2014-06-24 16:48:53

ሌሎችን አለገደብ እናፍቅር፤ ሰውን ማሠቃየት ታላቅ ኃጢአት ነው፣


ይህንን ያሉ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ም እመንና ነጋድያን ጋር የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ጉባኤ አስተምህሮ ነው፣ የጥቀ ቅዱስ ቍርባን በዓል ምንም እንኳ በዕለቱ ባለፈው ሓሙስ በቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራነንሰ ባዚሊካ በመቀደስና እስከ ታላቁ የቅድስት ማርያም ባዚሊካ ሳንታ ማርያ ማጆር ቅዱስ ቍርባን ይዘው ዑደት በማካሄድ ቢያከብሩትም በአብዛኛው አከባቢ እንደሚደረገው ከሥራ ጋር ለማመቻቸት የትናንትናው እሁድም የጥቀ ቅዱስ ቍርባን እሁድ ስለሚከበር ቅዱስነታቸው “ቅዱስ ቍርባን እግዚአብሔር ምን ያህል እንዳፈቀረን ይህም አለገደብ እንዳፈቀረን የሚያሳይ ነው፣” ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ ባለፈው ሳምንት የተስታወሰው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀንና እፊታችን ዕለተ ሮብ ለሚዘከረው ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ጭቆናና ሥቃይ ቀን ምክንያት በማድረግ “ሰውን ማሰቃየት ታላቅ ኃጢአት ነው” ጭቆናና ሰውን ማሳቃየትን አውግዘዋል፣
አያይዘውም በዕለቱ የሚከበረውን በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ኮርፑስ ዶሚኒ የጌታ ኢየሱስ ሥጋ በተመልከተም ይህ ሥጋ ለሰው ልጆች ፍቅር የተፈተተ ሲሆን ይህም ጌታ ኢየሱስ ለሰው ልጆች የሰጠው ሌላ ነገር ሳይሆን ገዛ ራሱን መሥዋዕት እንