2014-07-25 16:26:30

ር.ሊጳ. ፍራንሲስ መርያምን ተቀብለው አነጋገሩ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሱዳን ካርቱም ላይ እምነታቸው ከእስላም እምነት ወደ ክርስትና ለውጠዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው እና የካርቱም ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጡ ተበይኖባቸው የነበሩ ወይዘሮ መርያምን ቫቲካን ውስጥ ተቀብለው ከባለ ቤታቸው ጋር ተቀብለው እንዳነጋገርዋቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በዚሁ ጉዳይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ፓፓ ፍራንቸስኮ ወይዘሮ መርያም ለእምነታቸው ያሳዩት ጽናት አወድሰው እንዳመሰገንዋቸው አስታውቀዋል።ቤተ ክርስትያን በእምነታቸው ምክንያት ከሚሰቃዩ እና ከሚንገላቱ እንደምትተባበር እና እንደምትጸልይላቸው ፓፓ ፍራንሲስ መግለጣቸው እና ከወይዘሮ መርያም ባለ ቤታቸው እና ልጆቻቸው መገነናኘታቸው ቅድስነታቸው በተጨማሪ መግለጣቸው ቃል አቀባዩ ገልጠዋል።የጣልያን መንግስት የወይዘሮ መርያም ካርቱም ላይ የተካሄደው የፍርድ ሂደት በቅርብ መከታተሉ እና አዎንታዊ ዲፕሎማስያዊ ሚና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒስተሊ በዚሁ ትናትና ቫቲካን ውስጥ በፓፓ ፍራንሲስ እና በወይዘሮ መርየም መካከል የተካሄደው ግንኙነት ተገኝተው ነበር ።የጣልያን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወይዘሮ መርየምን ቤተ ሰብ ሞራላዊ እና ማቴርያላዊ ከፍተኛ ትብብር ማደረጉ ይታወቃል። ወይዘሮ መርየም አባታቸው ኢብራሂም የሚባሉ የእስላም ሃይማኖት የሚከተሉ ኢትዮጵያዊት እናታቸው የኦርቶዶክስ ተውሃዶ ቤተ ክርስትያን አማኝ ሲሆኑ ራሳቸው ደግሞ ካቶሊካዊት መሆናቸው የሚነገርላቸው መርየም አንድ ክርስድትያን በማግባታቸው ነበር የካርቱም ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጡ እና እንዲወገሩ የበየነባቸው ። የካርቱም ፍርድ ቤት እንዳሰራቸው እና የስምንት ወር እርጉዝ በመኖራቸው እስር ቤት ውስጥ ልጅ መስጠታቸው እና በሞት እንዲቀጡ እንደተበየነባቸው ብያኔው በዓለም አቀፍ ደረጃ መወገዙ የማይዘነጋ ነው ። በመጨረሻ ግን ምሕረት ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸው ይታወቃል።ይሁን እና ወይዘሮ መርያም የአካል ጉዳተኛ እና የደቡብ ሱዳን ዜጋ ባለ ቤታቸው ከሁለት ልጆቻቸው ከካርቱም ሮም አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጣልያን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ማተዮ ረንጺ አቀባበል አድርጎውላቸዋል። ወይዘሮ መርየም ከቤተ ሰቦቻቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ከምብረራቸው በፊት የጣልያን መንግስት እንግዶች መሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ሰጥተዋል። የዩናትድ ስቴትስ መንግስት ለወይዘሮ መርያም እና ባለቤታቸው ካርቱም ውስጥ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ሰብአዊ ተገን መስጠቱ የሚታወስ ነው ።ወይዘሮ መርያም ካርቱም ውስጥ ከባድ ችግር ገጥሞዋቸው መኖሩ የእስላም ሃይማኖት የማቀበሉ ከሆነ በሞት እንደሚቀመጡ ሲነገራቸው ሞት መምረጣቸው ጠቁመው ለድኅነታቸው ከፍተኛ ጥረት ላካሄዱ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ በማለት መግለጫ መስጠታቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.