2014-07-09 15:27:39

አባ ዞልነር፦ አቢይ ትርጉም ያለው ግኑኝነት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከጀርመን ከአየር ላንድ ከተባበሩት ግዛት ብርጣንያ የተወጣጡ በጠቅላላ ስድስት በአንዳንድ የውልደ ክህነት አባላት ለወሲብ ዓመጽ የተዳረጉት ስድስት ዜጎች ጋር በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ ያካሄዱት ግኑኝነት አቢይና ጥልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ በተካሄደው ግኑኝነት ከጀርመን ለመጡት ሁለት ለወሲብ ዓመጽ ለተዳረጉት ዜጎች ባስተርጓሚነት ኃላፊነት የተገኙት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ጳጳሳዊ የሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ተንከባካቢ ድርገት አባል አባ ሃንስ ዞልነር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ እነዚህ በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የወሲብ ዓመጽ ግፍ የተፈጸመባቸው ዜጎች ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስለ ደረሰባቸው አስከፊው በደል ሲገልጡና ቅዱስ አባታችን በጽሞናና በትልቅ ኃላፊነት እንዲሁም በጥልቅ መንፈሳዊነት ሲያዳምጡ ማየቱ ልብ የሚነካ ተመክሮ ነው ብለዋል።
ይኽ ዓይነቱ ግኑኝነት ተራ ምልክት ነው እየተባለ የሚሰነዘረው ትችት ከእውነት የራቀ ነው። ግኑኝነት ምልክት ነው ምልክትነቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ አጽም ባረፈበት ክልል የወሲብ ዓመጽ ከደረሰባቸው ዜጎች ጋር ተገናኝተው ሲወያዩ በእውነቱ የእርቅ የእምነት የተስፋ ምልክት ነው። ስለዚህ ተራ ሳይሆን ጥልቅ ትርጉም ያለው ምልከት ነው። እነዚህ ዜጎች የወሲብ ዓመጽ ጸያፍ በደል የተደረሰባቸው በሌሎች ሳይሆን በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት ነው። እንዲህ በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዚህ ዓይነት ጸያፍ ተግባርና ወንጀል ልክ እንደ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳሉት ጸረ ሰብአዊ ወንጀል በማለት ገልጠዉታል፣ በእውነቱ የተካሄደው ግኑኝነት በቲዮሎጊያ አመለካከት ቅድስ ምሥጢር ለማለት የሚቻል ነው። ማለትም የጋጣማቸው ተመክሮ የሚለውጥ የሚቀይር የለውጥና የኅዳሴ ምሥጢር ነው። እንዲህ የሚያስብለውም የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑት ዜጎች ከተካሄደው ግኑኝነት በኋላ ስለ እምነት ስለ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላላ ስለ ውሉደ ክህነት የነበራቸው በገዛ እራሳቸው ታሪክ ላይ የነበራቸው አሉታዊ አመለካከት የለወጠ በመሆኑ ነው የደረሰባቸው በደል ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ለመሰረዝ የሚቻል አይደለም ሆኖም ግን ሁኔታዎችን በተስፋ እንዲያዩ አድርጓቸዋል ብለዋል።
ጳጳሳዊ ለሕጻናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ድርገት ባለፈው እ.ኤ.አ. ሓምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ስብሰባ ማካሄዱና ቀጣይ ስብሰባውንም እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. ለማካሄድ ወስነዋል፣ ይኽ ድርገት መልከዓ ምድራዊ ወካይነት ቅርጽ ያለው ማለትም ከአፍሪቃ ከእስያ ከኦቻይና የተወጣጡ አባላት እንደሚኖሩትና ስለዚህ ድርገቱ በሚያቅፋቸው አባላት ዓለም አቀፋዊነት መልክ ለበስ ይሆናል። እነዚህ አባላት ይኽ ድርገት የሚጠቁማቸው ሲሆን ውሳኔው ግን የቅዱስ አባታችን ይሆናል ብለው አክለውም ድርገቱ የገዛ እራሱ የውስጥ ደንብ እንዲሁም ቢሮ እንደሚኖረውና በሰብአዊ መንፈሳዊ ባህላዊ ሕንጸት አማካኝነት የወሲብ ዓምጽ ቀድሞ ለመከላከል በሚል አገልግሎት የሚጠመድና በተለይ ደግሞ የውሉደ ክህነት ተማሪዎችና በጠቅላላ ውሉደ ክህነት ማነጽ በሚል ዓላማ ላይ የሚያተኵር ይሆናል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.