2014-09-19 16:09:32

Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ፦ ‘ጊዜ’ ርእስ ያደረገ ዓውደ ጥናት


RealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ያለመ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት የተነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከመስከረም 26 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ጊዜ በሚል ርእስ ሥር የሚወያይ ዓውደ ጥናት በኢጣሊያ ቦሎኛ ከተማ በከተማይቱ አልማ ማተር ስቱዲዮሩም መንበረ ጥበብ ጋር በመተባበ እንደሚያካሂድ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፋራንኮ ራቫዚና የአልማ ማተር ስቱዲዮሩም መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ኢቫኖ ዲዮኒጂ በጋራ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።
በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ “የዚህ ሊካሄድ የተወሰነው ዓውደ ጥናት ርእስ ‘ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቤት’ የሚል ነው። ይኽ ደግሞ በሁለተኛው መጽሓፈ ሳሙኤል ዳዊት የእግዚአብሔር ቤተ ለመገንባት ይሻል፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር አንተ አይደለኽም ቤተን የምትገነባው እኔ እንጂ’ የሚል እግዚአብሔር የሰጠው ቃል እናገኛለን፣ ስለዚህ ጊዜ ሲባል ቦታ የሚለውን በውስጥ የያዘ መሆኑ የሚያመለክት ሲሆን፣ በእብራይስጥ ቋንቋ ባይት በሚል ቃል የተገለጠ ሃሳብ ነው ስለዚህ ቤት ሥፍራ ጊዜን ቅርጽ የሚሰጥ ግኡዝ ነገር ነው። ቦታ የጊዜ ውጫዊ አካል መሆኑ ያመለክታል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ጊዜ በእኛ ውስጥ ነው” በማለት እንዲህ ባለ ሃሳብ አጠር በማድረግ ዓውደ ጥናቱ ጊዜ የእግዚአብሔር ቤት በሚል ርእስ እንዲካሄድ የተመረጠበት ምክንያት ሲያብራሩ ፕሮፈሰር ዲዮኒጂ በበኩላቸውም፦ “የተመረጠው ርእስ ለአማኝም ይሁን ለኢአማንያን አቢይ ተጋርጦ ነው። አንዱ ያለ እምነት ስለ ተባለው ሊያምን ይችላል፣ ስለዚህ በዚህ ርእስ ዙሪያ አማንያንና ኢአምንያን ማወያየት በርግጥ ለምን እንደታመነና ለምን እንዳልታመነ በተጠቀሰው ርእስ ዙሪያ መልስ ይሰጡበታል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.