2014-09-22 15:54:25

የር.ሊ.ጳ ሓዋርያዊ ጉብኝት በአልባንያ፤


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በአልባንያ ባደረጉት የአንድ ቀን ሓዋርያዊ ጕብኝት “ዛሬ እዚህ የመጣሁት ለሰጠችሁት ምስክርነት ላመሰግናችሁ ነው እንዲሁም በእናንተ ውስጥና በአከባቢአችሁ ያለውን ተስፋ ለማበራታት ነው የመጣሁት፣ ምልክታችሁ የሆነው ንስርን አትርሱ፣ ንስር ቤቱን አይረሳም ሆኖም ግን እጅግ ከፍ ብሎ ይበራል፣ እናንተም ከፍ ብላችሁ እንድትበሩ ይሁን፣ ልቦቻችሁ ለክርስቶስ ለእግዚአብሔር ለቃለ ወንጌል ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በእርሳችሁ ለመገናኘት ክፍት አድርጉት በዚህም ለመላው ኤውሮጳ ምስክር ትሆናላችሁ፣” ሲሉ በማዘር ተረዛ አደበባይ ለቅዳሴና ለጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ለተሰበሰቡት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አልባናውያን የጕብኝታቸው ዓላማ ገልጠዋል፣
ትናንትና እንደገለጽነው ቅዱስነታቸው ትናንትና ጥዋት በሮም ሰዓት አቆጣጠር ሰባት ሰዓት ተኵል ከሮም ዓለም አቀፍ የፊዩሚቺኖ አውሮፕላን ማረፍያ ሲነሱ የተለያዩ ባለሥልጣናት እንደሸኝዋቸው እንዲሁም በበረራ ላይ እያሉ ለኢጣልያ ፕረሲደንትና ለአባንያ ፕረሲደንት የመልካም ምኞት የምስጋናና የቡራኬ ተለግራም እንደላኩም አብሮዋቸው የተጓዙ የቅድስት መንበር ጋዜጠኞች አመለከቱ፣ በአይሮፕላኑ ሲጓዙም ምንም እንኳ አብዛኛውን ጊዜ በሚደረጉት ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉዞዎች ረዘም ያለ ጊዜ ስለሚገኝ ቅዱስነታቸው አብረዋቸው ከሚጓዙ ጋዜጠኞች ጋር እንደሚወያያኑ የተለያዩ ጥያቄዎችም የሚመልሱ ቢሆን፤ የዛሬውኑ ግን አጭር ጉዞ በመሆኑ የቅድስት መንበር የኅትመትና ጋዜጣ ክፍል እና የቫቲካን ሬድዮ ኃላፊ የሆኑ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዶ ጋዜጠኞችን በመወከል ቅዱስነታቸው በመካከላቸው መገኘታቸውን በማመስገንና እንኳን ደህና መጡ በማለት መግቢያ ካደረጉ በኋላ “በዛሬው ጉዞ ከ50 በላይ ጋዜጠኞች ከቅዱስነትዎ ጋር አብረን እንጓዛለን ነገር በዓለም ሙሉ የሚገኙ አስር አገሮችን እንወክላለን የኅትመት የዜና አገልግሎ የተለቪዥን የሬድዮ የስእል አገልግሎት ወዘተ አሉ፣ ከአልባንያ ስድስት ባልደረቦች አሉ ሶስት የተለያዩ የተለቪዥን አገልግሎ ሲሆኑ ጉዞውን በቀጥታ ይዘግባሉ፣ በተለይ እነኚሁ አልባናውያን በዚሁ ጉዞ ምን እንደሚሰማዎ ሊያውቁ ስለሚፈልጉ ዕድሉን ለእነርሱ በመስጠት መልስዎን እንጠባበቃለን” ሲሉ ቃላቸውን ካሰሙ በኋላ ቅዱስነታቸው እንደልማዳቸው እንደምን አደራችሁ መልካም የሥራ ቀንም ይሁንላቸው ምክንያቱም የምታደርጉት የዕረፍት አይደለምና፣ ለምታበረክቱቱ ሥራ አመስግናችዋለሁ ቢያንስ ር.ሊ.