2014-10-10 16:25:45

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ አቡነ ምቦንይተገ፦ የቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት በወቅታዊው አገባብ እንዴት መኖር እንደሚቻል የሚያንጽ ነው


RealAudioMP3 ቤተሰብ ጦርነት ግጭት ስቃይ በሚታይበት ክልል ችግር በመቋቋም ሆነ የእርቅ ይቅር የመባባል መሣሪያ በመሆን የሚሰጠው ክርስቲያናዊ ምስክርነት የላቀ መሆኑ በሲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት በሩዋንዳ የካብጋዪ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ስማራግደ ምቦንይተገ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፦ ቤተሰብ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ነው፣ በጦርነት ብሎም ሃይማኖትና ግብረ ገብ በሚያገለው እየተስፋፋ ባለው ባህል ቀዳሚ ተጠቂው ቤተሰብ መሆኑም አብራርተው፣ በሩዋንዳ ተከስቶ በነበረው የዘር ዕልቂትና ጅምላዊ ጭፍጨፋ ጦርነትና ስደት መፈናቀል ያስከተለው ጠባሳ ሁሉ የማግለሉ ታጋሽ ጉዞ ከቤተሰብ ነው የተነቃቃው ይኽም ያንን ቤተሰብ በትክክል የሚመለከተ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማረጋገጥ ሊሸገር ተችለዋል፣ የዚያ ዓይነት ችግር እንዳይከሰት የሚሰጠው ሕንጸት ከቤተሰብ የሚጀምር ነው ብለዋል።
በሩዋንዳ የሴቶች ሰብአዊ መብትና ክብር በማነቃቃቱ ረገድ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አስተአዋጽኦ ይኽም የወንድና የሴት እኵልነት የሚያረጋገጠው መሠረታዊ አምክንዮ የሚያበክር መሆኑና በተለይ ደግሞ በሁሉም መስክ የሴቶች ተሳትፎ ማሳየል ማለት ሴትነትና ወንድነት ማቀላቀል ሳይሆን ሁሉ እንደ መሆኑ በአገር በቤተሰብ በቤተ ክርስቲያን ባካባቢ በተለያዩ መዋቅሮች እንዲሳተፉ ማድረግ በሚለው ዘርፍ ቤተ ክርስቲያን በሩዋንዳ አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት የእናትነትና የአባትነት ባህርይ መዛባት እንደሌለበት ታንጻለች።
ይኽ በመካሄድ ላይ ያለው ስኖዶስ አንድ አዲስ የሚሥጢረ ተክሊል ሥርወ እምነት የሚያፈላልግ ሳይሆን በአሁኑ ወቅትና በወቅታዊው አገባብ እንዴት ባለ ሁኔታና ተግባር ሥርወ እምነት ለምኖር ይቻላል ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚሞክር ነው። ሁሉንም ችግር የሚፈታ ሳይሆን በተለያዩ ክልሎች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚያጋጥመው ስለ ቤተሰብ የሚመለከተው ችግር ለመፈታት የሚደግፍ የጋራ መሪ የሆነው ሃሳብ እንድትከተል ኵላዊ መመሪያ የሚወጥን ነው በማለት የካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.