2014-07-09 15:29:44

አባ ዲ ኖቶ፦ የወሲብ ዓመጽ ዳግም እንዳይከሰት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካብ ቅድስት ማርታ ሕንፃ በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የወሲብ ዓመጽ ወንጀል የተፈጸመባቸው ዜጎች በተሳተፉበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ቃል፦ “በእግዚአብሔር ፊትና በእናንተ ፊት በሕዝበ እግዚአብሔር ፊት በእናንተ ላይ በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የተፈጸመባችሁ የከፋው ጸረ ሰብአዊ ወንጀል የሆነው የወሲብ ዓመጽ ተግባር ምክንያት በጥልቅ ባዘነ ልብ በትህትና ምህረትን እጠይቃለሁ” ሲሉ የተናገሩት ቃል ያለው ጥልቅ ትርጉምና ከቅዳሴው በኋላም የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ከሆኑት ከስድስቱ ዜጎች ጋር ያካሄዱት የግል ግኑኝነት አስመልከት በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ እንዳይኖር የሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጓች ማኅበር መሥራች አባ ፎአቱናቶ ዲ ኖቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውሰው፣ የሮማ ጳጳስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዱካን በመከተል በሕፃናት ላይ አንዳንድ የውሉደ ክህነተ አባላት የፈጸሙት የወሲብ ዓመጽ በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን ያላት ቁርጥ ውሳኔና የምትከተለው ሕግ እጅግ ጽኑ መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው።
ቤተ ክርስቲያን እናት ነች ስለዚህ እናትነትዋን የሚያጨልም የእናትነት ባህርይዋን ለአደጋ የሚያጋልጥ ወንጀል ጸረ ሰባአዊ ወንጀል ነው ቅዱስ አባታችን ይኸንን ነው እያበከሩ ያሉት፣ በሕፃናት ላይ የሚፈጸው በደልና ግፍ ሕፃን ኢየሱስ የገዛ እራሱ በማድረግ የሚያፈሰው እንባ መሆኑ ቅዱስነታቸው በማስገንዘብ ቤተ ክርስቲያን አጽናኝ እንጂ የእምባና የሐዘን ምክንያት መሆን እንደማይገባት ብቻ ሳይሆን የገዛ እራሷ የምትከተለው የመሥራችዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ በሙላት መኖር ግዴታዋና ኃላፊነትዋም መሆኑ ነው የሚያስገነዝበው፣ ስለዚህ ቤተ ክስርቲያን ከሚበደለው ለተለያየ አመጽ ከሚጋለጠው በበለጠ ደግሞ በወሲብ ዓመጽ ከሚጠቁት ጎን መሆንዋ ነው የመሰከሩት፣ ለሁሉም የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ሉኡካን ብፁዓን ጳጳሳት እረኞች ሁኑ እረኞች ናችሁ ልትመሩት ለተሰጣችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሁኑ፣ ልኡካነ ወንጌል ናችሁ የበጉ ጠረን ይኑራችሁ በማለት የሚሰጡት ምዕዳንና ሥልጣናዊ ቃል የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ከሆኑት ጎን ሁኑ ከተናቁት ከተበደሉት ከድኾች ጋር ሁኑ ለታናናሾች ተንከባከቡ ጠበቃ ሁኑ ስለ እነርሱ ጸልዩ የሚል ነው። ለኅዳሴ ለለውጥ ለእርቅ የሚመራ ነው። ሆኖም ግን የዚህ ዓይነት ዘግናኝ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ዳግም እንዳይከሰት የውሉደ ክህነት ሕንጸት ጥብቅ መሆን እንደሚገባው የሚያስገነዝብም ነው ብለዋል።
ይኽ በእሳቸው የተመሠረተው ማኅበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊትም ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት መሪ ቃል በመታዘዝና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መንፈሳዊ ሓዋርያዊ ስልት ሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ሊከተሉትና ሊኖሩት ይገባል፣ እንደ ካህንም ለገዛ እራሴ የማሳስበው ቃል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.