ጳ ምን እንደሚያደርጉ አብያተ ክርስትያን ምን እንደሚሠሩ በዛሬው ዕለት ደግሞ በአልባንያ ምን እንደሚከናወን ሰዎች እና መላው ዓለም እንዲያውቅ በምታበርክቱት እርዳታ አመስግናለሁ፣ ከኮርያ ሓዋርያዊ ጉዞ ስመልስ ስለአልባንያ አውስቼ እንዳልኩት ይህ አገር እጅግ የተሰቃየች አገር ስትሆን ለስቃይና ችግር ሳትበገር በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ተቻችሎ በሰላም ለመኖር የቻለች አገር ናት፣ ይህም ለዓለማችን ዋና ምልክት ነው፣ ውይይትና ሰላምን ስለመረጡ የአንድነት መንግሥት ለመፍጠር ችለዋል፣ ይህን ነው ለማለት የምፈልገው መልካም ሥራ በጸሎታችሁ አስብኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ” ሲሉ ስሜታቸውን ከገለጡ በኋላ አባ ሎምባርዲም በበኩላቸው ጋዜጠኞችን ወክለው እኛም እናመስግንዎታለን እንደወትሮው በታላቅ ደስታ እንሸኝዎታለን መል እክትዎን ለሁሉም እንዲዳረስም አገልግሎታችንን እንሰጣለን ሲሉ አመስግነዋል፣ ተነሥተው ቅዱስበታቸው በአልባንያ ዋና ከተማ ቲራና ማዘር ተረዛ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፍያ በደረሱ ጊዜ በአገሪቱ የሚገኙ እንደራሴያቸው ማለትም ኑንስዮ አፖቶሊኮና የፕሮቶኮል አላፊ ወደ አይሮፕላኑ በመውጣት ለቅዱስነታቸው ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ አብረው ከአይሮፕላኑ ሲወርዱ የአልባንያ ፕረሲደንት ኤዲ ራማ ተቀብለዋቸው በአየር ማረፍያ በሚገኘው የቭፕ እንግዳ መቀበያ ለጥቂት ደቂቃዎች ከተወያዩ በኋላ በመኪና ወደ ቤት መንግስት ተጉዘዋል፣ በቤተ መንግሥት የአገሩ ርእሰ ብሔር ቡጃር ኒሻኒና ሌሎች ባለሥልጣኖች የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ፈጸሙላቸው፣ ከአየር ማረፍያዊ እስከ ቤተ መንግሥት ስምንት ኪሎሜት የሚሆን ርቀት ሲኖር ጐዳናዎቹ ር.ሊ.ጳጳሳቱን ለመቀበል ሰላምታ ለማቅረብና ለማየት በተሰበሰበ ሕዝብ አጥለቅልቆ ነበር፣
በአቀባበል ሥርዓቱ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር የእንኳን ደህና ንግግር ካቀረቡ በኋላ ቅዱስነታቸውም ለሕዝባዊ ባለሥልጣናትና ዲፕሎማቶች እንዲሁም በቦታው ለተገኙ የሃይማኖት መሪዎች፤በዚችው በተከበረቸው ሕይወታቸውን ለአገር ነጻነት የሰው የጀግኖች አገር እንዲሁም በከባድ የስደት ጊዜ እምነታቸውን ለመመስከር ደማቸውን ያፈሰሱ የሰማዕታት አገር በሆነቸው የአልባንያ መሬት ከእናንተ ጋር መገኘት ታላቅ ደስታ ይሰጠኛል፣ የንስር ምድር በማለት የምትታወቀው አገራችሁን ለመጐበኘት ስላቀረበላችሁት እድሜ አመሰግናለሁ እንዲሁም ለዚሁ ታላቅ አቀባበል አመሰግናችኋላእሁ፣ በማለት ምስጋናና ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ባለነው ዘመን ዓለምን አናውጦ ያለው ሃይማኖትን እንደሽፋን በመጥቀም የሚካሄደውን ግብረሽብራ በማውገዝ “ማንኛው እግዚአብሔርን ተገን በማድረግ የዓመጽና የጥፋት ተል እኮዎች ለመፍጸም ማሰብ የለበትም” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው አልባንያን ምድረ ንስር በማለት የዛሬ 25 ዓመታት ከስደትና ጭቆና ወደ ነጻነት በምትሸጋገርበት የተሰጠውን ስም በመጠቀም አገሪቱ ጀግኖች አርበኞችና ሰማዕታት እንዳፈራችና የሰማዕትነታቸው ፍሬ የሆነም ነጻነትና ሰላም ብሎም በዘመናችን የማይቻል መስሎ የሚታየውን በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በውይይትና በሰላም አብሮ ሰላማዊና የበለጸገ መንግሥት ለመገንባት እንደሚቻል ማስተማራቸውን አመልክተው በግጭት ያሉ አገሮች በተለይ ደግሞ በሃይማኖት ምክንያት በውግያ የሚገኙ ወገኖች ሁሉ ከነዚሁ የአስላም ኦርቶዶክስና ካቶሊካውያን የሃያ አምስት አመታት ተመኵሮ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል፣
