2014-10-01 16:01:58

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ትያትራዊ አዘኔታ አስወግዶ ስለ ሚሰቃዩት በእውነት መጸለይ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሁሌ ማለዳ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በመቀጠል በላቲን ሥርዓት የዕለቱን ምንባብ ከመጽሐፈ እዮብ ምዕ. 3፣ 1-3፣ 11-17፣ 20-13 እንዲሁም የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 9፣ 51-56 መሠረት በማድረግ፦ ትያትራዊ ሰቆቃነት ወይንም አስመሳይ አዘኔታ አስወግዶ ስለ ሚሰቃዩት በእውነት መጸለይ” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኮረ ስልጣናዊ አስተንትኖ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ኢዮብ የተወለደባትን ቀን ይረግማል፣ ጸሎቱም እንደ እርግማን ሆኖ ነው የሚገለጠው፣ ኢዮብ ሕይውቱን የተረገመች በማለት ይገልጣታል፣ እዮብ ቤተሰቡም ሳይቀር ሁሉን አጣ። ሁሉም ተወሰደበት፣ ጤንነቱ አካሉንም ሁሉ አጣ፣ በሚዘገንን ቁስልም ተሞላ፣ በዚህ ሁሉ ተመክሮ ምክንያትም ትእግስት ተሟጠጠች፣ እዮብ የሚለው ሁሉ ያስፈራል፣ ሆኖም ግን ካለ ምንም መደባበቅ ስላጋጠመው ሁሉ የሚገልጠው ሃሳብ ቅንና እውነተኛ ሰው መሆኑ ነው የሚያስተጋባው። ስትናገር በእውነት መናገር ነው። ኤርሚያስም የተወለደባትን ቀን የተረገመች ትሁን ሲል ይጸልያ፣ “ገዛ እራሳችንን እንጠይቀ እነዚህ ሰዎች የተወለዱባትን ቀን በመርገማቸው የእግዚአብሔርን ስም ያረክሳሉን? ኢየሱስ ኣባቴ ሆይ ለምን ተውከኝ ሲል ሰቆቃውን ሲገልጥ እናስታውስ፣ ታዲያ ኢየሱስ የአባቱን ስም ያረከሰ ይመስላችኋልን? አቢይ ምስጢርም እዚህ ላይ ነው። በዚህ በተጨባጩ ዓለም ብዙ ሰዎች የነበራቸው አጥተው ለስቃይና መከራ ተዳርገው ለብቻቸው በመቅረታቸውም ምክንያት ሰቆቃ ሲያሰሙ ለምን ይህ ሁሉ መከራ ያጋጥመኛል በማለት ሲያማርሩ የህልውና ጥያቄ ሲያቀርቡ እንሰማለን፣ በእግዚአብሔር ላይም ይነሳሉ፣ አዎ ይኽ ለገዛ እራሱ ጸሎት ነው። ልክ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ለምን ለብቻየ ተወከኝ ለሚለው ጸሎት ተመስሎው ነው። ስለዚህ ይኸንን ጸሎት ለመድገም አባባ ብለን የመጥራት የውሉድነት ክብር ተሰጥቶናል” የእዮብ ጸሎት ሌላ ዓይነት ጸሎት ሆኖ ለመቅረብ የማይቻል ነበር ጸሎቱ የሆነው ሁሉ ከዕለታዊ ሕይወትና ገጠመኝ ጋር የተቆራኘ ነው። እውነተኛው ጸሎት ከልበ የሚመነጭ ጸሎት መሆኑ የዕለቱ ምንባብ ይመሰክረዋል ብለው፦ “በዚህ ባለንበት ዘመን በአካባቢያችን አጠገባችን በእዮብ ሁኔታ የሚገኙ ብዙ ናቸው፣ እንደ እዮብ የታረሙ ግብረ መልካም ቅን ሆነው የሚያጋጥማቸው ስቃይ ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት ከባድ የሆነባቸው ሰዎች። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ለስደት ለመከራ የሚደረጉትን እናስብ፣ አለ ምንም ባዶአቸው በመቅረትም ለከፋ ስቃይ ይዳረጋሉ፣ እነዚህ ወንድሞቻችን ‘አዎ አግዚአብሔር ሆይ እምነቴን በአንተ አኖርኩኝ አሜንም አልኩኝ ታዲዮ ባንተ ማመኔ እርግማን ነውን? በማለት ይጠይቃሉ። ቤተ ክርስቲያን የሰዎችን ሰቃይ የገዛ እራሷ በማድረግ መስዋዕት አድርጋ ታቀርባለች፣ ሁሉ ነገር እያለን የምናጉረመርም ስንቶቻችን ነን። ለሚያጋጥመን ትንሽ ችግር እንደ ተራራ በመመልከትም ሰቆቃ እናሰማለ፣ ሰማዕት የሆን ይመስለናል፣ በትንሽ ስቃይ ምክንያት ስንቶቻችን ነን ጸሎት ያቋረጥን በቅዳሴ ከመሳተፍ የጎደልን፣ ታዲዮ ትልቅ ችግር ሲያጋጥመ ምን ልንሆን ነው? ቅድስት ተረዛ ባጋጠማት ጨለማ ወደፊት ለማለት የሚያበቃት ጸጋ እግዚአብሔር እንዲሰጣት ጸልያች፣ ይኽ ደግሞ ትዕግስት ማለት ነው። የእኛ ዕለታዊ ሕይወት የተመለከትን እንደሆን በእውነቱ ችግር አለብን ለማለት የተገባን እይደለንም፣ ትያትራዊ ሰቆቃን እናሳያለ፣ ጌታችን ኢየሱስ በጌተ ሰማንየ በመስቀል እስከ መሰቀል አባቱን አባባ ሆይ ለምን ተውከኝ ሲል ይጸልያ፣ ብለው ጨለማ ሊያጋጥም ስለሚችል ከወዲሁ መዘጋጀት፣ ልክ ለእዮብ እንዳጋጠመው ላይሆንም ይችላል፣ ነገር ግን በሕይወታችን ጨለማ ሊያጋጥመን ይችላል፣ የቤተ ክርስቲያን ጸሎት የሚሰቃየው ኢየሱስ ነው፣ የተለያዩ ሰዎች የሚያጋጥማቸው ስቃይ የሚያጠቃልል ጸሎት መሆኑ ገልጠው የለገሱት ጥልቅ አስተንትኖ እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.