናና ያሳደግዋት ለጌታ ጥሪ ክፍት የሆኑ ወንጌል የሚሰብኩ ወንዶችና ሴቶች እንድታፈራ ያድርጋት፣ ባለንበት ወቅት ለዚሁ ቅዱሳን ይህንን አማልዱልን ማለት ያሰፍልጋል፣ሲሉ ጸሎት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.