2014-10-01 18:51:57

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! እግዚአብሔር ከመጀመርያ ቤተክርስትያኑን በመንፈስ ቅዱስ ልዩልዩ ስጦታዎች በማበልጸግ ሕያውና ፍርያማ እንድትሆን አደረጋት፣ ከእነዚህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ለመንፈሳዊ ሕንጸትዋና የማኅበርዋ አባላት ጉዞ የሚያገለግሉ ልዩ ስጦታዎች አሉ፣ እነዚህን ስጦታዎች ካሪዝማ እንላቸዋለን፣ አሁን በዚሁ ትምህርተ ክርስቶስ ካሪዝማ ወይንም ልዩ ስጦታ ምን ማለት ይሆን? እንዴትስ ልናውቀውና ልንቀበለው እንችላለን? ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከሁሉ በላይ ደግሞ እነኚህ ልዩ ስጦታዎች ቤተ ክርስትያናችንን በመከፋፍል ችግር ይፈጥራሉ ወይንስ እንደመልካም ነገር ተቀብለን እንገለግልባቸዋልን?
በዕለታዊ ዘይቤ ስለ ካሪዝማ ወይንም ልዩ ስጦታ ሲወራ ልዩ ባህርያዊ ችሎታ እንደመኖር ይገመታል፣ ለምሳሌ ያህል ይህ ሰው ለማስተማር ልዩ ችሎታ ወይንም ስጦታ አለው እንላለን፣ እንዲሁም አንድ በእውቀት የተካነ ሰዎችን የማግባባትና የመሥራት ችሎታ ያለው ካየን ካሪዝማቲክ ነው ልዩ ስጦታ አለው እንላለን፣ ካሪዝማቲክ ምን ማለት ነው ያልን እንደሆነ ግን እዛ ቆመን እንቀራለን፣ በክርስትያናዊ አመለካከት ግን ካሪዝማቲክ ወይም ልዩ ስጦታ ያለው ሲባል ከግላዊ ዕውቀትና ጠባይ ከፍ ያለ ነው፣ ካሪዝማ ስንል ከእግዚአብሔር አብ የተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ሥራ አማካኝነት የምናገኘው ጸጋ ነው፣ ይህ ስጦታ የሚታደለው አንድ ሰው ከሌሎች የበለጠ ሆኖ ወይንም የሚገባው ሆኖ ሳይሆን እግዚአብሔር በነጻ የሚሰጠን በነጻ እንደተቀበልነው ደግሞ ለማኅበሩ አገልግሎት ለሁሉ ጥቅም በሚውልበት አግባብ በነጻ በፍቅር የሚበረከት ነው፣ በሰብአዊ አነጋገር እግዚአብሔር ይህን ጸጋ ለአንድ ሰው ሲሰጠው ለግል ጥቅሙ ሳይሆን ለማኅበሩ አገልግሎት ነው እንላለን፣ ዛሬ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ብዙ የአካል ጉዳተኞች የሆኑ ሕጻናት ተቀብየ አነጋገርኩኝ፣ እነኚህን ሕጻናት የሚንከባከብ አንድ ማኅበር አለ፣ የማኅበሩ ማንነት በማኅበሩ የሚያገልግሎ ሰዎች በተለይ እንዲህ ዓይነት ችግር ያልቸውን ሕጻናት ለመንከባከብ የሚረዳቸው ስጦታ ወይም ካሪዝማ እንዳላቸው ተገነዘብኩ፣ ካሪዝማ ወይም ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ማለት ይህ ነው፣
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን አንድ አስፈላጊ ነገር አለ፣ አንድ ሰው ካሪዝማ ወይንም ልዩ ስጦታ እንዳለው እና ምን መሆኑን ሊያውቅ አይችልም፣ ሆኖም በዕለታዊ ሕይወታችን ብዙ ሰዎች እኔ የዚህ ዓይነት ስጦታ አለኝ፤ መዘመር እችላለሁ፣ እነኚህ ዓይነት ሰዎችን ግን ብርታት አንግቦ አረ ዝም በል እባክህ ስትዘምር ደስ አትልም ማለት ይሻል ምክንያቱም አንድም ሰው እኔ ይህ ካሪዝማ አለኝ ለማለት አይችልምና፣ እግዚአብሔር አባታችን የሚሰጠን ልዩ ጸጋ ወይንም ካሪዝም በማኅበረ ክርስትያን ውስጥ ሆነው ናቸው የሚለምልሙትና የሚያብቡት፣ እንዲሁም ለሁሉም ልጆቹ የፍቅር ምልክት መሆናቸውን ለማጤንና ለማወቅ የሚቻለውም በዚሁ ማኅበር ውስጥ ሆኖ ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዳችን እግዚአብሔር ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ወንድሞቼ በማኅበረ ክርስትያንዋ ሊያውቁትና ሊያበረታቱት የሚቻል በኔ ላይ አንድ ካሪዝም አወረደ ወይ ብለን ገዛራሳችንን