2014-10-08 15:34:30

ሲኖዶስ፦ የቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ማደስ


ስለ ቤተሰብ እየመከረ ያለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ልዩ ሦስተኛው ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ውይይት፦ “ለምሥጢረ ተክሊል የሚሰጠው የቅድመ ዝግጅት ሕንጸት ፍጻሜ ይኽ ቅዱስ ምሥጢር ለመቀበል የሚል አቋም አዘል ሳይሆን አቢይ ትርጉሙና የላቀው ግቡ እውነተኛው የግልና የጣምራዊ ሰብአዊና መንፈሳዊ እድገት” የሚል ዓላማ አዘል መሆን አለበት የሚል ሃሳብ ያበከረ እንደነበር የቅድስት መንበር ዜና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ስለ ውሎው በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀው፣ በዚህ አጋጣሚም ሁከትና ውጥረት የተሞላው መካከለኛው ምስራቅ ለቤተ ክርስቲያን ልብ ቅርብ መሆኑና ይኸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለምታውጀው ብፅዕና ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ካርዲናሎችና ፓትሪያርካት የሚሳተፉበት የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ መጥራታቸውና በዚህ አጋጣሚም ብፁዓን ካርዲናሎች እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2 ቀን እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ውሳኔ መሠረት ስለ መካከለኛው ምስራቅ የመከረው ጉባኤ የፍጻሜ ሰነድ ዝክረ ነገር በማድረግ ስለ መካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ በማካተት የሚወያ መሆኑ የገለጡት አባ ሎምባርዲ በተለያየ ችግር በስቃይ ላይ የሚገኘው መካከለኛ ምስራቅ ለቤተ ክርስቲያን ልብ ምንኛ ቅርብ መሆኑ የሚመሰክር መርሃ ግብር መሆኑ እንዳብራሩም የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎ ሞናኮ አስታወቁ።
ሲኖዶሱ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ውሎው የአስፍሆተ ወንጌል ኅዳሴ ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመረበት አባ ሎምባርዲ ሲገለጡ፦ “ብፁዓን ጳጳሳት በውሎው ቋንቋ ማእከል በማድረግ በሰጡት አስተያየትና ባቀረቡት ሃሳብ የቤተ ክርስቲያን ቋንቋ መታደስ እንዳለበት የሚል፣ መልስ የሚሰጥና ሌላው ሊረዳው የሚችል ቋንቋ መሆን አለበት የሚልና ሌላውም ክርስቲያን ክርስቲያን ቤተሰብና ብሎም ወደ ክርስቲያናዊ ጋብቻ አልሞ የሚያደርገው የጥሪ ጉዞ በቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር የተመራ ሆኖ ደረጃ በደረጃ በቀጣይነት የሚሰጥ መሆን እንዳለበትም ብፁዓን ጳጳሳቱ እንዳመለከቱና በተለይ ደግሞ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ‘የቤተ ክርስቲያን ሙላት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ኅልው ነው፣ ሆኖም ወደ ቅድስና የሚያደርሱ ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ እጹብና እጅግ አስፈላጊ የሆኑት ባህርያት ወይንም መሠረታዊ ነገሮች አሉ፣ ይኽንን አባባል ተምሳይነት መሠረት በማድረግ ከክርስቲያናዊ ትዳርና ከክርስቲያናዊ ቤተሰብ ውጭ በእውነቱ ለቅድስትና የሚያበቁ እጹብ ባይርያት ያሉት እውነተኛ ፍቅር የሚኖርባቸው ተምሳይ ትዳር አለ” የሚል ሃሳብ የሚያንጸባርቁ አስተያየቶች እንደቀረቡ ማስታወቃቸው ሎ ሞናኮ ገለጡ።
የተለያዩ የሲኖዶስ አበው የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት በሚገባ ሊታወቅና ሁሉም ስለ ስልጣናዊ ትምህርት ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ እንዳቀረቡ አባ ሎምባርዲ ሲገልጡ፦ “ብዙውን ጊዜ እንደሚገባው ሳይታወቅ የሚቀረብ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ዓላማውና ግቡ እንዲሁም ጥልቅ ትርጉሙ ለማሳወቅ ጥረት ማድረግና ማነቃቃት ወሳኝ መሆኑ ብዙ የሲኖዶስ አበው በሰጡት አስተያየት እንዳበከሩና ስለዚህ ሥልጣናዊው ትምህርት ስለ ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ምስጢረ ተክሊል የሚናገረውን ለጋብቻ በሚሰጠው ቅድመ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም በክርስቲያናው የሕይወት ደረጃ መሠረት በሚሰጥ ቀጣይ ሕንጸት መርሃ ግብር አማካኝነት መቀጠል አለበት፣ ክርስቲያናዊ ሕንጸት እንደየ ጥሪ መሠረት ቀጣይ መሆን አለበት” የሚል ሃሳብ እንዳሰመሩበት አስታቀዋል።
ቀጥሎም ባካባቢ ውጥረትና ግጭት ሳቢያ በቤተሰብ የሚከሰተው ችግር በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የቤተሰብ ሁኔታ ባጠቃላይ በተለያዩ አገሮች የሚታይ ውጥረትና ግጭት በቤተሰብ ላይ የሚኖረው ተጽኦ ተመስሎው በተመለከተ አንዳንድ ብፁዓን የሲኖዶስ አበው በሰጡት አስተያየት እንዳሰመሩበት የገለጡት አባ ሎምባርዲ አያይዘው የሲኖዶስ አበው መጽሓፍ ቅዱሳዊ ጠቀስ በተለይ ደግሞ ወንጌልና የቅዱስ ጳውሎስ መልክት መሠረት የሚገለጠው ጋብቻ የማይሻር ምሥጢር ብሎ የሚገለጠው ሃሳብ ዙሪያ አስተያየት በመስጠት ሆኖም ከጥንት ልደተ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ በዚህ ዙሪያ ይታይ የነበረው ችግር እርሱም ከእለታዊ ሕይወት ጋር በማገናዘብ ያንን የጋብቻ የማይሻር ባህር የሚል የኢየሱስ ፍላጎት አተረጓጐሙና በዕለታዊ ሕይወት አፈጻጸሙ ዙሪያ አስተያየትና ሃሳብ ማቅረባቸው አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ ሃሳቡ ቀረበ እንጂ የማጠቃለያ ሃሳብ ገና አልተሰጠም እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አስታወቁ።
ሌላው ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ያነሱት ሃሳብ ምስጢረ ተክሊል ለመቀበል ነጻ ፍላጎት በመግለጥ የትምህርተ ክርስቶስ ሕንጸት እንዲሰጣቸው ለሚጠይቁ እንዲሁ በዘልማድ ተቀብሎ ትምህርተ ክርስቶስ ሰጥቶ ምስጢሩ መሥራት ሳይሆን፣ ለቃል ኪዳን በነጻው ፍላጎት ለሚመጡት የነገ ባለ ትዳሮች አለ ምንም ፍርሃት ስለ ምስጢረ ተክሊል ሰፊ ሕንጸት በማቅረብ ለመጋባት ያነሳሳቸው ቅዉም ሃሳብ ለይተው እንዲያውቁ በሚያደርግ ጥልቅ እውቀት መታነጽ ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳጠቃለሉ ሎሞናኮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.