2014-09-03 18:08:30

የር.ሊጳ. ፍራንሲስ ሥርዓተ ቅዳሴ እና ስብከት :


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናንትና ጥዋት በርካታ ውሉደ ክህነት እና ምእመናን በተገኙበት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ አሳርገዋል።
ቅድስነታቸው መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ባሰሙት ስብከት የክርስትና ማንነት የዓለም መንፈስ መላበስ ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መልበስ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
የአንድ ክርስትያን ሥልጣን ከመንፈስ ቅዱስ እንጂ ከሰው እውቀት ወይም ከየሥነ መለኮት ትምህርት እንዳማይገኝም አስታውቀዋል።ኢየሱስ ክርስቶስ በሰበከበት ግዜ ህዝቡ ይደነቅ ነበር ምክንያቱም ቃላቶቹ የመንፈስ ቅዱስ ኅይል ስለነበራቸው በማለት ቅድስነታቸው ሰብከዋል።መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር መሆኑ እና ዓለምን ከጥፋት ለማዳን ጨለማ አግዶ ብርሃን የሰጠ ለፍጥረት ሁሉ ከባርነት አውጥቶ አርነት የሰጠ በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በስብከታቸው ላይ አክለው አስታውቀዋል።
ስብከታቸው በማያያያዝም የኛ የክርስትና ማንነት እንዴት ይመስላል ብለን መጠየቅ ይጠበቅብናል ብለዋል።በመቀጠል ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ እኛ የምንናግረው ከሰው እውቀት ተነስተን እይደለም ያለውን ጠቅሰው እሱ ማለት ቅዱስ ጵውሎስ በላተራንንሰ ወይም ግረጎርያን ጳጳሳዊ ዩኒቨትስቲዎች አልተማረም ወይም ሰብአዊ እውቀት ስለ ኖረው አይደለም ብለው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከመንፈስ ቅዱስ የቀሰመው እንደሆነ አመልክተዋል።ታድያ በመንፈስ ቅዱስ የተሟላ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ አሳምሮ ሰብከዋልብለዋል።
በሰብአዊ አቅም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይገኝም በእግዚአብሔር እገዛ ምሕረት እና ፍቅር ግን ለመድረስ እንደሚቻል አመልክተዋል። እንድግዲህ እኛ ክርስትያኖች የመንፈስ ቅዱስ ነገር በሚገባ ካልገባን ምስክሮች ለመሆን ያዳግተናል ብለዋል ቅድስነታቸው ። የክርስትና ማንነት ለመረዳት የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ እንዲኖረን ይገባል ያሉት ቅድስነታቸው የተሎግያ ሙሉ እውቀት ቢኖረንም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሌለን ከንቱ ውእቱ መሆኑ መረዳት ያሳል ብለዋል። የክርስትና ኀይልም ሆነ ሥልጣን ከመንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣ ጠቅሰው መንፈስ ቅዱስ ያደራቸው ዕድለኞች ሥነ መለኮት ካጠኑ ምሁራን እንደሚልቁ በየሕይወታችን ተሞክሮ ያየነው ነው በማለትም አያያዘው ሰብከዋል። እግዚአብሔር አምላካችን መንፈስ ቅዱስ እንዲቸረን እንለምነው የእውነት ክርስትያኖች እንሁን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕጎች እና ፈሪሀ እግዚአብሔር ስለ ሚያስተምረን እናንብበው ለመማር ሳይሆን የክርስትትና እሴቶች ለማወቅ የክርስትያን ባህርይ ለመልበስ ሰላማዊ ሕይወት ለማሳለፍ ይረዳናል ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ፓጳሳት ፍራንሲስ ። በመጨረሳም በዚሁ ቅዳሴ ተሳታፊ ለሆኑ ውሉደ ክህነት እና ምእመናን ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው እና መልካም ቀን ተመኝተው ተሰናብተዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.