2014-10-03 14:54:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሥራ የሁሉም የይገባኛል ሰብአዊ መብት በገበያው ፖሊቲካ የሚቀያየር አይደለም


RealAudioMP3 የሰዎች እኩልነት በሚል ሥርወ ሃሳብ ላይ የጸና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ሕጋዊነትና ዋስትናውን ማረጋገጥ ይገባል እንጂ በተለያየ ምክንያት ሊቀያየር ወይንም ሊጣስ የተገባ አለ መሆኑና በዚህ መሠረተ ሃሳብ ላይ የሚጠቃለለው የሰው ልጅ ሥራ የማግኘት ሰባአዊ መብትና ክብር በገበያው መለዋወጥ ወይንም በገበያው ፖለቲካ የሚለዋወጥ እንዳልሆነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጳጳሳዊ የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት እያካሄደው ወዳለው ምሉእ ይፋዊ ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው በዓለም የተፈጥሮ ሃብት ለሁሉ በእኩል ለማዳረስና ማንንም ፈጽሞ የማያገል ትምህርት፣ የጤና ጥበቃ እንክብካቤ የማግኘት ሰብአዊ መብትና ክብር ከመቼው በበለጠ እንዲጠበቅና ለዚህ ሰብአዊ መብት አክብሮትና ጥበቃ የሚያበረታታ መዋቅራዊ ህዳሴ አስፈላጊ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት የማኅበራዊ ትምህርት አስተዋጽኦ መሠረት የቤተ ክርስቲያም የማኅበራዊ ትምህርት ሂደቱ በመገምገም ቀጥሎም ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በተሰኘው ዓዋዲ መልእክታቸ አማካኝነት በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ሃሴት በተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክታቸው አማካንነት በቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ሥር ቀጣይነቱ እንዴትና በምን ዓይነት መንገድና ብሎም በአሁኑ ወቅት እንዴት እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ ለይቶ የሚወያየው ዓመታዊው ይፋዊ ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፦ እኩልነት በሚል ሥርወ ሃሳብ ላይ የጸና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ሕጋዊነትና ዋስትናውን ማረጋገጥ እንጂ ይኽ ማኅበራዊና ሰብአዊ መብትና ክብር መሰረዝ በተለይ ደግሞ ሁሉም ሥራ የማግኘት ሰብአዊ መብቱና ክብሩ ዋስትና መስጠት እንጂ በንግድ በቁጠባውና በገንዘብ ፖለቲካ የሚወሰን የሚቀያየር አይደለም፣ ምክንያቱም የንግዱ የቁጠባውና የገንዘብ ፖለቲካ የድኾች ብዛት ከፍ እንዲል በማድረግ ሰዎች ለድኽነት የሚዳርግ ነው። ስለዚህ ይክ ዓይነቱ ስልት ተቀይሮ ኤኮኖሚ ለሰው ልጅና ለማህበራዊ ጥቅም ብሎም የሕዝቦች ተሳትፎ የሚዋስ ዴሞክራሲያዊ መዋቅር የሚደግፍ መሆን አለበት” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“የድኻው ኅብረተሰብ ክፍል ችግርና ማኅበራዊ ፍትህ ግምት የሚሰጥ የፖለቲካ የኤኮኖሚ ኅዳሴና የዓለም ሃብት ለሁሉም ማዳረስ ብሎም በዓለማዊነት ትሥሥር አማካኝነት የሚከወነው ነጻው ገበያ ለሰው ልጅ፣ ለቤተሰብ አገልግሎት በሚል መሥረታዊ ሕግ የሚመራ መሆን አለበት፣ ይኽ ደግሞ የሉኣላዊነት እኩልነት በብሔዊም ዓለም አቀፋዊም ደረጃ በማክበር የአገሮችና የሕዝቦች እኩልነት በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ኅዳሴ እንዲከወን አደራ፣ ፍቅር በሐቅ በተሰየመው ዓዋዲ መልእክት ዘንድ የተመለከተው የዚህ ፍቅር መሠረታዊ ሕግ እጅግ የላቀ ወቅታዊነት ያለው መሆኑና፣ በእውነት የተሞላ ፍቅር፣ በሃሰት ላይ ሊጸና አይችልም። በሐቅ የተሞላ ፍቅር ለስደት የሚዳርጉ ችግሮች፣ አመጽና ግጭት እርሃብና ድኽነት መከፋፈል እንዲወገድ ለሚደረገው ጥረት መሠረት ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.