2014-07-07 15:33:48

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሞሊዘ ከወጣቶችና በወህኒ ቤት ከሚገኙት ዜጎች ጋር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በካምፖባሶ ያካሄዱት የሐውጾተ ኖልዎ መርሃ ግብር መሰረት ከሰዓት በኋላ በኢሰርኒያ በካስተልፐትሮሳ በሚገኘው በእመ ወድንግለ ጽሙረ ቅዱስ ሥፍራ ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ጥልቀት ከሌለው ከገረፍ ገረፍ ዓይነት እርሱም ከጊዚያዊነት ከሚከተል ባህል ዓይነት ሕይወት በኢየሱስ አስተንፍሶ መሰረት እንዲቆጠብ የሚያሳስብ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ ገለጡ።
“መንገድ መምረጥ ሲባል ምን ማለት ነው? በቅድሚያ ቆሞ አለ መቅረት ማለት ነው። አንድ ወጣት ባለበት በመሄድ ቆሞ መቅረት የለበትም። መራመድ አለበት። ስለዚህ አንድን ነገር ግብ አድርጎ መጓዝ ማለት ነው። አንድ ሰው የተሳሳተ መንገድ ሊከተል ስለሚችል፣ ሊንቀሳቀስ ይችላል ነገር ግን ሳይራመድ ይቀራል፣ ምክንያቱም ዙሪያ ጥምጥም ዓይነት መንቀሳቀስ ሊሆን ስለሚችል ነው፣ ሕይወት ግን በዚሪያ ጥምጥም ለመራመድ የተፈጥፈረች አይደለችም። ለመራመድ የተፈጠረች ነች፣ ስለዚህ የእናንተ ወጣቶች አቢይ ተጋርጦ ደግሞ ይኽ ነው” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አክለው ቅዱስ አባታችን የካስተልፐትሮሶ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ጧት ከሠታተኞችና ከባለ ሃብቶች ጋር ተገናኝተው ያሰመጡት ምዕዳን ያስተጋባ ወጣቱ ትውልድ እጅግ እያጠቃው ያለው የሥራ አጥነት ችግር፣ እያስከተለው ያለው ጉዳት ማንኛውም ዓይነት ተስፋ የሚያጨልም መሆኑ ማእከል በማድረግ፦ “በከሆነና በካልሆነ የሚኖር ወጣት ማየት እንዴት ያሳዝናል፣ ሥራ የማያገኝ ከሆነ ለምን እማራለሁ የሚል፣ ለመማር እየፈለገ እድሉ አጥሮት የሚኖር፣ ተምሮ ሥራ ያጣ ባጠቃላይ በሥራ አጥነት የተጠቃው ወጣት፣ ሁላችን ይኸንን ተጋርጦ ለመቅረፍ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል፣ የሥራ ክብር የተነፈገው ወጣት ትውልድ ማየት ተላምደን ከመኖር አደጋ አደራ እንቆጠብ፣ ሥራ አጥነትን ተላምደን አንኑር አደራ” እንዳሉ አስታውቀዋል።
ቅዱስነታቸው ከወጣቶች ተሰናብተው በከተማይቱ ወደ ሚገኘው ውህኒ ቤት በመሄድ ከእስረኞች ጋር ተገናኝተው ወህኒ ቤት እስር ቤት ማለት ሳይሆን ኅያው ሥፍራ ስቃይ ተስፋ የሚኖርበት ሥፍራ መሆኑ ላይ ያተኮረ ንግግር ከማስደመጣቸው ቀደም በማድረግ የወህኒ ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ባርባራ ለንዚኒ ለቅዱስነታቸው የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ካስደመጡ በኋላ፦ ሁላችን በሕይወታችን ስህተት እንፈጽማለን፣ ሁላችንም በፈጸምነው ስህነት ተጸጽተን ዳግም ላለ መሳሳት ምሕረትን እንጠይቅ፣ ይኽንን ተግባር ብዙዎች በቤታቸው ሁነው ይፈጽሙታል እናንተ ደግሞ ይኸንን ቁርጥ ውሳኔ በወህኒ ቤት ሆናችሁ ትፍፈጽሙታላችሁ፣ ሁላችን ኃጢአተኞች ነን። ምኅረትን ለመጠየቅ ወደ ጌታ ስንሄድ እርሱ ይምረናልም ቀድሞ በምህረቱ የሚገኘው እርሱ ነው፣ በምህረቱ የማይደክም ጌታ ነው። እርሱ የሚው ከስህተት መንገድ ተመለስ ተለወጥ የምትከተለው የስህተት መንገድ አይበጅህም ነው። በመመለስና በመለወጥ መንገድ ይደግፈናል፣ ይኽ ደግሞ ዳግም በመታረም ተዋህዶ በሱታፌ ለመኖር እንድንችል የሚያደርገን ምሕረት ነው። ሁላችን የሚመለከት መንገድም ነው” እንዳሉ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.