2014-10-06 19:24:41

እውነትን በመናገርና በትሕትና በማዳመጥ ለቤተሰብ መልካም ነገር እንሥራ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ጥዋት በጳውሎስ ስድስተኛ አደራሽ በሚገኘው የሲኖዶስ ጉባኤ ክፍል ሦስተኛው ልዩ ጠቅላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ስለቤተሰብ የሚወያይ ሲኖዶስ ሲከፍቱ “እውነትን በመናገርና በትሕትና በማዳመጥ ለቤተሰብ መልካም ነገር እንሥራ፣” ሲሉ ሲኖዶዱ እንዲሳካና ውጤት እንዲኖረው ከተፈለገ የእውነተኛነትና የትሕትና አስፈላጊነት በማስመር ለሲኖዶስ አባቶች መሪ ቃል ሰጥተዋል፣
ቅዱስነታቸው በሲኖዶሱ መክፈቻ ንግግራቸው አነጥሮ መነጋገር እና በትሕትና ማዳመጥ እንደባቡር ሓዲድ ሲኖዶሱን መምራት ያለባቸው መሠረታውያን ነገሮች ሲኖዶሱ እውነተኛ ሆኖ ሥልጣናዊ የኅብረት ጉዞ እንዲኖረው ያደርጋሉ፣ ቅዱስነታቸው ልክ ትናንትና በቅዳሴ ጊዜ ባቀረቡት ስብከት አጠር ባለና ጥርት ባለ አንጋገር በወንጌሉ እንደተመለከቱት ታማኝ ያልሆኑ የወይን አትክልት ሠራተኞች እንዳይሆኑ በማስጠንቀቅ በዚሁ በጌታ የአትክልት ወይን የተመሰለው የእግዚአብሔር የደኅንነት ዕቅድ እኛም ተጠርተናል ሲሉ እንዳስጠነቀቁት ሁሉ ዛሬም የሲኖዶሱ አባቶችን እናንተ በመላው ዓለም የሚገኙ ልዩ ልዩ ክልላዊ አብያተ ክርስትያናት ድምጽ ነው ይዛችሁ የመጣችሁት ይህም ለሲኖዶሳዊ ጉዞ አንድ ድምጽ ነው፣
“የክልላችሁ አብያተ ክርስትያን ድምጽ በመሆን የቤተሰብ መንገድ በመሆነው በቃለ ወንጌል ለመጓዝ እንድትረድዋቸው ሁኔታቸውንና ችግሮቻቸውን አሰባስቦ ይዞ ወደ ሲኖዶሱ መምጣት ትልቅ ኃላፊነት ነው፤ ለዚህ መሠረታዊ ውል ደግሞ ጥርት ባለ መንገድ መናገር ማለትም በዚሁ ሲኖዶስ ውስጥ እንዲህ ማለት አይቻልም ወይንም ስለኔ እንዲህ ያስባሉ የሚል መጠራጠር አይኖርም ስለዚህ የሚሰማችሁን ነገር ሁሉ ጥርት ባለነገር ተናገሩ፣ብለዋል፣
ባለፈው የካቲት ወር በተደረገው ኮንቺስቶርዮ ዝግ የካርዲናሎች ጉባኤ ቅዱስነታቸው ስለቤተሰብ ሲናገሩ አንድ ካርዲናል “ር.ሊ.ጳ ለማክበር ሲሉ እንዲሁም ር.ሊ.ጳ ሌላ ነገር ይረዳቸዋል በሚል ፍራቻ አንዳንድ ካርዲናሎች የልባቸውን አለመናገራቸው ያሳዝነኛል” ብሎ እንደጻፈላቸው ገልጠው ነበር፣
“ለአክብሮት ወይም ለሌላ ነገር የልብን አለመናገር ሲኖዶሳዊነት አይደለም፣ በጌታ ፊት መናገር እንዳለብን በኅልናችንየ የሚሰማንን ነገር የግድ መናገር አለብን፣ ለዚህ ምንም ሰብአዊ አክብሮትና ፍራቻ አያስፈልግም፣ ልክ ከዚህ ጋር ትይዩ በመሆነ መንገድ ደግሞ በትሕትና ማዳመጥና ወንድሞቻችን የሚሉትን ልብን ከፍቶ መቀበል ያስፈልጋል፣ በእነዚሁ ሁለት ነገሮች ሲኖዶሳዊነት ይካሄዳል፣ ስለዚህ እባካችሁ ይህ የወንድማማችነት መንፈስ ይኑራችሁ፣
“ይህን ስታደርጉ በእርጋታና በሰላም አድርጉት ምክንያቱም ሁሌ ሲኖዶስ ሲካሄድ ከጴጥሮስ ጋር በጴጥሮስ አመራር ስር መደረግ ስላለበት የር.ሊ.ጳ በመካከላችሁ መኖር ለሁላችሁ ዋስትና እና እምነትን ለመጠበቅ ነው ሲሉ ከተማጠኑ ሲኖዶሱ እውን እንዲሆን ላበረከቱት ሁሉ በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል ሎረንዞ ባልዲሰሪ እንዲሁም በሲኖዶሱ ለመሳተፍ ለመጡት ሁሉም አመስግነው በሲኖዶሱ ሂደት ውስጥ ለማገልገል የተመረጡ አፈ ጉባኤም ይሁን ዋና ጸሓፊ እንዲሁም የሲኖዶሱ ተወካይ ፕረሲደንቶች በሲኖዶሳዊ መንፈስ እንደተመረጡ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“የመጀመርያዎቹ ሁለት ማለት አፈጉባኤና ዋናጸሓፊ በቀጥታ በሲኖዶስ አባቶች በድኅረሲኖዶስ ምክርቤት ናቸው የተመረጡት የድኅረሲኖዶሱ ምክርቤት አባቶቹ ቀጥታ በሲኖዶስ የተመረጡ ነበሩ፣ በደንቡ መሠረት ሁለቱ ፕረሲደንቶች በር.