2014-09-24 15:59:55

ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ፦ ስደተኛና ወንጀለኛ ማለት አይደለም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የሰደተኞችን ተፈናቃዮች ቀን ምክንያት ያስተላለፉት መልእክት የስደተኛና ተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ካላቲፓራምቢል በጋራ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንባብ መብቃቱ የተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ አስታወቁ።
ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ፦ “የቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ስደተትና ስደተኛ ወቅታዊው ተጋርጦ ለመቅረፍ የሚቻለው በመተባበርና በማስተናገድ ባህል” መሆኑ የሚያብራራና በዚህ ብቻ ሳይታጠርም በአሁኑ ወቅት ስደተኛ በመጠራጠርና በፍርሃት የመመልከቱ አዝማሚያ በስፋት የሚታይ ነው። ይኽ አይነቱ አዝማሚያ ደግሞ ስደተኛና ወንጀለኛነትን በእኩል ለመመልከት ፈተና ይዳርጋል። ሆኖም ስደተኛ ወንጀል ጋር አጣምሮ መመልከቱና ስደተኛ ወጅለኛ ነው ብሎ ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ መስጠት በእውነቱ የሚያሳዝን ነው። ስደተኛ ማለት ወንጀለኛ ማለት አይደለም፣ ቅዱስ አባትችን እንዳሉትም ስደተኞች በቤተ ክርስትያን ልብ ልዩ የክብር ሥፍራ አላቸው’ ምክንያቱም ብዙ ነገር የሚያስፈልጋቸውና በቀላሉ ለተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተጋለጡ በመሆናቸው ነው። ድኻው ኢየሱስ ገዛ እራሱን የሚገልጥበት የህብረተሰብ ክፍል ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በመቀጠልም ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ካላቲፓራምቢል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ “ወቅታዊው ዓቢይ ተጋርጦ የዚያ በተለያየ ሰብአዊ ችግር ምክንያት ተገፋፍቶ ገዛ እርሱን ለስደት ለመዳረግ የተገደደው የስደተኛው ሰብአዊ ችግር ተላምዶ የመኖር ተግባር ነው፣ ያንን ችግር በልማድ የመመልከት ፈተና የወቅቱ አቢይ ተጋርጦ ነው። ስለዚህ ይኽ ተላምዶ መኖር ሌላውን በቸልተኛነት መመልከቱና በግድ የለሽነት ለእኔ አይመለከተኝም የሚለው አስተሳስብና ተግባር ያስከትላል፣ ይኽ ደግሞ ክርስቲያን ከእየሱስ ስቃይና ቁስል ርቆ መኖር ከሚገፋፋው ፈተና ጋር የሚመሳሰል ተጋርጦ ነው። በመተባብበርና በመተሳሰብ ባህል አማካኝነት የመላ ሰው ልጅ አንድነት እንዲረጋገጥ ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት አሳስበዋል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዝጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.