2014-06-30 16:40:31

ር.ሊጳ. ፍራንሲስ ከምእመናን ጋር ሰንበታዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እንደሚያደርጉት ሁሉ ትናንትና ሰንበት እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል ።
ቅድስነታቸው በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺ ከሚቆጠሩ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ በትናትና ዕለት ተከብሮ እና ተዘክሮ የዋለውን የቅዱስን ጰጥሮስ ወ ጳውሎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ትኩረት በመስጠት ቅዱሳኑ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምሶሶ መሆናቸው ጠቅሰው የክርስቶስ እምነት ቅዱሳኑን ወንድማማች ሰማዕታት እና አንድ አካል አድርጎዎቸዋል በማለት አስገንዝበዋል።ቅዱስ ጰጥሮስ እና ጳውሎስ በሰብአዊ አኳያ የተለያዩ ቢሆንም ሁለቱ በኢየሱስ ክርስቶስ መጠራታቸው ጠቁመው ጥሪውን ተቀብለው ሁለንትናቸው ሰጥተዋል ብለዋል።
ሐዋርያቱ በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለወጣቸው የሱ ታማን አርድእት መሆናቸውም በማያያዝ ገልጠዋል።ቅዱስ ጰጥሮስ በሕማማት ግዜ ኢየሰሱ ክርስቶስን መካዱ ሳውል ማለት ቅዱስ ጳውሎስም ክርስትያኖችን ማሳደዱ አውስተ በኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት ተቀይረዋል ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የመድህን ክርስቶስ ጓደኞሞች እና ሐዋርያት ሆኑ ሲሉ አመልክተዋል።ሁለቱ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምሰሶዎች ሰማዕታት እና ቅዱሳን የድህነታችን መንገድ ጠራጊዎች አመልካች እና መሀንዲሶች መሆናቸው ለምእመናን ገልጸዋል።ሐጥአን ብንሆን እና በጨለመ ሁኔታ ብንገኝም እግዚአብሔር ምሕረቱ ሰጥቶ እንደሚቀይረን ማወቅ እና መረዳት አለብን ብለዋል።መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር ለቅዱሳን እና ሰማዕታት ጰጥሮስ እና ጳውሎስ እንደቀየራቸው እና እንደማራቸው ሁሉ እኛንም ይምረናል ይቀይረናል እና እምነታቻን ጽኑ መሆን ይጠበቅበታል ቃል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ።የክርስትያን እና ቤተ ክርስትያን ጠላት የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ከተቀየረ እና ምሕረት ካገኘ በኃላ ህልውናው ሁሉ ለቤተ ክርስትያን መስጠቱ እና ላመነበት መስዋዕት መሆኑ አስገንዝበዋል።
የተወደዳችሁ ህዝበ ክርስትያን ልባችን ለመድህን ጳለም ከከፍትን ወልደ እግዚአብሔር ይለውጠናል ይምረናል ወደ ሱ ካልቀረብን እና ቃሉ ካልሰማን ሰምተን ገበራዊ ካለደረግን ግን ባለንበት የመቅረት ዕድላችን የበለጠ ይሆናል ብለው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቃል እግዚአብሔር ተቀብለን ሰምተን ተረድተን እና አምነን የመግስተ ሰማያት መንገድ እንጓዝ ዘንድ ቅድስት ድንግላማርያም ወላዲተ አምላክ ታማልድልን ዘንዳ እናለምናት ብለዋል ። ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኃላ ቅድስነታቸው ዒራቅ ላይ እየተካሄ ደ ያለውን ህውከት ግጭት እና ግድያ አስታውሰው በሁኔታው በእጅጉ ማዘናቸው ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ ብቸኛ የሰላም መንገድ ውይይት እና ዕርቀ ሰላም መሆኑ አስገንዝበዋል።
ከዒራቅ የሚደርሱ ዜናዎች ሀገሪቱ ብ አእሳት እየተለበለበች መሆንዋ ይህ አሳዛኝ ድርጊት በፍጥነት መገታት እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።የዒራቅ ብጹዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሀገራት አቀፍ ማሕበረ ሰብ የዒራቅ ጦርነት እንዲገታ ካደረጉት ጥሪ በመተባበር ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እጠይቃለሁ ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ።የሀገሪቱ ልዓላውነት እና አንድነት እንደታቀበ ሆኖ ጦርነቱ እና ይህን ተከትሎ በህዝብ ላይ እያስከተለው ያለው ሰቆቃ ስደት እንግልት እና ፍራቻ እንዲቆም አጽንኦት ሰጥተው ተማጽነዋል። ግጭት ሌላ ግጭት ይጠራል ህውከት ሌላ ህውከት ይጠራል እና የግጭቱ ተዋናያን ቆም ብለው እንድያስቡ እና ልዩነታቸው ለማስወገድ ለሰላማዊ ድርድር እንዲቀርቡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አቤት ብለዋል ።እንድሚታወሰው ዒራቅ ላይ በሀገሪቱ መንግስት እና ኢሲስ በተባለ የሱኒ ጂሀዳውያን ቡድን መካከል ከበድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። የዒራቅ ሰራዊት ቲክሪት በተባለች ከተማ ጥቃት እንደፈጸመ እና ኢሲስ ተብሎ የሚጠራው የሱኒ ጂሀዳዊ ቡድን ርእሰ ከተማ ባቅዳድ ለመያዝ እየተቃጣ እንደሆነ የመመልከተ ሲሆን የሩስያ መንግስት የዒራቅ መንግስት ለመርዳት የጦር መሳርያ ለዒራቅ መሸጥዋ እየተነገረ ነው ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን የዒራቅ ህውከት እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸው ከኒውዮርክ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.