ሊ.ጳ መመረጥ አለባቸው እኔ ግን ለእነዚህም ድኅረ ሲኖዶሱ ምክርቤት ለዚህ የሚሆኑ እጩዎች እንዲያቀርቡልኝ ጠይቄ እነርሱ የጠቆሙትን ሰዎች ሾምኩ፣ ሲሉ መግቢያ ንግግራቸውን ደምድመዋል፣

ቅዱስነታቸውን ቃለ ም ዕዳናቸውን ከሰጡ በኋላ የሲኖዶሱ ጠቅላይ አፈጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ ውይይት ከመጀመሩ በፊት “ቤተሰብ ከጐዳናው የተዛባ አይደለም ስለዚህም ቤተ ክርስትያን በተስፋና በርኅራኄ ትመለከታቻለች፣ ቃልኪዳን የማይሻር መሆኑን በማስመር ደግሞ ሁላችን በኅብረት በችግር ላሉት ቤተሰቦች ጥርት ያለ መመሪያ መስጠት ያስፈልጋል” ሲሉ ቤተሰብ ያለውን እሴትና መልካምነትን እግምት ውስጥ በማስገባት በተስፋና በምሕረት ዓይን መመልከት እንደሚያስፈልግ እንጂ በጐዳናው የተዛባ የሚያስመስሉትን ችግሮች ብቻ መመልከት እንደሌለባቸው አሳስበዋል፣
ብፁዕነታቸው በዘመናችን ያሉ ችግሮች ዋና መንሥኤ የሆነው በሰው ልጅ ደካማነትና ለግል ኑሮ ብቻ ባተኮረ አኗኗር ሕይወት እንደአንድ ዕቅድና በግዝያት እውን የሚሆን መሆኑን እንድንዘነጋ ስላደረገን የግዜ ምልክቶችን በማጤን የቤተ ቃለ ወንጌል የሚሰጠንን እውነተኛ መድኃኒት በማጤን በችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን መርዳት ስለሚያስፈልግ ከማንኛው የር እዮተ ዓለምና ሌሎች ፖሎቲካዊ እንቅሳቃሴዎች ነጻ በሆነ መንገድ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ያለውን ሰፊውንና ለሁሉም የሚዳረስ የእምነት ዕሴቶች መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፣
ከቀትር በኋላ ለሚካሄደው አጠቃላይ ውይይትና ክርክር እንዲረዳም አባቶች ከሁሉ አስቀድመው ቤተሰብ የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ዘመደ አዳም የጋራ ዕሴት በመሆኑ እንዲጠበቅ እንዲዳብር አበርትሮ መሥራት እንዲሁም እንድንከላከልለት ያለብን እሴት ነው፣ እርግጥ ነው በምእመናኖንቻችን የቃልኪዳን ትምህርትና ዓንቀጸ ሃይማኖት በሚገባ የሚታወቀውና በተግባር የሚለው በአብዘኛዎች ቸል የሚባል ቢሆንም ይህ ግን ቃል ኪዳንን በክርክር የሚያገባ አይደለም፣ ቃል ኪዳን ከቤተ ክርስትያን ምሥጢራት አንዱ መሆኑና ሊበተን የማይቻል መሆኑን የሚመለከት ጉዳይ በድርድር ውስጥ የሚገባ አይደለም፣
በሌላ በኩል ደግሞ በቃል ኪዳን ችግር የሚኖሩ ቤተ ሰቦች ቤተ ክርስትያን ቤታቸው የአባታቸው ቤት መሆኑን በመረዳት እረኝነታቸውን በተመለከተ የታደሰና በቂ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መምርያ ያስፈልጋል ሲሉ አደራ ብለዋል፣
ከቀትር በኋላ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከአራት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት የመጀመርያ አጠቃላይ የአበው ውይይት እየተካሄደ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.