2014-07-07 15:24:05

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ለሠራተኞች ሰብአዊ ክብር ዳግም ማጎናጸፍ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሞሊዘ ከፍለ ሃገር ከሠራተኞች ከባለ ሃብቶችና ጋር በካምፖባሶ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የጉባኤ አዳራሽ ተገናኝተው፣ የመንበረ ጥበቡ ዋና አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ጃንማሪያ ፓልሚየሪ ካስደመጡት የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ቀጥለው ሠራተኞችንና ባለ ሃብቶችን ከወከሉት ዜጎች የቀረበ ንግግር አዳምጠው፣ ትክክለኛው የተፈጥሮ ጸጋ አጠቃቀም የሥራና የቤተሰብ ክብር ላይ ያነጣጠረ ንግግር ማስደመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ ገለጡ።
እግዚአብሔር ከስሰጠ ተፈጥሮ ጋር ሊኖረን የሚገባው ግኑኝነት እርሱም የግብርና ሞያ ሲባል አለ ለውጥ በልማድ መኖርና ባለህበት መራመድ ወይንም መመላለስ ማለት ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር ውይይት ገንቢና ውጤታማና በመጻኢ ላይ ባተኮረው የፈጥራ ችሎታ አማካኝነት መገናኘት ማለት መሆኑና ስለዚህ ሰው ከመሬት ጋር የሚኖረው ግኑኝነት ለግል እርባና ሳይሆን ለሁሉም ፍሪያማነት ላይ ያነጣጠረ ግኑኝነት ሊኖረው እንደሚያስፈግ ገልጠው የሰው ልጅ ድካምና ትልቁ ኃጢአትም መሬት በውስጥዋ ያለው ሃብት በእኩልነት ትሰጠን ዘንድ ከእርሷ ጋር ከመገናኘትና ከመውያየት ይልቅ እርሷን ለመበዝበዝ ያቀና የምናካሄደው ተግባር መሆኑ እንዳብራሩ ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አስታወቁ።
“የሥራ ጉዳይ በተመለከተ ዘርፍ ሰንበት የዕረፍት ቀን ተራ የሥራ ቀን እየሆነ መጥተዋል፣ አዎ ይኽ አማኞን የሚመለከት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም የሚመለከት ሥነ ምግባራዊ ጉዳይ ነው። አንዳንድ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑት ልዩ የእገልግሎት መስጫ መዋቅሮች በስተቀረ እሁድ የእረፍት ቀን ነው ሲባል ቅድሚያ ኤኮኖሚ ሳይሆን ሰው ይሁን የሚል ነው። ስለዚህ ገባያዊ ግኑኝነት ሳይሆን ቤተሰብአዊ ወዳጅነታዊ ወንድማማችነታዊ ግኑኝነት ይኖር የሚል ነው። ለአማኞች ደግሞ ከእግዚአብሔርና ከማኅበረ ክርስቲያን ጋር ግኑኝነት የሚኖርበት ክርስቲያናዊ ቤተሰብ የሚመሰከርበት ዕለት ነው። ስለዚህ ሰንበት ቀን መሥራት እውነተኛ ነጻነት ማለት ነው? እስቲ ይኸንን ጥያቄ ለገዛ ራሳችንን እናቅርብ? እንዳሉ ላ ቨላ አስታውቀዋል።
በተካሄደው ግኑኝነት ንግግር ያስደመጡት ወጣት እናት ኤሊሳ የፊያት ፋብሪካ ሠራተኛ “የተለያዩ ኢንዳስትሪዎች የኤኮኖሚ አውታሮች ፋብሪካዎች ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ያስከተለው ችግር ለመቅረፍ የሚከተሉት እቀድ ቀላል ድካም ጥረት የማይጠቅይቅ አርቆ የማያይ ራእይ የሌለው መንገድ ነው። በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም ፋብሪካዎች ኢንዳስትሪዎች ትክክለኛና ቅነኛ ሥነ ምግባር የሚከተል ኤኮኖሚያዊ ውደራ በመከተል ቀዳሚ የፋብሪካና የኢንዳስትሪ አቢይ ሃብት የሆነውን ሠራተኛ ችላ እንዳይሉ እናት ሠራተኞች ወላጆች ሠራተኞች የቤተሰብ ሃላፊነታቸውን የሚያከብር የሥራ ፖለቲካ አስፈላጊ ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አክለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኤሊዛ ንግግር በማያያዝ፦ “ሥራ አጥ መሆን ማለት አለ መሠረታዊ አስፈላጊ ነገር መኖር ማለት ብቻ አይደለም፣ ምናልባት ምግብ እናገኝ ይሆናል፣ የከፋው ችግር ዕለታዊ እንጀራ ይዞ ወደ ቤት አለ መግባት ነው። አለ ዕለታዊ እንጀራ ቤት መግባት የከፋ ስቃይ ነው። ምክንያቱም ከሰብአዊ ክብር ጋር የተቆራኘ ኃላፊነትና ጥሪ ነውና። ሥራ ማግኘት መሥራት ይገባናል ሰብአዊ ክብራችንም ነውና፣ ሰብአዊ ክብራችን እንከላከል” እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.