2014-08-13 18:59:19

የር.ሊ.ጳ ሓዋርያዊ ጉብኝት በደቡብ ኮርያ (እ.አ.አ ከነሓሴ 13 ቀን 2014 እስከ ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም)


RealAudioMP3 ክቡራትና ክቡራን አድማጮቻችን ባለፉት ዝግጅቶቻችን እንደተገለጸው ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኮርያ ዋና ከተማ የመላው ኤስያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በደዦጝ ከተማ በምታካሄደው ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ዛሬ ዕለት ብሮም ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ከፊዩሚቺኖ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ እንደሚነሱና ነገ ጥዋት በኮርያ ሰዓት አቆጣጠር አሥር ሰዓት ተኵል በሰዖል የአውሮፕላን ጣቢያ እንደሚደርሱ ተመልክተዋል፣
ቅዱስነታቸው ባለፈው ሚያዝያ ወር 13 ቀን 2014 ዓም ባደረጉት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ “እፊታችን ነሓሴ ወር 15 ቀን ወጣቶችን ለማግኘት ወደ ኮርያ እሄዳለሁ” ብለው ሓዋርያዊ ጉዞውን ይፋ ካደረጉት ወቅት ጀምሮ በተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ መኖራቸው የሚታወስ ሆኖ ባሁኑ ጊዜ ሁሉም በታላቅ ጉጕት ይህንን ታሪካዊ ፍጻሜ ለማየት እየተጠባበቀ መሆኑ ከቦታው የሚደርሱ ዜናዎች ያመለክታሉ፣
ቅዱስነታቸው ከፊዩሚችኖ ዓለም አቀፍ የአይሮፕላን ጣቢያ የተነሱት ይህ ፕሮግራማችን ከመሰራጨቱ በፊት ሲሆን ከቅድስት መንበር ሲነሱ የነበረው ሁኔታ ይህን ይመስል ነበር፣
ቅዱስነታቸው ከሚኖሩበት የቅድስት ማርታ እንግዳ መቀበያ እስከ አየር ማረፍያ በመኪና ሊጓዙ በመወሰናቸው በሮም ሰዓት ከቀትር በኋላ ሶስት ሰዓት ላይ ከፐትርያን አደበባይ ቅዱስነታቸውን የሚሸኙ ባለሥልጣናትና ጋዜጠኞች በአውቶቡስ ሲነሱ ሰስት ሰዓት ተኵል ደግሞ ቅዱስነታቸውን የያዘች መኪና ከቅድስት ማርታ እንግዳ መቀበያ ከቫቲካን ከተማ ተነሳች፣
ቅዱስነታቸው በፊዩሚቺኖ የአይሮፕላን ጣቢያ ላይ በደረሱበት ጊዜ የኢጣልያ መንግሥት ተወካዮች በተከበሩ የአገሩ የሚኒስትሮች ምክርቤት ፕረሲደት ማተዮ ረንዚ ጋር ሆነው ሸኝዋቸዋል፣
ምንም እንኳ ከዚህ ሲሄዱ የፍዩሚቺኖ የአይሮፕላን ጣቢያ ቢጠቀሙ እፊታችን ሰኞ ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓም ላይ ሮም ሲመለሱ ግን በቻምፒኖ የአይሮፕላን ጣቢያ እንደሚያርፉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና ያመለክታል፣
ሓዋርያዊ ጉብኝቱን በሚያካሄዱ ባለሥልጣኖች በወጣው መርሓ ግብር መሠረት ቅዱስነታቸው ነገ ጥዋት በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር አሥር ሰዓት ተኩል ሰዖል የአይሮፕላን ጣብያ ላይ የተለያዩ ባለሥልጣኖች ከተቀበልዋቸው በኋላ ቀጥታ በከተማው በሚገኘው የሓዋርያዊ እንደራሴ ኑንስዮ አፖስቶሊኮ በሚገኘው ቤተ መቅደስ በግል መሥዋተ ቅዳሴ እኩለ ቀን ላይ እንደሚያሳርጉ ምሳ በልተው ጥቂት ዕረፍት እንደሚያደርጉ ተመልክትዋል፣
ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ከቀትር በኋላ ደግሞ የእንኳን ደህና መጡ ሥርዓት በብሉ ሃውስ በሚታወቀው የሰዖል ከተማ በሚገኘው ቹንጉሙ አደራሽ ይካሄዳል፣ ከሥር ዓቱ በኋላ ወዲያውኑ ቅዱስነታቸው የአገሩ ፕረሲደንትን ይጐበኛሉ፣ እንደገና በቹንጉሙ አደራሽ ተመልሰውም ከአገሩ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት ዲስኩር እንደሚያቀርቡና ከባለሥልጣናቱ ጋር እንደሚወያዩ ተመልክተዋል፣
ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የሚያደርጉትን ግኑኝነት ከፈጸሙ በኋላ ማምሻውን ከአገሪቱ ጳጳሳት ጋር በኮርያ ረኪበ ጳጳሳት መንበርና መሰብሰብያ አድራሽ ተገናኝተው ዲስኩር ያቀርባሉ፣
