2014-08-27 18:48:09

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! እምነታችንን በምናሳድስበት ጊዜ ሁሌ ጸሎተ ሃይማኖት ስንደግም ቤተ ክርስትያን አንድና ቅድስት መሆንዋን እናረጋግጣለን፣ አንድ የሚያሰኛት በአንድነትና ሶስትነት ፍጹም የአንድነት ምሥጢር በሚገለጠው ቅድስት ሥላሴ ስለምትመነጭ ነው፣ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወት አግኝታ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተመሠረተችና በፍቅሩና በደህንነቱ ስለተሞላች ቅድስት ናት፣ ነገር ግን እኛ ሁላችን አባሎችዋ ስለሆንን ይህንም በየዕለቱ በምንኖረው ድካማናተቻንና ችግራችን ስለምንመለከተውና ኃጢአትኞችም ስለሆንን ቅድስትና በኃጢአተኞች የቆመች ናት፣ ስለዚህ ይህ የምንመሰክረው እምነት በየዕለቱ ይህንን አንድነትና ቅድስና በሕይወት እንድንኖረው ለንስሓና ለውጥ ይጠራናል፣ ምናልባት አንድ ያልሆንና ቅዱሳን ያልሆንን እንደሆነ ለኢየሱስ ለገባነው ቃል ታማኞች አልሆንም ማለት ነው፣ ነገር እርሱ ማለትም ኢየሱስ ብቻችን አይተወንም፤ ቤተ ክርስትያኑን አይተዋትም፣ እርሱ ከእኛ ጋር ይጓዛል ሁኔታችንም በደምብ ይረደዋል፣ ደካማነታችንና ኃጢአቶቻችንን ይረዳል ይምረናልም ይህ ግን እኛ ሁሌ ምሕረቱን የተቀበልን እንደሆነ ነው፣ እርሱ ዘወትር ከእኛ ጋር ነው! ኃጢአት አብዘተን እንዳንሠራና ቅዱሳን እንድንሆን አንድ እንድንሆን እየረዳን ይኖራል፣
    የመጀመርያው መጽናናት ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ብዙ ከመጸልዩ ይመነጫል፣ ይህ ጸሎት የመጨረሻ እራቱን ከሓዋርያት አብሮ ከበላ በኋላ አባቱን “አባ አንድ እንዲሆኑ እለምናሃለሁ” ያሳረገው ጸሎት ነው፣ ይህንን የአንድነት ጸሎት ያደረገውም ሁለመናውን ለእኛ መሥዋዕት ለማድረግ በሚቀራረብበት አስጨናቂ ጊዜ ለሕማማት በሚዘጋጅበት ወቅት ነበር፣ ይህ የወንጌል ክፍል ደጋግመን ማንበብና ማስተንተን ያለብን ክፍል ነው፣ የዮሓንስ ወንጌል 17፡11.21-23 ጥልቅ ይዘት ያለውና ልብን የሚቀሰቅስ ክፍል ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ሊሞት ጥቂት ግዝያት ቀርቶበት በነበረበት ወቅት ለገዛ ራሱ ሳይሆን ስለእኛ መጨነቁና መጸለዩን ማወቅ እንዴት የሚያጽናና ነው፣ ከአባቱ ጋር ባደረገው የጸሎት ውይይት ከእርሱ ጋር አንድ እንድንሆንና እርስ በእርሳችንም አንድ እንድንሆን ጸልየዋል፣ እየውላችሁ በእነዚህ ቃላት ኢየሱስ በእግዚአብሔር አብ ፊት ጠበቃችን ሆኖ ስለእኛ ያማልዳል፣ ይህንም ያደረገበት ምክንያት እኛም ከእርሱ ጋር ሙሉ የፍቅር አንድነት ኖሮን ከእርሱ ጋር በመንግሥቱ እንድንገባ አንድነታችንም መለዮአችንና መታወቂያችን ሆኖ ቅዱስ ጴጥሮስ በአንደኛ መል እክቱ 3፤15 ላይ እንደሚለውም ማኅበረ ክርስትያኖቻችን በውስጣችን ስላለው ተስፋ ማንኛው ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ ይህንን መልስ በተግባር ሊሰጡ እንዲችሉ ነው፣

“አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።” (ዮሓ 17፤21)፣ ቤተ ክርስትያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምራ ይህንን በኢየሱስ ልብ ታላቅ ቦታ ይዞ የሚገኝ ፍላጎት እተግባር ላይ ለማዋል እየታገለች ናት፣ በሓዋርያት ሥራ ያነበብን እንደሆነ የመጀመርያዋ ቤተ ክርስትያን ዋነኛ መለዮ “አንድ ልብና አንድ ነፍስ ብቻ” እንዳላቸው ሆነው ይኖሩ እንደነበር ነው፣ (የሓ ሥራ 4፤32) ሓዋርያው ጳውሎስም ያቆማቸውን ማኅበረ ክርስትያኖች “አንድ አካል” ብቻ መሆናቸውን እንዳይዘነጉ አደራ ይላቸው ነበር (1ቆሮ 12፤13)፣ ታሪክ የሚያስተምረን ግን ሌላ ነው የአንድነት አንጻር የሆኑ ብዙ ኃጢአቶች እንደተፈጸሙ ነው፣ ምናልባት በአብያተ ክርስትያን ያሉ ልዩነቶችን እናስብ ይሆናል ነገር ግን የቍምስና ኃጢአቶች ብለን ልንጠራቸው በምንችል በየቍምስናው በየማኅበረ ክርስትያኑ የሚፈጸሙ ኃጢአቶችን እናስብ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ አንዳንዴ የመከፋፈልና የውህደት ማእከል ሊሆኑ የተጠሩ ቍምስናዎቻችን የቅናት የመከፋፈል የመጣላት ቦታ ሆነው ይገኛሉ፣ ሕሜታ እንደወረርሽኝ በየቍምስናው ተሰራጭተዋል፣ ይህ መልካም ነገር አይደለም፣ ለምሳሌ አንድ ም እመን የአንድ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ሆኖ በሚመረጥበት ጊዜ ስንት ሓሜት አለ፣ ሌላዋ የትምህርተ ክርስቶስ ማኅበር ሊቀ መንበር ሆና በተመረጠችበት ጊዜም ሌላ ሓሜት ይነሳል፣ ነገር ግን ይህችን ቤተ ክርስትያን ለማለት አያስደፍርም፣ ይህ መደረግ የሌለበት ጉዳይ ስለሆነ እናስወግደው፣ ይህንን ላለማድረግ ጌታን ጸጋው እንዲሰጠን እንለምነው፣ እንዲህ ዓይነት ችግር የሚያጋጥመው ትኵረታችን በገዛ ራሳችን በማድረግ ግላዊ ምኞቶቻችንና አመለካከቶቻችንን ወደ ፊት ለማራመድና በከፍተኛ የመሪነት ቦታዎች ያደረግን እንደሆነና ሌሎችን ችሎታቸውንና መልካም ነገሮቻቸውን ትተን ጉድለቶቻቸውን በመፍረድ ነው፣ በዚህም አንድ የሚያደጉንን ነገሮች ትተን የሚከፋፍሉንን ነገሮች ላይ እናተኵራለን፣ ለምሳሌ ቀድሞ አገለግልበት በነበረ ሃገረ ስብከት ሰዎች ስለ አንዲት አዛውንት ጥሩ አስተያየት ሲሰጡ ሰማሁኝ እኝህ አዛውንት ሙሉ እድሜያቸውን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የዋሉ ነበር ስለዚህ እኝህን አዛውንት በደንብ ነበር የሚያውቋቸው እኝህ ሴት አድን ቀን እንኳን ወሬ ሲያወሩ ወይ ሲያሙ ታይተው አይታወቅም ሁሌ በፈገግታ ነው አንዲህ አይነት ሴት ነገም ቢሆን ማጽደቅ ይቻላል! ይህ ጥሩ ምሳሌ ነው የቤተክርስቲያንን ታሪክ ከተመለከትን በኛ ክርስቲያኖች ስንት መከፋፈል አለ አሁንም ቢሆን ተከፋፍለናል በታሪክም ቢሆን እኛ ክርስቲያኖች ለተለያየ የነገረ መለኮት(ቴኦሎጂ) አመለካከቶች እርስ በእርሳችን ተዋግተናለል እስቲ በዚህ 30 አመታት ውስጥ ያለውን እናስብ ይህ እውነት ክርስቲያናዊ እይደለም ሁላችንም ለክርስቲያናዊ አንድነት በሕብረት መስራት አለብን ሁላችንም እየሱስ ለጸለየበትና ለሚፈልገው ወደ እርሱ ሕብረት ወደ ሆነው መንገድ መጓዝ አለብን
    ይህንን ሁሉ በመመልከት እስቲ እራሳችንን ጠለቅ ያለ እውነተኛ የሕሊናን ምርመራ እናድርግ በአንድ የክርስቲያን ማሕበረሰብ መከፈፈሉ አቢ ሐጢአት ነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ያልሆነ ምልክት ነውና ና መከፋፈል የዲያቢሎስ ተግባር ነው ዲያቢሎስ ስራው መከፋፈል ነው በጓደኝነት ጸብን የሚፈጥር በሰዎች መሃል ሃሜትንና አሉባልታን በማውራት. በአንዲት የክርስቲያን ማህበር ሰብ በትምህርት ቤትም ይሁን በቤተክርስቲያን አንዲሁም በድርጅት መከፋፈል አቢ ሐጢአት ነው ምክንያቱም የዲያቢሎስ ስራ ነውና . እግዚአብሔር ግን ከኛ የሚፈልገው እርስ በእርሳችን በመከባበር እንድናድግ እንድንዋደድና ይቅር በመባባል እርሱን እንድንመስል ነው እርሱ ሕብረትና ፍቅር ነውና. እዚህ ላይ ነው የቤተክርስቲያን ቅድስና ያለው የክርስቶስን አምሳል በመገንዘብ በምህረቱና በጸጋው ሙላት ነው

ውድ ወገኖቼ እነዚህን የክርስቶስ መልእክቶች በልባችን እናትማቸው ስለ ሰላም የሚሰሩ ብጹአን ናቸው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና (ማቴ ም 5ቁ 9 ) በምንኖርበት ሕብረተሰብ ውስጥ በማወቅም ባለማወቅም በፈጠርነው ግጭትና ልዩነት ሁሉ ከልባችን ይቅርታን እንጠይቅ ምክንያቱም ይቅር በመባባል ብቻ ነው ወደ አንድነት የምንደርሰው. ለውጥ ምን ማለት ነው. ክርቶስን ከሃሜት ከአሉባልታ ከወሬ የምንርቅበትን ጸጋን ሲያበዛልንና እርስ በእርሳችን ስንዋደድ ነው ለዚህም እንለምነው. ይህ ጸጋ ነው ክርስቶስ የሚሰጠን ይህ ነው መለወጥ የልብ መለወጥ እስቲ በየእለቱ በሕብረተሰባችን ውስጥ ያለው ግንኙነት በበለጠ ያማረና ደስተኛ ግንኙነት ከክርስቶስና ከአባቱ ጋር እንዲሆን እንለምን እንጠይቅ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.