2014-08-29 16:25:10

ቤተ ክርስቲያን በቀውስ በተጠቁት ቤተሰብ ፊት ዘወትር ትንበረከክ


RealAudioMP3 በኢጣሊያ ቶሪኖ ክፍለ ሃገር በምትገኘው በላሞንተ ከተማ የወንድም ጃኮፓ የትብብር ማኅበር “ሰብአዊነትን ማቀብ ለቤተሰብ መልካምነት ነው” በሚል ርእስ ሥር ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት የፍትሕና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ ባሰሙት ንግግር እ.ኤ.አ. ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
በሮቨረቶ ቆሞስ በኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ አስተዳዳሪ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ኒኮሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በአሁኑ ወቅት ብዙዎች በፈጸሙት ክርስቲያናዊ ሚሥጢረ ተክሊል ተዳክመው ቃል ኪዳኑ ሲያፈርሱ ይታያል፣ እነዚህ የተፋቱት ቃል ኪዳን አፍርሰው የሚኖሩት በቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ተቀባይነትም ሆነ ሥፍራ እንደሌላቸው ሆነው ይሰማቸዋል፣ ከቤተ ክርስቲያንም ይርቃሉ፣ እንደ የቤተ ክርስቲያን አባላት ትርፍ እንደ ሆኑ ይሰማቸውል በብዙዎችም እንዲህ ባለ መልክ የሚታዩና የሚፈረድባቸውም ናቸው፣ በርግጥ ቅድስና የሁሉም ክርስቲያን ጥሪ ነው። መፍረድ ሳይሆን ማፍቀር ማራቅ ሳይሆን ማቅረብ የሚያግዝ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስቲያን የደከመው ልትተው ሳይሆን ልትደግፈውና አብራው እንድትጓዝ የተጠራችው በችግርናበቀውስ በሚገኘው ሰው ፊት ትንበረከክ ዘንድ የተጠራች ነች። ስለዚህ አንድ ሰው የገባውን ቃል ኪዳን በተለይ ደግሞ ቅዱስ ምሥጢር አፍርሷል ብሎ ለብቻው መተው ክርስቶሳዊ መንፈስ አይደለም፣ ብዙውን ጊዜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለሚሰቃዩትን በከተሞቻችን በህልውናም ጥጋ ጥግ ለሚገኙት ርቀው ለሚኖሩት ለተናቁት የእግዚአብሔር የዋህነት አሳቢነት ጠባቂነት ፍቅር መመስከር መጠራታችንና ቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያን ከገዛ እራሱ ወጥቶ ከወንድሙ ጋር ሊገናኝ እንዲወጣ የሚያቀርቡት ሥልጣናዊ ትምህርት መሠረት ያለው ክርስቶሳዊ አገልግሎት ነው ብለዋል።
ለተፋቱት ቃል ኪዳን ላፈረሱት ቅርብ መሆንና በዚሁ ዓይነት መንገድ በሚሰጡት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት በመፋታታቸው ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው በሰብአዊነታቸው የከሰሩ ሆነው ተስፋ ቆርጠው ይኖሩ የነበሩት ጋር በመገናኘት በእውነቱ ስቃይ ባለበት መውደቅ ባለበት የእግዚአብሔር እቅድና ዓላማ አለ። ስለዚህ በዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት መፋታትን ቃል ኪዳን ማፍረስን አመክንዮ ለመስጠት ሳይሆን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔርን አባባ ብለው የሚጠሩበት እምነትና መንፈስ እንዳያጡ ዳግም በሚገኙበት የሕይወት ሁነት ቤተ ክርስቲያን ቅርባቸው በመሆን ምንም’ኳ በስቃይ ቢገኙም በሕይወታቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲኖሩና እንዲያዜሙ መደገፍ ይኖርባቸዋል፣ በሚሰቃየው ፊት መንበርከክ ያስፈልጋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.