አርብ ዕለት ነሓሴ 15 ቀን 2014 ዓም ከጥዋቱ ዘጠኝ ሩብ ጉዳይ ከሰዖል በሄሊኮፕተር ወደ ደዦጝ ይጓዛሉ፣ አሥር ሰዓት ተኩል ደግሞ በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ የሚከበረውን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሠታ በዓል ለማክበር በከተማው በሚገኘው የዓለም ዋንጫ እስታድዩም መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በመሥዋዕተ ቅዳሴው ላይ ስብከት እንደሚያቀርቡና የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎትም በሜዳው ከሕዝቡ ጋር እንደሚያሳርጉ መርሓ ግብሩ ያመልክታል፣
በደዦጝ በሚገኘው ዓቢይ ዘር አ ክህነት ደግሞ ከወጣቶች ጋር ምሳ በልተው ከተዝናኑ በኋላ ልክ አራት ሰዓት ተኵል ከቀትር በኋላ በሄሊኮፕተር ወደ ሳልሞየ መካነ ንግደት ይጓዛሉ፣ በመካነ ንግደቱም ከኤስያ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው ዲስኩር አቅርበው ማምሻውን በሄሊኮፕተር ወደ ሰዖል ይጓዛሉ፣
ካቀረቡ በኋላ ይወያያሉ፣
ቅዳሜ ዕለት ነሓሴ 16 ቀን 2014 ዓም በጥዋቱ ስምንት ሰዓት ከአምሳ አምስት ደቂቃ የሰዮሶሙን ሰማዕታት መካነ ንግደትን ይጐበኛል፣ አሥር ሰዓት ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር አገልጋይ ፓውል ዩን ዚ ቹንግ እና 123 ጓደኞቹ በሰማዕትነት እምነታቸውን ስለመሠከሩ ሥርዓተ ብፅ ዕናቸውን ለመፈጸም መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ ከቀትር በኋላ ሶስት ሰዓት ተኵል ላይ በሄሊኮፕተር ወደ ክኮቶንኘ ይሄዳሉ፣ አራት ሰዓት ተኵል ላይ ደግሞ በክኮቶንኘ የሚገኘው በሃውስ ኦፍ ሆፕ በሚታወቀው የአካል ጉዳተኞች ማእከል ይጐበኛሉ፣ ቀጥለውም አምስት ሰዓት ከሩብ ላይ በክኮቶንኘ በሚገኘው በስኩል ኦፍ ላቭ የሚታወቀው በኮርያ የሚገኙ የደናግል ማኅበሮች ማሠልጠኛ ማእከል ይጐበኛሉ፣ በዕለቱ መጨረሻም ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ በክኮቶነኘ በሚገኘው የመንፈሳውነት ማእከል የም እመናን ተል እኮ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት የዕለቱን ተግባራቸው አጠቃለው ሰባት ሰዓት ላይ በሄሊኮፕተር ወደ ሰዖል ይጓዛሉ፣
እሁድ ዕለት ነሓሴ 17 ቀን 2014 ዓም በሄሊኮፕተር ወደ ሄሚ በመሄድ ከኤስያ ጳጳሳት ጋር በቦታው በሚገኘው የሄሚ መካነንግደት ተገናኝተው ምክራቸውን ከለገሱና ከጳጳሳቱ ከተወያዩ በኋላ በመካነ ንግደቱ ማድ ቤት ከጳጳሳቱ ጋር ምሳ ይበላሉ፣
ከቀትር በኋላ አራት ሰዓት ተኩል ላይ የኤስያ ወጣቶች ስድስተኛ ዓለም አቀፍ ቀን መደምደምያ ቅዳሴ በማስረግና ስብከት በማቅረብ ከፈጸሙ በኋል ሰባት ሰዓት አከባቢ በሄሊኮፕተር ወደ ሰዖል ይመለሳሉ፣
ሰኞ ዕለት ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓም በአሮጌው የመንበረ ሊቀ ጵጵስናው የጉባኤ አደራሽ የአገሩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ከተገናኙ በኋላ በምዮንግ ዶንግ ካተድራል ለአህጉሩ ሰላምና ዕርቅ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ስብከት ያቀርባሉ፣
ከእኩለ ቀን ከአርባ አምስት ደቂቃ ከኮርያ ሪፓብሊክ ሓዋርያዊ ጉብኝታውን ፈጽመውን የሚሰናበቱበት ሥርዓት በሰዖል የአይሮፕላን ጣቢያ ተካሂዶ እስከ መንበራቸው ጉዞ ይጀምራሉ፣ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ አምስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ በቻምፒኖ የአይሮፕላን ጣቢያ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.