መጠየቅ ያስፈልጋል፣ በዚህ ካሪዝም እንዴት እመላለሳለሁ በልግስና ለሁሉም አገልግላለሁ ወይንስ ረስቼው ዝም ብያለሁ? ወይንም ደግሞ አያድርገውና በዕብሪት ተነፍቼ ሁሌ ስለሌሎች ሳጕረምረም ማኅበሩን ደስ እንዳለኝ አዋከበዋልሁ? እነኚህን ጥያቄዎች ደጋግመን መጠየቅ አለብን፣ ማለትም ካሪዝማ ወይንም ልዩ ስጦታ ያለኝ እንደሆነና በቤተ የታወቀ መሆኑን ማወቅ እንዲሁም በዚሁ ስጦታ ደስተኛ መሆኔ ወይንም ለሌሎች በተሰጠው ካሪዝማ የምቀና ከሆነ በደምብ ማስተዋል ያስፈልጋል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ካሪዝማ እግዚአብሔር ብቻ ሊያድለው የሚቻል ልዩ ስጦታ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፧ ከሁሉ በላይ ደስ የሚያሰኘው ግን እግዚአብሔር ቤተ ክርስትያኑን በተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሆኑ ካሪዝማዎች ያበለጸጋት መሆኑን ማወቅ ነው፣ ይህ ስጦታ የመለያየትና የመከፋፈል መሣርያ መሆን የለበትም፣ እነኚህ ሁሉ ስጦታዎች እግዚአብሔር የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስትያኑ በውህደት በእምነትና በተስፋ እንደአንድ አካል እንድትዳብር በነጻ የሚያድላት ጸጋዎች ናቸው፣ እነኚህ የተለያዩ ስጦታዎች የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ገዛ ራሱ ደግሞ ውህደትን ይፈጥራል አንድ ያደርጋል፣ እነኚህ የተለያዩ ስጦታዎች በፊታችን ሲደቀኑ ልባችንን ከፍተን የእግዚአብሔር ምን ያህል ድንቅ ነው በማለት ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችንና በእርሱ መወደዳችን ምኑን ያህል ደስ ያሰኛል ነው ማለት ያለብን፣ እነኚህ ስጦታዎች የመለያየት የመቀናናት እና የመከፋፈል መሳርያ ከሆኑ ወዮላችን፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው በአንደኛው መልእክቱ ምዕራፍ 12 ላይ እንደሚያመለክተው ሁሉም ስጦታዎች በእግዚአብሔር ዓይን አስፈላጊዎች ናቸው በማኅበሩ የሁሉ ስጦታዎች አስፈላጊነት አለን አንድ ስጦታ በሙላት እተግባር ላይ የሚውለው ከወንድሞች ጋር ለጋራ በጎ ነገር የተካፈልነው እንደሆነ ነው፣ ይህችም ማኅበር ቤተ ክርስትያን ናት፣ ይህችም ቤተ ክርስትያን በእነዚሁ የተለያዩ ስጦታዎች በውህደት ስትሰራ ልትሳሳት አትችልም፣ ይህ በመል እልተ ባህርያዊው የእምነት ስሜት ኃይል የሚገለጥ ሲሆን በሕይወታችን ኢየሱስን እስከመከተል በወንጌል አጥልቆ ሊያስተምረን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ጸጋ ነው፣ ዛሬ ቤተክርስትያን የኢየሱስ ሕጻን ቅድስት ተረዛ በዓልን ታከብራለች፣ ይህች ቅድስት በ24 ዓመት ዕድሜዋ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፣ ቤተክርስትያንን እጅግ ትወድ ነበር ወደ ሚስዮን እንድትላክም ብርቱ ጉጕት ነበራት ሁሉንም ካርዝማዎች ትፈልግ ነበር፣ እግዚአብሔር እንዲያበራላት ለመጸለይ ሄደች እዛም ልዩ ስጦታዋ ፍቅር መሆኑን አወቀች “በቤተ ክርስትያን ልብ እኔ ፍቅር እሆናለሁ” የሚል ቆንጆ ሓረግም ጻፈች፣ ይህን ስጦታ ማለትም ወዶ አፍቅሮ የመቻል ስጦታ ሁላችን አለን፣ በዛሬው ዕለት የኢየሱስ ሕጻን ቅድስት ተረዛን ቤተ ክርስትያንን እጅግ የማፍቀር ስጦታችንን አበልጽጋ እናታችን የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስትያንን እንደልጆችዋ እጅግ እንድናፈቅራት እንድታስችለን እንለምናት፣







All the contents on this site are copyrighted ©.