2014-10-01 16:12:24

አገረ ቫቲካን፦ ስለ መካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚወያይ ጉባኤ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2 ቀን እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በግብጽ በእስራኤል በኢየሩሳሌልም በፍልስጥኤም በዮርዳኖስ በኢራቅ በኢራን በሊባኖስ በሶሪያ በቱርክ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታትና በጀነቭ በተባበሩት መንግሥታት ማኅበራትና በኤውሮጳ ህብረት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢዎች የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎች አበይት ባለ ሥልጣን ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት እነርሱም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የቅድስት መንበር ተለዋጭ ምክትል ዋና ጸሓፊ፣ የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ፣ በቅርቡ በመካከለኛው ምስራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው የተመለሱት የአህዛብ አስፍሆተ ወንጌል የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፣ የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው ውይይት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ የአቢያተ ክርስቲያን አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ ጳጳሳዊ የውህድ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በሚያሳትፍ ስለ መካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊው ሁኔታ ርእስ ዙሪያ የሚወያይ ጉባኤ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጠራቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.