2014-06-30 16:13:59

በእግዚአብሔር መተማመን ከፍርኃት ከሰንሰለትና ከምድራዊ ሥልጣን ነጻ ያወጣል፣


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ የተከበረውን የቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ክብረ በዓል በደብረ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ “እውነተኛ መጠጊያችን በእግዚአብሔር ያለን መተማመን ነው፣ ይህ መተማመን ፍርኃት ሰንሰለትኝና ምድራዊ ሥልጣንን ከእኛ ያርቃል፣” ሲሉ ስብከዋል፣ ዘወትር በዚሁ ክብረ በዓል እንደሚያደርጉትም ዘንድሮ ለተሰየሙት 24 አዳዲስ ካርዲናሎችም አክሚም ሰጥተዋል፣ ይህ የመልካም እረኛ ምልክት የሆነው ከበግ ጸጉር የሚሰራ አክሚም ነው፣ ከአዲሶቹ ካርዲናሎች መካከል ሶስት በሥርዓቱ ሊገኙ ስላልቻሉ በመንበሮቻቸው ይሰጣቸዋል፣ ቅዱስነታቸውን አዳዲስ ካርዲናሎችን “ከሥልጣን ራስን ከፍ ከማድረግና ከትዕቢት” እንዲጠበቁ አደራ ብለዋል፣
በዕለቱ ከተነበበው ቃለ እግዚአብሔር ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 12 የተወሰደ ሆኖ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ጴጥሮስን ከእስር ቤት ሰንሰለቱን ከእጆቹ ከእግሮቹ አውልቆ ነጻ እንዳወጣው የሚገልጥ ምእመናኑም ሌሊቱን ምሉ ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲጸልዩ እንዳደሩ የሚገልጥ ነበር፣ ቅዱስነታቸው ይህንን መነሻ በማድረግ “እግዚአብሔር ለጴጥሮስ እንዳደረገው ሁሉ እውነተኛ ነጻነት እስክናገኝ ድረስ ከማንኛው ፍርኃትና ሰንሰለት ነጻ ያወጣናል፣ እውነተኛ መጠጊያችን በእርሱ ያለን እምነት ሲሆን ይህች እምነት ከማንኛው ፍርኃትና ባርነት ነጻ ያወጣናል፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ምሳሌ በመከተል ከፍርኃትና ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮአችንን ተገን ከማድረግ መጠንቀቅ አለባችሁ” ለአዳዲስ ሊቃነ ጳጳሳትና ካርዲናላት አሳስበዋል፣
“ውድ ወንድሞቼ ጳጳሳት ፍርኃት ፍርኃት ይለናል? የሚያስፈራን ምንድር ነው? ፍርኃት ፍርኃት ሲለን የማን ጥገኝነት ተገን እንሻለን? ዋስትና ከሓዋርያዊ ግብረተልኮአችን ለማግኘት እንጥራለንን፧ ወይንም በዚሁ ዓለም ሥልጣን ይዘው ያሉ ዋስትና እንዲሰጡን እንሻለን? ወይንም እውቅና እንድናገኝና ስመ ጥር እንድንሆን በመጣር በት ዕቢት እንታለላን በዚህም ዋስትና የምናገኝ ይመስለን ይሆን? ዋስትነታችን በማን ስር እናስቀምጠዋለን? ሲሉ ከጠየቁ በኋላ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ መለስ ብለው “ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ በተያዘበት ሌሊት ባደረገው ክህደት ስለተማረ በገዛ ራሱ ችሎታ ምንም ማድረግ እንደማይችል ስለተረዳው በጌታ ምሕረት ይተማመናል ይህ መተማመን ከክሕደቱ እጅግ ያየለ መሆኑንም ያውቃል በዚህም ምክንያት ጌታ ጴጥሮስ ከእነዚህ ይበልጥ ትወደኛለህ ወይ ብሎ ሲጠይቀው ጌታ ሁሉን አንተ ታውቃለህ እንደምወድህም አንተ በደንብ ታውቃለህ ብሎ ይመልሳል፣ ስለዚህ እኛ ጳጳሳትም እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ በችሎታችን ሳሆን በእግዚአብሔር ባለን የማይነቃነቅና ከሰብአዊ ግምቶች ሁሉ በላይ በሆነ እምነት የተመሠረትን እንደሆነ ፍርኃት መጠራጠርና ስንፍና ይባረራሉ፣
“የሚገባን ሆኖ ሳይሆን እግዚብሔር በቸርነቱ በእኛ እረኞች በሆነን ላይ አለማቋረጥ የሚያጸናው መተማመን የእምነታችንና የሰላማችን ምንጭ ናቸው፣ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበቃናል፣ በማይረቡ ተጨማሪ በሆኑ ነገሮች አንቁም፣
“ጌታችን ዛሬም ለኔም ይሁን ለእናንተ እና ለሁላቸው እረኞች ተከተለኝ ይለናል፤ በማይረቡ ንግግሮችና ሓሜቶች ጊዜ አታጥፉ በማይረቡ ተጨማሪ ነገሮች ሳትቆሙ መሠረታዊ ወደሆነው ነገር በማትኰር ተከተለኝ ይለናል፣ ምንም እንኳ ችግር ቢበዛ ወንጌልን ለመስበቅ ተከተለኝ፤ በጥምቀትና በክህነት ለተቀበልከው የጸጋ ስጦታ የሚማማ ሕይወት እየኖርክ በመመስከር ተከተለኝ፣ ዕለት ተዕለት አብረህ ከምትኖራቸው ሰዎች ጋር በሥራም ይሁን በድካም በውይይትም ይሁን በጓደኝነት ስለ እኔ በመናገር ተከተለኝ፣ ለሁሉም ወንጌል በመስበክ በተለይ ደግሞ ለተረሱትና ለተገለሉት ሰዎች እንዲህ በማድረግህ ከማንኛው ፍርኃት ነጻ አውጥቶ በእግዚአብሔር መተማመን እንዲያምኑ የሚያደርጋቸው ቃለ ሕይወት አይጐድላቸውም፣ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
በዚሁ ክብረበዓል የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በርጠለሜዎስ አንደኛ ተወካይ በሆኑ በበርጋሞ ሜትሮፖሊታ ብፁዕ አቡነ ዮሓንስ የተመራ ቡድን ተሳትፈዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ዘወትር እንደሚያደርጉት በቅዳሜና እሁድ ሁለት አጫጭር መልእክቶች ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ከአሥራ አራት ሚልዮን በላይ ለሆኑ ደንበኞቻቸው “የእግዚአብሔር ጓደኞች መሆን ማለት አንድ ሕጻን ወደ ወላጆቻቸው እንደሚያደርገው በገርነት መጸለይ ነው፤” የቅዳሜው ሲሆን የትናንትናው ደግሞ “ቅዱሳን ሓዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በሮም ከተማና በመላው ዓለም የምትገኘው በጉዞ ያለችውን ቤተ ክርስትያን ይባርኩ” የሚል ነበር፥








All the contents on this site are copyrighted ©.