2014-09-12 17:01:54

ጦርነት የሚቀሰቅሰው የተፈጥሮ ሃብት ሳይሆን ፖለቲካ ነው


RealAudioMP3 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ዓመታዊ ገምጋሚ ስነዱን ለማቅረብ በሮማ ባካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የተሳተፉት ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶ ከጉባኤው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ጦርነት የሚጐተጉተው የተፈጥሮ ሃብት ሳይሆን ፖለቲካ ነው” በማለት የተካሄደው ጉባኤ መሠረታዊ የሰው ልጅ ጥያቄ ተገቢ መልስ ለመጠት ብቃት ያለው የፖለቲካ ኤኮኖሚ እንጂ የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ መማስወገድ ኤኮኖሚን ለማሻሻል ተጋድሎ ማድረግ የሚለው የቁጠባ ሥልት ለብቻው መፍትሄ አይሆንም ብለዋል።
አለ ልማት ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ አይቻልም፣ ስለዚህ ልማት እንዴት ተደርጎ ማነቃቃት መደገፍና ማቀብ ይቻላልን? በርግጥ አሁን ዓለም በሚከተለው የኤኮኖሚ ሥልት አማካኝነት ፈጽሞ የሚቻል አይደለም፣ ስለዚህ የተፈጥሮ ጸጋ፣ ባህል በጠቅላላ የምርምርና የእድገት ግኝትና የሥነ ምርምር ችሎታ መለዋወጥ ያስፈልጋል። በመሆኑን ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ እድገትን ለማፋጠንና ተቻይ እንዲሆን ለማድረግ የተፈጥሮ ሃብት ጸጋ በሚል ግንዛቤ መገንዘቡና ጸጋ መሆኑ ስንረዳም በነጻ የተሰጠ መሆኑ እናስተውላለን ስለዚህ ተካፍሎ መኖር ለሚለው እሴት መሠረት ይሆናል ይኸንን ከተገነዝብን የተፈጥሮ ሃብት በኅብረተሰብና በአገሮች መካከል መለዋወጥና መደጋገፍ ለሚለው እሴት መሠረት እንደሚሆን አያጠራጥርም ብለዋል።
ዓለማዊነት ትሥሥር ለገንዘብ ሃብት ዝውውር አመች በመሆኑ በርግጥ ለእድገት ድጋፍ ሆነዋል፣ ነገር ግን ዓለማዊነት ትሥሥር እየተረጋገጠ ባለበት በአሁኑ ወቅት አሁንም በአገሮች መካከል በአንድ አገር ሕዝብ መካከል ውስጥ እኵልነት ተጓድሎ ይታያል፣ ይኽም ምግባረ ብልሽት ሙስና ዘመደ አዝማድ በሚል አሰራር እንዲሁም በመልካምና በጥሩ ሂደት ማለት በግብረ ገብና ሥነ መግባር የተካነ የማስተዳደር ብቃት መጓደል አንዱ አቢይ ምክንያት ነው። አንድ በቅርብ የማውቀው ደራሲ ለምን አሁንም በአፍሪቃ ድኽነትና አፍሪቃ አሁንም ድኻ። ለምን? በሚል መጽሓፊ መልስ ሲሰጥ፣ የተመረጠ ድኽነት ሲል መልስ ሰጥቶበታል። ምርጫ ነው። ምርጫ ነው ሲባል ምናልባት ያስገርም ይኾናል፣ ሆኖም ግን የተመረጥ ድኽነት ሲባል የአፍሪቃ መንግሥታት የሚከተሉት የኤኮኖሚ ፖለቲካ የድኽነት እድገት የሚደገፍ መሆኑ ነው የሚገልጠው፣ ስለዚህ የአፍሪቃ ድኽነት ከመንግሥታት ጋር የተቆራኘ ነው ብለዋል።
ባለ ሃብቶች አበይት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኢንዳስትሪዎች ከአንዳንድ አገሮች መግንሥታት ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስላላቸው ወዳጅ መንግሥት ባለበት አገር አለ ምንም ሕግና ሥርዓት የአገር ሃብት ይበዘብዛሉ፣ ያገኙትም ትርፋ ትርፍ ትርፍ ለማግኘት ላበቃቸው አገር ምንም ነገር ሳይተዉ ያገኙት የተትረፈረፈ ገቢ ወደ ገዛ አገራቸው ያዛውራሉ፣ ስለዚህ እነርሱ እንጂ ለተጠቀሙበት አገር አልጠቀሙም፣ መንግሥታት ብስለት ማሳየት ይኖርባቸዋል፣ አንድ ወዳጅ ባለ ሃብት ድርጅቱ ወይንም ኢንዳስትሪውን ባስገባበት አገር እንዴት ለድኽነት መስፋፋት ምክንያት ይሆናል? ስለዚህ ወዳጅ ብሎ መጥራቱም ያስቸግራል፣ የምትወደው አገር ትደግፈዋለህ እንጂ አትበዘብዘውም፣ የአንዲት አገር ለም መሬት መኻን አለ ማድረግ፣ የግብርናው ኤኮኖሚ አለ ማዳከም፣ የተፈጥሮ ሃብት ለሁሉም ኢድናስትሪዎች ባለ ሃብቶች ተጠቅሞ መጥቀም የሚለው አሰራር ሊተገብሩ ይገባቸዋል መጥቅም ለሕዝብ ማለት ነው ብለው ከዚሁ ጋር በማያያዝም የተፈጥሮ ሃብት ሳይሆን ፖለቲካ ነው ጦርነት የሚቀሰቅሰው፣ የተፈጥሮ ሃብት ለመበዝበዝ የሚል ፍላጎት ለግጭት መንስኤ ይሆናል። በአቢይ ሃይቆች ክልል ያለው ሁኔታ በኰንጎ ያለው ውጥረት እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል ብለው ሥነ ምግባር ግብረ ገብ የተካነ ኤኮኖሚና የኤኮኖሚ ፖለቲካ አስፈላጊ ነው። ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተፈጥሮ ሃብት የተፈጥሮ ነው ይኽም ጸጋ ነው ማለት ነው። ይኽ ግንዛቤው ሲኖር ብቻ ነው ተካፍሎና በመደጋገፍ ለመኖር የሚቻለው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.