2014-07-07 15:35:34

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የፍቅር ሥራ ለአስፍሆተ ወንጌል መሪ ጎዳና


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሞሊዘ ክፍለ ሃገር ሐውጾተ ኖልዎ ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በካምፖባሶ በሚገኘው ሮማኞሊ በተሰየመው ነበር የእግር ኳስ ሜዳ 80 ሺሕ ምእመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ለአስፍትሆተ ወንጌል መሪ ጎዳና የፍቅር ሥራ ወይንም የሚሠዋ ፍቅር አገልግሎት መሆኑ በስፋት የሚገልጥ ሥልጣናዊ ስብከት እንደለገሱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገልጠው፣ ጠቅለል ባለ መልኩ የቅዱስነታቸው ስብከት፣ ወቅታዊው የዓለም ማኅበረሰብ ሁኔታ የዳሰሰና ያለው ወቅታዊው ተጋርጦ ይኽም የሚታየው ድኽነት ለማሸነፍ የመደጋገፍ የመተሳሰብ የመረዳዳት ባህል ማስፋፋ ያለውት አስፈላጊነት የሚበክር መሆኑ ጠቅሰው፣ ብዙውን ጊዜ ቅዱስ አባታችን ቤተ ክርስቲያን የበጐቿን ጠረን ለይታ የምታውቅ መሆን እንደሚገባት በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ በማተኮር የሰጡት ምዕዳን፣ ቤተ ክርስቲያን እረኛ መሆንዋ የሚያረጋግጥ ሥልጣናዊ ትምህርት መሆኑ የካምፖባሶ ቦያኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጃንካርሎ ብረጋንቲኒ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ቀደም በማድረግ ባሰሙት ንግግር ገልጠው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት መንበረ ታቦት በስተ ጀርባ የተኖረ ቅዱስ ምስል በአንድ የሰኔጋል ተወላጅ ስደተኛ የተቀረጸ እርሱም በተለያየ ችግር በአደንዛዥ እጽዋት፣ በአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት ወይንም በስራ አጥነት ምክንያት ወደ ባዶነት ሕይወት ያዘነበለ ሰው የሚገልጥ ሆኖም ከችግሩ ለመላቀቅ እጆቹን ዘርግቶ እርዳታን የሚጠይቅ በቅድስት ድንግል ማርያም የተመራ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ድጋፍ ሲቀርብለት የሚያሳይ፣ ቅዱስ አባታችን የወቅቱ ሰው የሚሻው የሰብአዊነት ቅርበት አብነት ነዎት የሚል መሆኑ፣ እንዲህ ባለ መልኩ ትርጉምን እንዳብራሩ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ስብከት ማርያም ወደ ቅድስት ኤልዛቤጥ በመሄድ እንዳገለገለቻት በማስታወስ “ማርያም የሚሰዋ ፍቅር ወይም የግብረ ሠናይ የፍቅር አገልግሎት አርአያ ነች። ቤተ ክርስቲያን ይኽ አብነት የምትኖር የሁሉም ሰው ልጅ ችግር ስቃይ በመካፈል የፍቅር ሥራ በመሆን የሰው ልጅ አሻግሮ እንዲመለከትና ተስፋ እንዲያደርግ ትመራለች፣ በወንድሞች አማካኝነት እግዚአብሔርን በማገልገል የመተሳሰብ ባህል የምታስፋፋ በተለይ ደግሞ በዚህ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የሥራ አጥነት ችግር የቁጠባና የኤኮኖሚ መቃወስ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ላይ ያተኮረ መፍትሄ ወሳኝ መሆኑና ከዚህ ውጭ የሚደረገው ጥረት ሁሉ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ነው፣ ቀዳሚው የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ማእከልነት ነው። የሰው ልጅ ክብር ሲባል ያ በሰው ዘንድ የታተመው የእግዚአብሔር አርአያና ምስል ማለት ነው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ትርጉም ጌታን የሚያገለግል ሕዝበ እግዚአብሔር ማለት ነው። አለ መቀናናትና ምቀኝነት አለ መከፋፈልና ሓሜት ሁሉም እርስ በእርስ መደጋገፍ መተሳሰብ ይኑር፣ ሱታፌን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ከተለያዩ ፈተናዎች ሁሉ ጌታ ያድነን፣ ከተካዥ ሕይወት እንጠንቀቅ” ብለው በመጨረሻ ያስደመጡት ስብከት ሲያጠቃልሉ፦ “ደቀ መዛሙርት፣ እኛም የጌታ ተከታዮች ደቀ መዛሙርት ነን፣ ምንም’ኳ ደካሞች ኃጢአተኞች ብንሆንም ሁላችን የጌታ ደቀ መዛሙርት ነን። እምነት በደስታና በጽናት ሱታፌ ከእግዚአብሔር ጋርና ከወንድሞቻችን ጋር እግዚአብሔርን በማምለክ ለመኖር የተጠራን ነን። የሕይወት ፈተናና ዕለታዊ ችግር የምንወጣው እግዚአብሔርን በማምለክ ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።
ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁም፣ በካምፖባሶ ወደ ሚገኘው ካቴድራል በመሄድ በቅዱስ ቁርባን ፊት ጸሎትና አስተንትኖ ፈጽመው እዛው የተገኙት ህሙማንና አካለ ስንኩላን ጋር ተገናኝተው አባታዊ ፍቅራቸውን መስክረዋል። በተለይ ደግሞ ከአንድ በከባድ ህመም ከተጠቃው ፍራንቸስኮ ከተባለ ወጣት በመቀጠልም አንዲት በነቀርሳ በሽታ ከተጠቁት ወጣት መምህር ጋር ተገናኝተው ያቀረበችላቸው በአንገት የሚጠልቅ መስቀል ገጸ በረከት በማቅረብ ቅዱስ አባታችንን ሰላም ካለች በኋላ ቅዱስ አባታችን ወጣቷን እጆችዋን ይዘው መስቀሉን ባርከው መልሼ ላንቺ አስረክበዋለሁ የምጠይቅሽ ነገር ግን ጸሎት ነው። ስለዚህ ይኸንን መስቀል በመያዝ ዘውትር ስለ እኔ ጸልዪ በጸሎት እንተዋወስ ብለው ይኸንን ነው የምጠይቅሽና አደራ ቃል ግቢልኝ በጸሎት እንተሳሰብ ብለው በካቴድራሉ ያካሄዱት መንፈሳዊ ንግደት አጠናቀው የመላእክቶች ቤት ወደ ተባለው በክልሉ በሚገኘው ካሪታስ የተሰየመው የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማሕበር ቅርንጫፍ ከሚረዱት ጋር ምሳ ተቋድሰው አዲሱ የድኾች መርጃ ማእከል መመረቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጆሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.