በመጨረሻም ስለተደረገላቸው አቀባበል ለሁላቸው ልባዊ ምስጋና አቅርበው በወርኃ ሚያዝያ 1993 ዓም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለአገሪቱ እንደተመኙላት እሳቸውም የመላውን የአልባንያ ሕዝብ ተስፋ በመልካም ምክር እናት በሆነች እመቤታችን ድንግል ማርያም በማማጠን እግዚአብሔር በአልባንያ ጸጋውና ቡራኬው እንዲያሰፍን በመለመን ንግግራቸውን ደምድመዋል፣
ከዚህ በመቀጠል ቅዱስነታቸው በማዘር ተረዛ አደባባይ በተዘጋጀው ሰፊ ቦታ ላይ መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ ብክፍት የጂፕ ማኪና ሲጓዙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ በጐዳናዎቹ ግራና ቀኝ እያወዛዘና መልካም ምኞቱን እየገለጠ ተቀበላቸው፣
በቅዳሴ የተነበበው ወንጌል ከሉቃስ 10 ሲሆን ጌታ ከ12 ሓዋርያት ባሻገር “ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው” በማለት አርድ እትም እንደሾመ የሚያመልክት ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ይህንን ቃል መነሻ በማድረግ ጌታ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው የእግዚአብሔርን ፍቅር ሊያማጣልን ሲሆን ይህንን ለሁሉ ለማዳረስ ደግሞ አርድ እትንና ሓዋርያትን እንደመረጠና ወደ ዓለም ሁሉ በመሄድ ሁሉንም ደቀ መዛሙርቱ እንዲያደግዋቸው ይልካቸዋል፣ በወንጌሉ እንደተመለከተውም የስብከተ ወንጌሉ አካሄድ ቀላልና ጥርት ያለ ነው፣ ሓዋርያት እገበቡት ቤት “ሰላም ለዚህ ቤት” በማለት ሰላምታ እንዲያቀርቡ የሚያዘው ይህ ሰላምታ ማንኛ ሰላምታ አይደለም ይህ ሰላም ለዚህ ቤት የሚለው ስጦታ ነው የሰላም ስጦታ፤ መሆኑን ገልጠው ቅዱስነታቸውም ለአልባንያ ሕዝብ ይህንን ሰላምታ እንደሚመኙላቸው ገልጠዋል፣
ውድ አልባናውያን ወንድሞቼና እኅቶቼ እኔም ዛሬ እዚህ ለትህትና ታላቅ የዚህ ምድር ልጅ የሆነች ብፅዕት እናት ተረዛ ዘካልኩታ ስም በተየመ አደባባይ በመካከላችሁ ስገኝ ያ ጌታ ያዘዘውን ልደግምላችሁ እወዳለሁ ሰላም በየቤቶቻችሁ ይሁን ሰላም በልቦቻችሁ ይሁን ሰላም ለአገራችሁ ይሁን! ሰላም ሲሉ የክርስቶስን ሰላምታ ለሁላቸው አቅርበዋል፣
ምንም እንኳ ባለፉት ዘመናት የአልባንያ በሮች ተዘግተውና ብርቱ ችግር ያሳለፉ ቢሆኑም ዛሬ ግን ሁሉ ክፍት ስለሆነ ወንጌል ለመስበክ እንዲተጉ አደራ ብለዋል፣ አገሪትዋ የምትሰየምበትን የንስር መሬት ምሳሌ በማድረግም እንደ ንስር ወንጌልን ለሁሉ ለማዳረስ እንዲበሩ ሆኖም ግን ልክ እንደ ንስር ደግሞ ቦታቸውን እንዳይረሱ ማለትም ንስር የትም ዞሮ ወደ ቦታው ስለሚመለስ ምስዮናውያን ሆነው ወደ ሁሉም ቢላኩም መሬታቸውን እንዳይረሱ በማሳሰብ እንደ ማዘር ተረዛ ያሉ ትላልቅ ሚስዮንውያንና በደማቸው ክርስቶስን የመሰከሩ ታላላቅ ሰማዕታት በማፍራታቸውም አመስግነዋል፣ እግዚአብሔር እንዲሰሙና እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ አሳስበው ቤተ ክርስትያን አልባንያን እንደማትረሳት በማረጋገጥ በሰማዕታት ደም የተገኙትን ነጻነት ፍትህና ሰላም በመጠበቅ ወደፊት እንዲራመዱ አደራ ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.