2014-10-03 15:02:23

ሦስተኛው ልዩ ጠቅላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ


RealAudioMP3 ቤተሰብ ዙሪያ እንዲወያይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጠሩት ሦስተኛው ልዩ ጠቅላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. እሁድ ቅዱስ አባትችን በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ እንደሚከፈት ሲገለጥ የሲኖዶሱ ማካሄጃ ዝክረ ነገር ከወዲሁ ከሁሉም በሁሉም አገሮች ከሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን ከሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ምእመናን መንፍሳዊ ማኅበራት በቀረበው የመጠይቅ ሰነድ መሠረት የተወጠነ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኽ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ሦስተኛው ልዩ ጠቅላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አስመልክተው የቤተሰብ ጉዳይ ለሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የምንኖርበት ወቅት በየትኛውም ክፍለ ዘመን ያልታየ አቢይ የሥልጣኔ ሥር ነቀላዊ ለውጥ እየታየበት ነው። ቤተሰብ-ትዳር-ሕይወት የተሰኙት እሴቶች ከመቼውም በበለጠ በአሁኑ ወቅት በተለያየ መልኩና በተለያየ ዘርፍ ለኅዳሴም ይሁን ለሌላ ጥቅም እየተባለ የሚጋጥሙት ለውጦች ግራ የሚያጋባው የወቅቱን ዓለም አንገብጋቢ ጥያቄ መሠረት ያለው ነው እየተባለ ያጋጠመው የትርጉም የይዞታ መቀያየር በእውነቱ ቀላል አይደለም” ብለው ስለ ቤተሰብ የሚመክረው ሲኖዶስ ከዚህ አንጻር አጠር በማድረግ ያለው አንገብጋቢነት ገልጠው፣ እግዚአብሔር ሰው ብቻው ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም … ሲል የተጋረው የሚጻረሩ ተግባሮች ሰው ለብቻው ይሆን ዘንድ መልካም ነው የሚል ባህል የሚያረማምዱ ግለኝነት ልቁ ለእኔ ባይነት ባህል የሚያስፋፉ፣ ይኽ ባህል በቤተሰብ ላይ እያስከተለው ያለው ችግር በቀላሉ የሚገመት እንዳልሆነም አብራርተው፣ ያ ሰው ብቻው ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም ሲል እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ኢየሱስ እግዚአብሔር ያሰረው ማንም ሊፈታው አይቻለውም ሲሉ ፍጻሜ ሰጥቶበታል፣ የምንኖርበት ዓለም ይኸንን እውነት እንዴት ይተርጉመዋል፣ ቤተ ክርስቲያን ለወቅታዊው ዓለም ምሥጢረ ተክሊል በወንድና በሴት መካከል የሚጸና መጻኢን በመጪው ትውልድ ዋስትና የሚያሰጥ ነው። ስለዚህ የሰው ዘር ልዩ ሃብት ነው። ይክ መሠረት መናጋት የለበትን ብለዋል።
ከዚህ ጋር በማያያዝ ቤተሰብ ለተለያየ ችግሮች የሚያጋልጠው ሥራ እጥነት፣ ድኽነት የልጆች ችግር ባጠቃላይ ወቅታዊው ዓለም በቤተሰብ ላይ የሚደቅነው አበይት ችግሮችን ለይቶና እንዴት በመጋፈጥ መልስ ለመስጠት ለመምከር ነው። ስለዚህ ተቀዳሚው ተጋርጦ የግለኝነትና ለእኔ ባይነት የስግግብርነት ባህል ነው፣ ይኽ ለእኔ ባይነት የሁሉም ሚዛን እየሆነ በመጣቱም ስለ ሌሌላው ማሰብ ለሚለው ሰብአዊ ጥሪ እክል እየፈጠረ ቤተሰብ አስፍላጊ አይደለም እንዳውን እንቅፋት ነው ለሚደመድመው ባህል በር የከፈተ፣ በምጢረ ተክሊል እያስክተለው ያለው እንቅፋት ቀላል አይደለም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.