2014-07-21 16:31:17

ስደተኞች


ስደተኞች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነበት በሚታይበት ወቅት ገና ሜዴተራንያን ባህርን በማቋረጥ ግማሹ ማር ኖስትሩም በተሰኘው የኢጣልያ መንግሥት የባህር እልቂትን ለመከላከል ያቆመው ግዝያዊ ግብረ ኃይል እርዳታ ጥቂቶቹ ደግሞ ለሕይወት ፈታኝና አዳጋች የሆነ የባህር ጉዞ በማድረግ በጣልያን ደሴቶችና ወደቦች የሚደርሱ በዚሁ ዕለታት እየጐረፉ ናቸው፣
ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 203 የሚሆኑ ስደተኞች አብዘኛዎቹ የናይደርያ ዜግነት ያላቸው በአንድ የሲንጋፖር ባንደራ የያዘች የነዳጅ መርከብ እርዳታ ፖዛሎ በሚባለው የራጉዛ አውራጃ ደርሰዋል፣ እነኚህ በታናሽ መርከብ ከሊብያ የተነሡ ስደተኞች ከሊብያ ተነሥተው 45 ማይል በሄዱ ጊዜ የሞት አደጋ ያንዣበበባቸው፣ በዚህ ጊዜ የሲናጋፖር የነዳጅ መርከብ ሊረድዋቸው የተረዋወጡት እስከ ጣልያን አገርም ያደርስዋቸው፣ ይህ በእንዲህ ሳለ 267 ስደተኞች የያዘች ሌላ ትንሽ መርከብም በጣልያኑ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እርዳታ በኤፐዶክለ ፖርት እንዲደርሱ ተደረገ፣ ለዛሬ ደግሞ ከ500 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በፓለርሞና በመሲና ከተሞች ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፣ በሲቺልያ ያሉ የስደተኛ መጠለያዎች ከአቅማቸው በላይ ቢሞሉም ገና ከላምፐዱሳ በአይሮፕላን እየተጓዙ ያሉ ስደቶች ቦታዎቹን እያጣበቡ መሆናቸውም ተገለጸ፣
ማረ ኖስትሩም ባህራችን የተሰኘው የፍጡነ ረድኤት የባህር ሠራተኞች እንደገለጹት በቅዳሜ ዕለት ብቻ አምስት የነፍስ አድን ሥራዎች እንዳካሄዱና 749 ሰዎች እንዳዳኑ ከእነዚም 100 ሴቶች 61 ሕጻናትና ያኔ የተወለደ አዲስ ሕጻን ይገኙባቸዋል፣ ነገር ግን ሁላቸው ጉዞውን በሰላም ፈጸሙት ማለት አይደለም በሊብያና በማልታ መካከል እርዳታ ከተደረገለት አንድ መርከብ ውስጥ ከነበሩ 18 እንደሞቱና ሬሳቸው ይዘው እንደገቡም በኃዘኔታ ገልጠዋል፣ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደሚገልጸው ደግሞ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 5200 የሚሆኑ ሰዎች በመዝገቦቻቸው ሲመዘገቡ ከአንድ መቶ በላይ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በጉዞው እንደሞቱ የባሰውኑ ደግሞ ብዙ ሰዎች የት እንደደረሱ የማይታወቅ እንዲያው እንደጠፉም ይመለከታል፣ የስደተኞች ጉዳይ ሲነሳ በተለይ ደግሞ ባለፈው ዓመት በላምፐዱሳ ያጋጠመ እልቂትና ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እቦታው ላይ በመድረስ በባህሩ ስለሞቱት ሁሉ ጸሎት አሳርገው ኅሊና ላለው ሁሉ የሚነካ ሰብአዊ መልእክት አስተላልፈው ሁላችን እነኚህን ጊዜና የሰው የካዳቸው ችግሮች ለመርዳት የተቻለንን ማድረግ እንዳለብን ባቀረቡት ጥሪ መሠረት አንድ በማልታ የሚኖር ቤተ ሰብ ያላቸውን ሁሉ ለዚህ ተል እኮ ለማዋል በተለይ ደግሞ በአከባቢው በሚያጋጥሙ የባህር አደጋዎች በቀጥታ ለመሥራት ማኦስ ሚግራንት ኦፍሾር አይድ እስተይሽን በሚል ስያሜ የጠሩት የባህር ፍጡነ ረድኤት እንደሚጀምሩ ከቦታው የደረሰ ዜና አመልክተዋል፣ እነኚሁ ኢጣልያዊት ባለሃብትና አሜሪካዊ ባለቤትዋ በግል ሊያበረክቱት ያቀዱትና ከአንድ ወር በኋላ በይፋ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ምግባር ሠናይ መነሻው ምን ይሆን ተብለው በተጠየቁበት ጊዜ ለቫቲካን ረድዮ ይህንን መልስ ሰጥተዋል፣
ባለፈው ዓመት ለዕረፍት በላምፐዱሳ በነበርንበት ወቅት እንዳጋጣሚ ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ በላምፐዱሳ ጉብኝት ያደርጉ ነበር፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ባለፈው ጥቅምት ወር ያጋጠመው ትራጀዲ የብዙ ሰዎች ሕይወት ሲያልቅ በተከታተልንበት ወቅት ያ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸኮስ ያቀረቡት ጥሪ እንደገና በአእምሮአችን እየተመላለሰ አንድ ነገር ማድረግ አለብን የሚል ሓሳብ አስጨነቀን፣ ባለን ጥቂት ዓቅም እኛም ሌሎችን መርዳት አለብን ብለን ባለን አቅም ይህንን ማኦስ ሚግራንት ኦፍሾር አይድ እስተይሽን ተቅዋም ሥራውን ይጀምራል፣ እንደ ተቅዋም መንግሥታዊ ያልሆነ ተቅዋም ነው፣ ለሰብአዊ ደህንነት በተለይ በባህር የሚጓዙና ረዳት የሌላቸው ሰዎችን ለመርዳት የቆመ የምግባረ ሠናይ ተቅዋም ነው፣ በባህር ውስጥ በተለይ በዓለም አቀፉ የባህር ክፍል ኢንተርናሾናል ዋተር በማለት በሚታወቀው ምንም እርዳታ በማታገኝበት የባህር ክፍል እርዳታ ለማቅረብ ነው ያቀድነው፣ የሚያስፈልገውን ዝግጅት ሁሉ አድርገናል፣ እስካሁን ያለውን ወጪ በግላችን ሸፍነነዋል የሚረዱን ለማግኘትም እየጣርን ነው፣ በባህር ውስጥ የነፍስ አድን ጃኬትም ይሁን ሌላ ስጦታዎች ከመሠረታዊው የውኃና የመግብ እስከ ልብስና ሌላ ልትረዱን ትችላላችሁ፣ ሲሉ የዚሁ በግል ተነሳሽነት ያቀዱት የምግባረ ሠናይ ዓላማ ገልጠዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.