2014-08-16 10:03:55

ሐዋርያዊ ዑደት ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በደቡብ ኮርያ :


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በደቡብ ኮርያ ሐዋርያዊ ዑደት እያካሄዱ መሆናቸው ይታወቃል። ቅድስነታቸው ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ተነስተው 8.970 ኪሎሜትር በረው ርእሰ ከተማ ሰኡል ሲገቡ በደቡብ ኮርያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪሊ የሀገሪቱ ብፁዓን ካትዲናላት ጳጳሳት የመንግስት ከፍተኛ ባለስለጣናት የሲቪል ማህበረ ሰብ ተውካዮች ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከሰኡል ሀገራት አቀፍ አውርፕላን ማረፍያ በቀጥታ ወደ ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ ወኪል ቅድስት መንበር በደቡብ ኮርያ የተጓዙ ሲሆን እዚያ በግል መስሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል ኃላም በግል ለምሳ ማእድ መቅረባቸው እዚይሃው የሚገኙ የዜና ወኪሎቻችን አስታውቀዋል። ከአጭር ዕረፍት በኃላም ካረፉበት ቦታ 800 ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ብሉ ሃውሰ ቤተ መንግስት መጓዛቸው እና የሀገሪቱ መንግስት መሪ ፕረዚዳንት ፓርክ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ሙቅ እና መልካም አቀባበል እንዳደረጉላቸው ተመልክተዋል።ፕረሲዳንት ፓርክ በ2012 በተደረገው ህዝባዊ ምርጫ የተመረጡ ሆነው በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመርያ ሴት ወይዘሮ መሆናቸው ይታወሳል።
ይሁን ፖረዚዳንት ፓርክ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያደረጉ ሲሆን
ቅድስነትዎ በደቡ ኮርያ ሐዋርያዊ ዑደት ለማካሄድ በመምጣትዎ በስሜ እና በደቡብ ኮርያ ህዝብ ስም አመሰግንዎታለሁ የደቡብ ኮርያ ቆይታዎ መልካም ቆይታ እንዲሆን ከፍተኛ ተስፋ አለኝ ብ ለው ያሉት ፕረሲዳንት ፓርክ ደቡባዊ ኣኣን ሰሜናዊ ኮርያ ያለውን አለመጣጣም ጠቅሰው አለመጣጣሙ ቤተ ሰብን ያፈናቀለ በህዝብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያለው አሳዛኝ ጉዳይ መሆኑ አስገንዝበዋል። በማያዝም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እዚያው በሚቆዩበት ግዜ የሚያከናውንዋቸው ሐዋርያዊ ሙያዎች ገልጠዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ክብርት ፕረሲዳንት ፓርክ የተከበራችሁ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አምባሳደሮች ወንድሞቼ እና እኅቶቼ ለተደረገልኝ መልካም አቀባበል ከልብ አመስግናለሁ ካሉ በኃላ በደቡብ ኮርያ ሐዋርያዊ ዑደት ለማካሄድ መምጣቴ ጥልቅ ደስታ ይሰማኛል ። የማካሄደው ሐዋርያዊ ዑደት ዋነኛ ምክንቶች በደቡብ ኮርያ ደጆን ከተማ ላይ የሚካሄደው ስደተኛ የኤስያ ክፍለ ዓለም ሀገራት ስድሰተኛ የካቶሊካውያን ወጣቶች ዕለት ለመሳተፍ እዞች ሀገር ስለ ካቶሊካዊ እምነታቸው በሰማዕትነት ላለፉ 124 ዜጎች መዓርገ ብፅዕና ለመስጠት ብ አደቡብ ኮርያ እና ሰሜን ኮርያ መካከል ታሪካዊ አለመጣጣም እንዲወገድ ለመጸለይ ነው በማለት አብራርተዋል። ከዚህ በኃላ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ፕረሲዳንት ፓርክ ስጦታ ተለዋውጠዋል። ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ወደ ደቡብ ኮርያ የተጓዙ የስራ ባልደረቦቻችን እንደዘገቡት ቅድስነታቸው የብሉ ሀውስ ቤተ መንግስት ቆይታቸው አጠቃልለው ወደ ቤተ ረኪበ ጳጳሳት ደቡብ ኮርያ ተጉዘዋል ። የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት በ35 ጳጳሳት የቆመ እንደሆነ ይታወቃል።
እዚያው እንደደረሱ ብጹዓን ጳጳሳቱ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው እና የረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብጹዕ አቡነ ፒተር ካንግ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ማደረጋቸው የዜናው ወኪሎቹ አክለው አገንዝበዋል።ቅድስነትዎ በየኮርያ ጳጳሳት እና በክርስትያን ማሕበረ ሰብ ስም የእንኳን ደህና መጡ መልዕት ሳስተላልፍ የሚሰማኝ ደስታ የላቀ ነው ፡ የበገጋ ዕረፍትዎ ወደ ጐን በመተው ሙቀት ባለበት ግዜ በሀገራችን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ በመምረጥዎ በእጁ እናመሰግናለን እግዚአብሔር ይስጥልን ። እንኳን ደህና መጡ ።
ሐዋርያዊ ጉብኝትዎ የደቡብ ኮርያ ካቶሊካውያን ብቻ ሳይሆኑ የሀገሪቱ ህዝብ በሙሉ በደስታ እና በናፍቆት ሲጠባበቀው ቆተዋል ያሉ የደቡብ ኮርያ ረኪበ ጳጳሳት ዋና ጽሐፊ ብጹዕ አቡነ ፒተር ካንግ ንግግራቸው በማያያዝ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1984 እና 1989 በሀገራችን ሐዋርያዊ ዑደት አካሄደው ነበር ። የርስዎ ሶስተኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ነው ይህ የእግዚአብሔር ፈጣርያችን ፀጋ ነው ብለዋል ። ቅድስነትዎ መጥፎ ዕድል ሆኖ ደቡብን ሰሜንን ኮርያ ከተለያዩ እነሆ 66 ዓመት ደፍነዋል በ1950 በሁለቱ ወንድማሞች ኮርያ በተካሄደው ጦርነት የአንድ ሚልዮን ተኩል ህዝብ ሕይወት ቀጥፈዋል ፡ ሶስት ሚልዮን 600 ሺ ህዝብ መቁሰሉም የሚዘነጋ አይደለም። አሁንም ሁኔታው አስከፊ ነው እና ክርስዎ ጋ አብረን ስለ ሰለ ሰላም ለመጸለይ እንሻለን ደሴት ኮርያን ባርኩልን ብለዋል ብጹዕ አቡነ ፒተር ካንግ ። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍቭራንሲስ በበኩላቸው ለደቡብ ኮርያ ብፁዓን ጳጳሳት የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል።
ቅድስነታቸው ከብጹዕን ጳጳሳት ደቡብ ኮርያ ከተገናኙ በኃላ ወደ ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ መልእክተኛ ቅድስት መንበር ተጉዘው በግል ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው ከሸኙዋቸው ብፁዓን ካርዲናሎች ለእራት መቅረባቸው የዜና ወኪሎቻችን የላኩት ሪፖርት አስገንዝበዋል።
በየዜና ወኪሎቹ ዘገባ መሠረት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንሲስ ከርእሰ ከማና ሰኡል ወደ 137 ኪሎሜትር ርቃ ወደ ምትገኝ ደጆን የምትባል ከተማ ተጉዘዋል ደጆን አውሮፕላን ማረፍያ እንደ ደረሱ የከተማይቱ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ላዛሮ ሲክ ኢል እና የከተማይቱ የመንግስት ባለ ስልጣናት አቀባበል አድርጎውላቸውል። ቅድስነታቸው ከደጆን አውሮፕላን ማረፍያ ዎርልድ ካፕ ሳታድየም መጓዛቸው እና በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ሰብከዋል። ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተጠቃለለ 37 ኪሎሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ዓቢይ ዘርአ ክህነት በሆሊክፕተር መጓዛቸው እና የዘርአ ክህነቱ ዋና ሐላፊ እና ተማሪዎች መነኲስያት እና መነኮሳን አቀባበል እንደረጉላቸው ተገልጸዋል።
እዚያም ከኤስያ ክፍለ ዓለም ሀገራት ከተውጣጡ ወጣቶች ተወካዮች ጋር ለምሳ ለማእድ ቀርበዋል ። ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በደቡብ ኮርያ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል ከምሳ በኃላ ወደ ሶልሞ ገዳም ተጉዘው ገዳሙ ውስጥ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመዋል። በዚሁ ሶልሞ ተብሎ በሚጠራው ዓቢይ ገዳም ከየኤስያ ሀገራት ካቶሊካውያን ወጣቶች ጋር ተገናኝተዋል ። ወጣቶቹ መንፈሳዊ መዝሙር አስምተዋል ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በእንግልዝኛ ቋንቃ አባታችን በሰማይ የምትኖር ጸሎት ደግመዋል፡ ቅድስነታቸው ለወጣቶቹ አባታዊ ምክርም መለገሳቸው ተዘግበዋል ። ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር ወደ ደቡብ ኮርያ የተጓዙ የስራ ባልደሮቦቻችን እንደዘገቡት ቅድስነታቸው ከደጆን ከተማ ወደ ርእሰ ከተማ ሰኡል ተመልሰው ወደ ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ መልእተኛ ቅድስት መንበር ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው ለእራትም ቀርበዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.