2014-10-10 16:20:58

ሲኖዶስ፦ ቤተ ክርስቲያን የገቢ ቀረጽ የሚከፈልበት ቤት (የጉምሩክ ቤት) ሳትሆን አባታዊ ቤት ነች


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እዚህ ቤተሰብ ማእከል በማድረግ እ.ኤ.አ. ከ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ ስላለው ሦስተስኛው ልዩ ይፋዊ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በየዕለቱ ስላ ካሄደው ውይይት ባጠቅላይ ስለ ዕለታዊ ውሎው በማስመልከት የሚሰጡት ጋዜጥዊ መግለጫ በመቀጠል ይኸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ማምሻው የሲኖዶስ የአራተኛው ቀን ውሎው በማስመለከት፦ “ለሕይወት ክፍት መሆን የሚለው ውሳኔ ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወቅታዊ ዓቢይ ተጋርጦ” ይኽም በአሁኑ ወቅት በዓለም እየተስፋፋ ያለው የሞት ባህል ቤተሰብ በኑባሬ የተቀበለው ለሕይወት ክፍት የመሆን ጥሪው አማካኝነት በመጋፈጥ ለማግለል እንዲችል የሚያግዝ በትክክል በዚህ ላይ ያተኮረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያለው አስፈላጊነት ማእከል ያደረገ ውይይት መከናወኑ እንዳብራሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።
ምህረት በሚል ሃሳብና ተግባር ቤተ ክርስቲያን የሰውን ልጅ በትዕግስት የመሸኘት ኃላፊነት አላት በሚል ጽማሬ ሊጠቃለል የሚችል የአራተኛው ቀን ውሎው ብዙ ሃሳብ የቀረበበትና በታላቅ ስሜት ውይይት የተካሄደበት እንደነበር አባ ሎምባርዲ በማብራራት ቤተ ክርስቲያን ጤናማውና በተለያየ ቀውስ የተጠቃው ቤተሰብ የምታቅፍ እንጂ የደከመው ችላ የምትል እንዳልሆነችና እንዳውም የቤተሰብ ቀውስ ላጋጠመው በበለጠ ቅርብ መሆንዋ ብፁዓን የሲኖዶስ አበው፦ “ምስጢረ ተክሊል የሚመለከት አስፍሆተ ወንጌል በርግጥ ምሥጢረ ተክሊል አፍርሰው ብሔረ ጋብቻ ለፈጸሙት ቅዱስ ቁርባን ሱታፌ እንዲኖራቸው ጨርሶ የሚቻል አይደለም በሚል መሠረታዊ ሓሳብ ከቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት ጋር የሚስማማ ነው። ይኽም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ ተክሊል የይማፈርስ መሆኑ ለሰጠው ትምህርት ታማኝ መሆንን የሚያመለክት ነው። የቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት መሠረት ያደረገው ውሳኔ የፍርድ በትር ሳይሆን የምህረት መሣሪያ ነው። በመሆኑም ያንን የሚያጋጥመው የፍች ጉዳይ በዚህ ሁኔታ በመመልከት የተፋቱት ጠቅለል በማድረግ በአንድ ውሳኔ መመልከት ሳይሆን፣ የእያንዳንዱ ችግር በግል አመዛዝኖ መመልከት ወሳኝ መሆኑ የተገለጠበት ውይይት ነበር። ምኅረት የሚል እንጂ የቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት የሚጠይቀው ሁነት እጥያቄ ውስጥ ገብተዋል ማለት እይደለም” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ ገለጡ።
የሲኖዶስ አበው ስለ ተፋቱትና ዳግም ብሔረ ጋብቻ ስለ ፈጸሙት ጉዳይ በተመለከተ በተካሄፈደው ውይይትና የሓሳብ ልውውጥ ብፁዓን ጳጳሳት ያላቸው አመለካከት የሚስማማ ከመሆኑም ባሻገር፣ ምሥጢረ ተክሊል በቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች አማካኝነት ለመሻር የሚደረገው የአሠራር ሂደት የሚፈጀው ረዥም ዓመታት በእውነቱ አጠር ለማድረግ ያለው አስፈላጊነት ብሎም በቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች ብቃት ያላቸው ዓለማውያን ምዕመናን ማሳተፍን በዚህ የተልእኮ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረግ፣ እውነትና የገረፍ ገረፍ አይነት አሠራር እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚጠይቅ አቢይ ኃላፊነት መሆኑ ሲያመለክቱ፦ “አያንዳንድ የሲኖዶስ አበው ስለዚሁ ጉዳይ በተመለከተ ተጨባጭ አብነቶችን በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች (በሰበካዎች ደረጃ በብፁዓን ጳጳሳት ሥር በሚመሩት የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች) በሚገባ ማዋቀር ማደስ፣ ይኽ ሥራ እውነት የሚኖር ፍትህ ያካተተ አሠራርት መሆኑና ከዚህ ጋር በማያያዝም ለሕዝበ እግዚአብሔርና ለእያንዳንዱ ሰው እርባና ታስቦ ተፋተው የሚኖሩት በትዳር ቀውስ የተጠቁትን በልዩ የሚመለከተ ብቃቱ ባላቸው የውሉደ ክህነት አባላት የሚመራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት” ማሳወቃቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፣ ይኽ አይነቱ አሠራር በፍቅር ሥር ማለት በክርስቲያናዊ ፍቅር መመራት ያለበት ሆኖ ወንጀለኛ አንተ ነህ ወንጀለኛይቱ አንቺ ነሽ ብሎ ፍትህና እውነት ክርስቲያናዊ ፍቅር ያልታከለበት ብይን ለመስጠት ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ግምት የሚሰጥ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማረጋገጥና በተለይ ደግሞ የቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ቢቋረጥም የቤተ ክርስቲያን ልጅና የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን የሚሰርዝ እንዳልሆነ ብፁዓን የሲንዶስ አበው እንዳሰመሩበትና ስለዚሁ ጉዳይ በተመለከተ በተለያዩ ሰበካዎች፦ “በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ የሌላቸው በልዩ የሚመለከት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የጋራ መንፈሳዊ መርሃ ግብር፣ በቅዱስ ቁርባን ተጨባጭ ሱታፌ የሌላቸው ቢሆንም ቅሉ መንፈሳዊ ሱታፌ እንዳላቸውና ይኸንን እንዲኖሩ የሚያግዝ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ማጠናከር” ከዚህ ጋር በማያያዝም ምሥጢረ ተክሊል በወንድና በሴት መካከል በቤተ ክርስቲያን ምስክርነት የሚጸና የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ሆኖም ከዚህ ዓይነት ውጭ የሆነ ጣምራነት በሚኖሩት ላይ ፍርድ አለ መስጠትና የማይገቡ ገንቢ ያልሆኑት ቃላት በመጠቀም፣ ሰብአዊነት የማያከብር ቃላት መጠቀም እንደማያስፈግ የሲንዶስ አበው እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ መግለጣቸው ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።
ከአንድ ሚስት በላይ የማግባት ልምድ እየጠፋ በመሄድ ላይ መሆኑ፣ በዚህ ዓይነት ልማድ ሥር ይኖሩ የነበሩት የካቶሊክ ሃይማኖ ተቀብለው የተለወጡት ምሥጢረ ቅብአተ ቅዱሳት እንዲቀበሉ ማእከል በማድረግ የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ ምሥጢረ ንስኃ ያቋረጡ ካቶሊክ ምእመናን፣ በተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የሚፈጸመው ቅይጥ ጋብቻ ሕጋዊነት ያለው መሆኑና አለ መሆኑ ማጤን ከዚህ ጋር በማያያዝም በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፍች የሚፈቅደውን አመክንዮ በጥልቀት መመልከት፣ ይኽ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው የጋራው ውይይት አቢይ ድጋፍ መሆኑ የሲኖዶስ አበው በማብራራት ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምበት ቋንቋ ለአማኙ ብቻ ሳይሆን ለማያምነው ጭምር ሊናገር የሚችል መሆን እንዳለበትና የአስፍሆተ ወንጌል ቋንቋ እንዲታደስ የሚያሳስብ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው ባህርያዊ የወሊድ መቆጣጠር ሥልት የልጅ ኃላፊነት ለእናት ብቻ ሳይሆን አባት ያለው ኃላፊነት በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እንዴት መከናወን እንዳለበት፣ ሕይወት ጸጋ በመሆኑም ቤተሰብ ለሕይወት ክፍት መሆን ለክርስትያናዊ ጋብቻ መሠረት ነው። ጽንስ ማስወረድ አቢይ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ነው፣ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን ሁሉም ምእመናን የተስፋ መልእክት በማስተጋባቱ ሚና የላቀ ተሳታፊነት እንዲኖራቸው ብፁዓን አበው እንዳሰሰቡና በመጨረሻም እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅርቡ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2 ቀን እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፍ ቤተ ንባብ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማረጋገጥ ርእስ ዙሪያ የመከረው ጉባኤ መሠረት ስለ መካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚመክር ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንዲረጋገጥ እያካሄደችው ያለው ጥረት ርእስ ዙሪያ የሚወያይ የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መጥራታቸው አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.