2014-10-06 15:32:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያንና ኅብረተሰብ ከቤተሰብ ጋር በመገናኘት በመወያየት መታደስ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጠራቸው ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚመክረው ልዩ ሦስተኛው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መክፈቻ ዋዜማ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ስለ ቤተሰብ የሻማ ብርሃን ይብራ በሚል መርህ ቃል ተሸኝቶ በተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት በመሳተፍ ያ በክርስቶስ አይን በልዩ ፍቅር የሚታየው ቤተሰብ በመንከባከብ አብሮ በመወያየት ስለ እርሱ በማሰብ ቤተ ክርስቲያንና ኅብረተሰብ ማደስ የሚያሳስብ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።
“ባለ ትዳሮች በግል ውሳኔ አማካኝነት የሚረከቡት የሕይወት የሱታፌ፣ ለሕይወት ጸጋ ገዛ እራሳቸው ክፍት ለማድረግና ሕይወትን ለማቀብ የትውልድ ትውስታ ለመሆኑ፣ ትውልድ በሕንጸት በመሸኘት ክርስቲያን ቤተሰብ እምነት ለልጆቻቸው በማስተላለፍ የሚኖሩት ጥሪ ነው። ቤተሰብ ተወዳዳሪና መተኪያ የሌለው የሰብአዊነት ሕንጸት የሚረጋገጥበት በመሆኑን ለአንድ ቅንና ተባባሪ ኅብረተሰብ አማራጭ የሌለው እጅግ አስፈላጊ ነው” ካሉ በኋላ ቀኑ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ አመታዊ በዓል መሆኑም አስታውሰው፦ “የሰው ልጅ በጥልቀት የሚጠማው የድህነት መሠረታዊ አስፈላጊው ጸጋ በወንጌል የተገለጠው የምህረትና የጸጋ ቅዱስ ተግባር ነው። ስለዚህ ቤተሰብ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን የዚህ የድህነት ምሥጢር ህያውና ፍርያማ ምልክት እንዲሆን እደራ። ዕለት በዕለት የሚያጋጥመን ተጋርጦ በእውነቱ እይታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በማኖር እንዲንኖር በአስተንትኖ በቅዱስ ቁርባን ፊት ጸሎትና አስተንትኖ በመኖር የሚሸነፍ ነው። በሁሉም ኢየሱስን ተመስሎ ለመኖር ሲሞከር ድካም ሁሉ ይወገዳል፣ የሲኖዶስ ውሳኔ የሰው ልጅና የቤተሰብ ሂደት በሚመራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሥር እንዲተረጎም እንጸልይ። የቤተሰብን መሠረታዊ ፍላጎትን ለማዳመጥና አዳምጦም ተገቢ ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል ስለ ቤተሰብ የሚመክረው ሲኖዶስ በቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ አማላጅነት እንጸልይ፣ ቤተሰብና ኅብረተሰብም ይታደሳል፣ የታረቀች መሃሪ ድኾችን የምታፈቅር በትዕግስትና በፍቅር በውስጥ የሚያጋጥሙና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን ሁሉ የምታሸንፍ ቤተ ክርስቲያን ከወንጌላዊ ሓሴት የምትገኝ ነች ” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው የዚህ ዋዜማ ጸሎት አዘጋጅ ለሆነው ለኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር፣ ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ የአንድ ኅብረተሰብ መሠረታዊ ፍላጎት የሚያዛባ መቀራረብ መደጋገፍ ባጠቃላይ ሰብአዊነትን የሚጎዳ የሕይወት ባህል የሚያገል ድኾች አረጋውያንን የሚያገል ባህል የሚያስፋፋ መሆኑ አብራርተው፣ ስለዚህ ወቅቱ አቢይ ወንጌላዊ እውነት በሚገባ ለማስተጋባት እንዲችል የምሥጢረ ተክሊልና የቤተሰብ ወንጌላዊ ኑሮ እንዲስፋፋ ለሚያደርግ ተልእኮ የሚያነቃቃ ሁኔታ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.