2014-10-06 15:26:49

የር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 05/10/2014)


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባይ እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ቤተሰብ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድግ በእግዚአብሔር ቃል መመገብ ያስፈልገዋል በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ አስተምህሮ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ አስታወቁ።
ሁሉም መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ የመጸለይና የማስተንተን ፍቅር ይኖረው ዘንድ ባሳሰቡበት እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት በብዙ ሺሕ ለሚገመቱት ምእመናን በነጻ መጽሐፍ ቅዱስ መታደሉና ሁሉም ቤተ ክርስቲያን በይፋ ለጀመረችው ስለ ቤተሰብ ለሚመክረው ልዩ ሦስተኛው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እንዲጸልዩ አደራ እንዳሉ ሎሞናኮ ገለጡ።
ከመላ ዓለም የተወጣጡ አገረ ቫቲካን የገቡት የሲኖዶስ አበው በጸሎት እርስ በእርስ በመደማመጥ በጥልቅ አስተንትኖ ስለ ቤተሰብ ለመምከር ስለ ሚያካሂዱት ውይይት፦ “ሁሉም ምእመን በቅድስት ድንግል ማርያም እናትነት በመማጠን የቅድስት ድንግል ማርያም ዘፖምፐይ በሚደገመው የመቁጸሪያ ጸሎት መሠረት በጸሎት እንዲሸኛቸው በተለይ ደግሞ ቤተሰብና መላ ዓለም ሰላም ይታደል ዘንድ ሁሉም እንዲጸልይ አደራ” ብለው በዕለቱ የተነበበው ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 21፣ 33-43 በማስደገፍም፦ “የወይን አትክልት የእግዚአብሔር ሕዝብ ምሳሌ ነው። ልክ እንደ አንድ የወይን ተክል እግዚአብሔር የመረጠው ሕዝብ ብዙ እንክብካቤ ትእግስት የተሞላው ታማኝ ፍቅር ያስፈልገዋል፣ አንድ ቤተሰብ መንከባከብ በጌታ የወይን አታክልት ሥፍራ ማገልገል ማለት ነው። ቤተሰብ በመተማመን በተስፋ ተሸኝተው በመልካም መንገድ እንዲጓዙ በእግዚአብሔር ቃል መመገብ ይኖርባቸዋል፣ ለዚህም ነው ዛሬ የቅዱስ ጳውሎስ ማኅበር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገኝተው በማኅበራቸው የመገናኛ ብዙሃን ሐዋርያ በሆነው በብጹዕ ጃኮሞ አልበሪዮነ ምሥረታ ዝክረ መቶኛው ዓመት ምክንያት ለሁሉን መጽሓፍ ቅዱስ በነጻ ለማደል የተነሳሱት፣ ለዚህ መልካም ተግባርም እናመስግናቸው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አክለው፦ “በእያንዳንዱ ቤተሰብ ቅዱስ መጽሓፍ ይኖር ዘንድ አደራ፣ በመጽሓፍ መደርደሪያ ለማስቀመጥ ሳይሆን ዕለት በዕለት በማንበብ በቃለ እግዚአብሔር ለመመገብ ነው። በግልም ሆነ አባት እና እናተ ከልጆቻቸው ጋር በመሆን በዚህ ቃል ይመገቡ። እንዲህ ሲሆን ብቻ ነው አንዲት ቤተሰብ በሚገባ በመልካም ለማደግ በሚያበቃው ብርሃንና በእግዚአብሔር ቃል ኃይል በምመራት እውነተኛ ማደግን የሚጎናጸፈው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፅዕና የታወጀላት እናቴ ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች የቅድስት ኤልዛቤጥ የፍቅር ደናግል ማህበር አባል እንዲሁም በኢጣሊያ በብሔራዊ ደረጃ ታስቦ የሚውለውን ለያይ ድንበር እንዲወንገድ የሕዝቦች አድነት የሚያነቃቃው ቀን አስታውሰው፦ ለሁሉም የሰው ልጅ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሕይወት የመኖር የኅያውነት መብት ጥብቃ ይረጋገጥ ዘንድ አደራ፣ መንግሥታትና እንዲሁም ዜጎች ለዚህ ለማኅበራዊ ጉዳይ ልዩ ትኵረት በማድረግ በዚህ ዓላማ እንዲተጉ አደራ” ብለው ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር መርተው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መልካም እሁድ ተመኝተው ሁሉንም እንዳሰናበቱ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.