2014-07-07 15:27:36

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ምህረት የአዲስ ዓለም ትንቢት ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሞሊዘ ክፍለ ሃገር ያካሄዱት ሐውጾተ ኖልዎ በኢሰርኒያ ካቴድራል ፊት በሚገኘው አደባባይ ከከተማይቱ ነዋሪ ሕዝብ ከመስተዳድር አባላት ጋር ተገናኘው እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. የቸለስቲኑስ አምስተኛ ኢዮቤላዊ ዓመት በማለት አውጀው፦ ቅዱስ ቸለስቲኑስ አምስተኛ እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የእግዚአብሔር መሓሪነትና ይቅር ባይነቱን መስካሪ እንደነበር ገልጠው ዓለምን የሚያድሰው የእዚአብሔር ምሕረት መሆኑ ላይ ያተኮረ ንግግር በማስደመጥ መቀጠላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አመለከቱ።
እ.ኤ.አ. በ 1215 ዓ.ም. በኢዘርኒያ ከተማ የተወለዱት ፒየትሮ ዘ ሞሮኔ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ተሹመው ቸለስቲኑስ አምስተኛ የሚል ር.ሊ.ጳጳሳዊ መጠሪያ መርጠው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉ፣ እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ የእግዚአብሔር ምህረት መሐሪነት መንፈሳዊነት ላይ በማተኮር የዚያ የነበሩበት ሕብረተሰብ ድኽነት ስቃይ ልክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድኾች የተጨቆኑት የእስረኞች ስቃይና መከራ የገዛ እራሱ በማድረግ የኖረና ድኾችን ያፈቀረ መሆኑ ይኸንን መንፈሳዊነት በቃልና በሕይወት በመመስከር የኖሩ ምክር በመስጠት በመስበክ ሳይሆን በጊዜው የነበረው አስተሳሰብና አመለካከት በመቃወም፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር አሳቢነት በማስረከብ ለኅብረተሰብ መሠረታዊው ሃብት እርሱም የእግዚአብሔር መሐሪነት በቃልና በሕይወት የመሰክሩ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ሲገልጡ፦ የእግዚአብሔር ምኅረት፣ ሙሉ ሥርየተ ሐጢአት የአምልኮ ልማድ ሳይሆን ጥልቅ፣ ሸክምን የሚያቀል መንፈሳዊነት፣ እርሱም ልክ እንደ ቅብአ ቅዱስ ሰብአዊነትን የሚያረሰርስ ደጎችና ርህሩሆች እንድንሆን የሚያደርገን መንፈስ ነው። ስለዚህ የበለጠው ዓለም ትንቢት ነው። ምሕረት የተፈጥሮ ሃብትና የሥራ ሃብት ለሁሉም የሁሉም የሚሆንበት ማንም ሳይቸገር የሚኖርበት የሚያስፈልገውን ሁሉ የሚያገኝበት በእኩል የሚዳረስበት አንድም ተቸጋሪ የሌለበት የበለጠ ዓለም ማለት ነው። ምክንያቱን ተጨባጩ የወንድማማችነት ሕይወት የሚኖርበት መተሳሰብና ተካፍሎና ተቋድሶ የሚኖርበት ዓለም ማለት ነው” በሚል መሠረታዊ ሓሳብ ዙሪያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቸለስቲኑሳዊ ዓመት ኢዮቤል ትርጉም ምን እንደሚመስል አብራርተው ይኽ መንፈሳዊነት ሁሉም ሊከተለው የሚገባው መንገድ መሆኑና ብዙውን ጊዜ ይኽ መንገድ ችላ በማለት የምንኖር ሐጢአተኞች በመሆናችንም፣ በምህረትና ተከፋፍሎ ለመኖር የሚያግዙ ተግባሮች እንፈጽም ዘንድ ለእግዚአብሔር ምሕረት እራሳችንን እናወክፍ ዘንድ ሲያሳስቡ፦ “ፍቅር የሚያነጻ የህሊና ማኅበራዊ ግኑኝነት የሚያድስ ትርፍ ለማካበት ሳይሆን አንድ አዲስ ሰብአዊነት ሥራ ቤተሰብ ማእከል ላደረገ ኤኮኖሚ መረጋገጥ የሚያበቃ ኃይል ነው” ይኽ የእውነተኛው ፍቅር መንገድ ዓለም የሚያስተምረው አይደለም የሚታለም በህልም የሚኖር ማለት ሳይሆን ይኽ ኃይል፦ “በመለወጥና የምህረት ተግባር በመፈጸም የሚኖር ማለት ነው። ስለዚህ በቸለስቲኑሳዊ ዓመት ኢዮቤል ይኸንን መንፈሳዊነት በበለጠ ለመኖር የምንጸልይበት መልካም ተግባር ለመፈጸመ የምንተጋበት መሆን አለበት” ብለው ያስደተመጡት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.