2014-10-01 16:14:41

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ የሰው ልጅ በጭነት መርከብ የሚላክ ምርት አይደለም


RealAudioMP3 በዓለማዊነት ትሥሥራዊ ደረጃ በመስፋፋት ላይ ያለው የግድ የለሽነት ባህል ባጠቃላይ ስለ ሰው ልጅና ስለ ዓለም በጠቅላላ ያለንን አመለካከት በመለወጥ ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑ በጀነቨ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና ክብር አስከባር ድርጅት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት በጠራው 65ኛ ክፍል አጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ የአፍሪቃ ሁኔታ መሠረት በማድረግ ስለ ስደተኞችና ተፈናቃዮች ወቅታዊ ሁኔታ በዳሰሰው ጉባኤ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ በሚከሰተው የስደተኞች በባህር የመስመጥ አደጋ ምክንያት የሜዲትራርኒያን ባህር የማይደረስ የማይለቀስበት በጽሞና የተዋጠ የመቃብር ሥፍራ እንዲሆን ማድረጉ ገልጠው፣ በእውነቱ የእነዚህ ሰዎች የባህር ጉዞ እንደ እቃ በመርከብ ተጭኖ የሚላክ የንግድ ምርት ተመስለው እንዲታዩ ከማድረጉም አልፎ፣ እጅግ የሚያሳዝነው ስለ እነዚህ ስደተኞች ጉዳይ የሚመለከት ፖለቲካ እንደ እቃ እንጂ እንደ ሰው የማይመለከታቸው መሆኑ ነው። የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂው ሕይወቱን ለማዳን የሚጋፍጠው የስደተ ጉዞ በበለጠ ለካፋ አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ በማብራራት፣ ከተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ሕይወቱን ለማዳን ቤትና ንብረቱን አገሩን ጥሎ የሚሰደደው አለ ማስተናገድ፣ የሚሰደደው ለከፋ አደጋ መልሶ ማጋለጥ ነው። በመሆኑም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በተለይ ደግሞም መንግሥታት ሰውን ለስደት ለመፈናቀል አደጋ የሚያጋልጠው ችግር መፍትሄ በማፈላለግ እንዲረባበረብና የዓለም አቀፍ ስደተኞችና የተፈናቃዮች ሰብአዊ መብትና ክብር ውሳኔ ስደተኛውና ተፈናቃዩም በሚገባበት ክልል ሁሉ ተከብሮ አለ ቤትና ንብረት የቀረው የተሰደደው ሁሉ የተሟላ ጥበቃ ይደረግለትም ዘንድ አደራ ብለው፣ ውጥረት ጦርነት በውይይትና በመተባበር ተግባር እንዲወገድ የሁሉም ጥረት አስፈላጊ ነው። ይኸንን የሰላም መንገድ በሃብታምና በድኾች አገሮች መካከል ያለው ልዩነት በሚያጠብ ተግባር ሊደገፍ ይገባዋል፣ ይህ ድጋፍ ወደ ሰላም የሚመራ መንገድ እንደሚሆንም አያጠራጥርም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.