2014-09-24 16:08:40

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጋና ብፁዓን ጳጳሳትን ተቀብለው አነጋግሩ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የካቶሊክ ጳጳሳት በያምስቱ ዓመት በቫቲካን ሓዋርይዊ ጉብኝት በማከናወን ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ትሥሥር፡ አንድነትና ውህደት ለመመስከር ብሎም ለማጽናት፡ ለቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን፡ አንድነታቸውን ለመመስከርና ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለመሳለና ስለ ቤተክርስትያናቸው ወቅታዊና አንገብጋቢ ርእሶች አስደግፈው በመወያየት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናዊ መሪ ቃል የሚቀበሉበት መንፈሳዊ ዑደት ምክንያት አገረ ቫቲካን የገቡትን የጋና ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጋና ብፁዓን ጳጳሳት ባስደመጡት ንግግር የኢቦላ ሰለባ የሆኑትን ይኽ ተላላፊ በሽታ በሚታይበት በአሁኑ ሰዓት ካህናት ደናግል በጤና ጥበቃ ግብረ ሠናይ ሞያ የተሰማሩት የሚሰጡት ድጋፍ በበሽታና በድኽነት ከተጠቃው ጎን በመሆን የወንጌል ፍቅር የሚመሰክሩትን ሁሉ አድንቀው በጋና የምትገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረት በቅንነትና በአቢይ ሐዋርያዊ ኃላፊነተ በማስተዳደር በዚያ ሙስናና ምግባረ ብልሽት ቅን ኅብረሰብ ወደ ፊት እንዳይል የሚያስፋፋው መሰናከያ እንዲወገድ የሚያግዝ ተግባር መስካሪ ሆነው እንዲገኙ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ግኡዛዊ ድኽነት በመንፈሳዊ ስቃይ ለሚሰቃየው ክርስቶስን በመምሰል ለመደገፍ የሚያነቃቃ ሁኔታ እንደሚሆን የገለጡት ቅዱስ አባታችን በጋና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ለተለያዩ ሃይማኖቶች ግኑኝነትና የክርስቲያኖች እንድነት እንዲረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት አብነት ሆና እንድትገኝም በማሳሰብ ይኽ በአፍሪቃ አስከፊ ስቃይና መከራ ያስከተለው የጎሳ ልዩነት ግጭትና ብሔርተኝነት አመጽ በጋና ያልታየ መሆኑ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ግምት በመስጠት የአንድነት መሪ ለአገልግሎት የሚል አስተሳሰብና ተግባር አንቀሳቓሽ ሆና ትገኝ ዘንድ እንዳሳሰቡ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስነታቸው በጋና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ዓለማውያን ምእመናን የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች በማመስገን አለ እነርሱ አስተዋጽኦና ሱታፌ አስፍሆተ ወንጌል በበለጠ ባልተስፋፋ ነበር ብለው፣ በመጨረሻም የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. የአፍሪቅ ቃለ መሃላ የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት አስታውሰው የጋና ብፁዓን ጳጳሳት ለዓለማውያን ምእመናን ሕንጸት በበለጠ እንዲተጉ ማሳሰባቸው አስታወቀ።
ይኽ በእንዲህ እንዳለ ከተካሄደው ግኑኝነት ፍጻሜ የጋና ርእሰ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጋብሬል ቻልረስ ፓልመር ቡክለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. እንደ አባት መላ የጋና ብፁዓን ጳጳሳት በመቀበል ከሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን በኋላ የፈለጋችሁት ልትጠይቁኝ ለማለት የምትፈልጉት ካለ በእኔ ላይ ቅሬታ ካላችሁ በእኔ ሐዋርያዊ አስተዳዳር ደስ የማይላችሁ ወይንም ቅር የሚላችሁ ጉዳይ ካለ ጠይቁኝ ሲሉ የተናገሩት ሃሳብ በእውነቱ ለእያንዳንዱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምንኛ ቅርብ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
ካህን ብፁዕ ጳጳስ የበጊቱ ጠረን ያለው ይሁን በማለት በመደጋገም የሚሰጡት ምዕዳን ብፁዓን ጳጳሳት በማስታወስ የበግ ጠረን ሲባል ምን ማለት ነው ሲሉ ላቀረቡላቸው ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ሲመልሱ፣ በቅድሚያ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኮን የምትቀባው የቅብአ ቅዱስ ሽታ በመቀጠልም በእረኝነት የሚመራቸው የበጎቹ ሽታ ያለው ሦስተኛው ሽታ ደግሞ የእግዚአብሔር ሽታ ነው። ስለዚህ አንድ ብፁዕ አቡን እነዚህ ሶስት ሽቶ የሚሸት መሆን አለበት ብለው በትህትና መኖር ይኽ ማለት ደግሞ እረኛ መሆን ማለት ነው። በዓለም እጅግ ትሁት ሥራ እረኝነት ነው። እረኛ መሆን ብጎችን መንከባከብ ሲደክሙ መደገፍ እንዳይደነግኙ በተኵላው እንዳይነጠቁ መንከባከብ መጠበቅ ካህን ጳጳሳ ር.ሊ.ጳ. ቢኮንም እረኛ የመሆን ባህርይ ጨርሶ መዘንጋት የለበትን ሁሌ በየትም ሥፍራ እረኛ ሆኖ መገኘት ማለት ነው በማለት እንደገለጡት ጠቅሰው፣ ጸሎት የሕይወት ማእከል መሆን እንዳለበት ፖለቲካና ኤኮኖሚ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ሌላውን የማግለል ለያይ ባህል አረጋውያንና ሕጻናትን በድኽነት የተጠቁትን የሚዘነጋው ባህል በፍቅር ባህል መዋጋት ያለው አንገብጋቢነት በስፋት በተካሄደው ግኑኝነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሪ ቃል መለገሳቸው ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.