2014-06-25 18:02:36

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣(25.6.14)


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ባለፈው ዕለተ ሮብ በጀመርነው ስለቤተ ክርስትያን የሚመለከት አዲስ የትምህርተ ክርስቶስ ዙር እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር እንዳደረገው ለቤተ ክርስትያን ለመቋቋም በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ ቡራኬ እንዲሆኑ እንደመረጠን ተመልክተናል፣ በኦርት እግዚአብሔር በአብርሃም ጀምሮ በታላቅ ት ዕግስትና አሳቢነት የብሉይ ኪዳን ሰዎችን እንዳዘጋጀ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነትም በእግዚአብሔር በሰው ልጆች መካከል አንድ ኅብረት ያቋቋማል (ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ብርሃነ አሕዛብ ቍ 1 ተመልከት)፣ በዛሬው ዕለት ለክርስትያኖች የዚሁ ማኅበር አባል መሆን ምን ያህል አስፈላጊነት እንዳለው እንመለከታለን፣
፩. እያንዳንዳችን እንደግለሰብ ወይንም በተናጠል የቆምን አይደለምን ባህርያችን የአንድ ማኅበር አባላት መሆን ነው፣ ይህ ለእኛ አባታችን ስም መሆን አለበት፣ ስማችን ክርስትያን ከሆነ የአባታችን ስም ደግሞ የዚህች ቤተ ክርስትያን አባል ነኝ መሆን አለበት፣ ይህ አባልነት እግዚብሔር ለሙሴ ሲገለጥ ስለስሙ የሰጠውን ትርጓሜ ስለሚገልጥ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፣ በዕጸ ጳጦስ ሙሴን ወደ እስራኤል ልጆች ሲልከው “የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።” (ዘጸ 3፡15) እንዳለው ሁሉ እኛም የዚሁ ማኅበር አባሎች ነን፣ በዚህም እግዚአብሔር ከአባቶች ጋር ጥብቅ ኪዳን እንዳለውና በኪዳኑም ዘወትር ታማኝ መሆኑ እንዲሁም በዚሁ የሚቀድመን ኪዳን እንድንገባ እየጠራን ነው፣
1. በዚህም የመጀመርያው አሳባችን ወደ የቀደሙ ወላጆቻችን ሲወስደን በቤተክርስትያን ስለተቀበሉን ከታላቅ ምስጋና ጋር ነው፣ በገዛ ራሱ ክርስትያን የሚሆን ማንም የለም፣ የምናምነው የምንጸልየው ጌታን የምናውቅበትና ቃሉን የምንሰማበት እንዲሁም ቅርባችን መሆኑን የምናውቅበትና በአባሎቻችን መኖሩን የምናውቀው እኛን ቀድመው የኖሩ ይህንን እምነት ስለኖሩትና ወደ እኛ ስላስተላለፉትና ስላስተማሩን ነው፣ ጠለቅ ብለን ያሰብንን እንደሆነ ስለክርስትናችን ስናስተነትን ስንት ፊቶች በዓይኖቻችን ይደቀናሉ፤ እነኚህ ፊቶች ሕጻናት ሳለን ለእኛ ጥምቀትን የጠየቁ የወላጆቻችን ወይንም ት እምርተ መስቀልን ለማድረግና የመጀመርያ ጸሎትን ያስተማሩን የአያቶቻችንና የቅድመ አያቶቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወይንም ደግሞ ለመጀመርያ ትምህርተ ክርስቶስ በስተማር የእምነት ይዞታዎችን በማስተማር እንደ ክርስትያን ለማደግ የረዳን የቆማሳችን የአንድ ካህን የአንዲት ድንግልና የሆነ ትምህርተ ክርስቶስ መምህር ፊቶች ሊሆኑ ይችላሉ፣ እየውላችሁ ቤተ ክርስትያን ማለት ይህ ነው፣ አንዲት ታላቅ ቤተሰብ ናት፣ በዚሁ ቤተሰብ እንደአባል የመቀበል እንደአማኝ የመኖር ችሎታ እና የክርስቶስ ተከታይ ለመሆን የመማር ዕድል እናገኛለን፣
2.ይህንን ጉዞ ሌሎች በሚያደርጉልን ብቻ ሳይሆን ከሳቸው ጋር መኖር አለብን፣ በቤተ ክርስትያን በገዛ ራስህ ተዋጣው የሚለው ዲኢዋይ ዱ ኢት ዮርሰልፍ የሚል ፈሊጥ የለም፣ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ስንት ጊዜ ነው ቤተ ክርስትያንን እኛ በሚል ቅጽል የገለጡት፣ አንዳንድ ጊዜ እኔ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ ስለቤተ ክርስትያን ግን ምንም አያገባኝም የሚሉ እንሰማለን፤ እንዲያው አንዳንዶቹ ከቤተ ክርስትያን ሱታፌ እና ከቤተ ክርስትያን አማላጅነት ውጭ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ቀጥተኛ የግል ግኑኝነት እንዳላቸው የሚገልጡም አሉ፣ እነኚህ አደገኛና ግጂ ፈተናዎች ናቸው፣ የማሆኑ መከፋፈሎች ናቸው፣ እርግጥ ነው አብሮ መጓዝ መስዋዕትነትን ይጠይቃል አንዳንዴም ሊሰለች ይችላል፣ ምናልባት አንድ ወንድም ወይንም አንዲት እህት ሊያስቸግሩን ወይንም ዕንቅፋት ሊሆኑን ይችላሉ፣ ነገር ግን ጌታ የደህንነት መልእክቱን ምስክር ለሆኑ ለሰው ልጆች ነው አደራ የሰጠው፣ እነኚህም በልዩ ልዩ ስጦታዎች የታደሉና እንደ ሰው ልጅ ደግሞ ደካማዎች የሆኑ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ናቸው፣ ስንገናኝም እነኚህ ነገሮች እየጐሉ ይታያሉ፣ የዚሁ ቤተ ክርስትያን አባል መሆን ማለትም ይህ ነው፣
ውዶቼ የቤተ ክርስትያን እናት በሆነችው በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት አለ ቤተክርስትያንና አባሎችዋ ብቻየ ልድን እችላለሁ ከሚለው ፈተና ይሰውረን ዘንድ ጌታን እንለምነው፣ በዚሁ አንጻር ወንድሞቻችንን ሳንወድ ጌታን ልንወደው አንችልም፤ ከቤተ ክርስትያን ጋር አንድ ካልሆንን ከጌታ ጋር አንድ ለመሆን አንችልም፣ እንዲህ ካልሆነና ጌታ ኢየሱስን ለመከተል ከሚፈልጉ ጋር አንድ ሕዝብና አንድ አካል ሆነን ካልተጓዝን ደግሞ በጎ ክርስትያኖች ለመሆን አንችልም፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን “እያንዳንዱ ተገቢ ሥራ ይዞ ለማየት ስንቱን እሻለሁ! ሥራ የሰው ልጅ መብት መሠረታዊ ነገር ነው” ሱሉ በዚሁ የመል እክት ማስተላለፍያ ለሚከታተልዋቸው ከአሥራ አራት ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ አጭር መል እክት እንደጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.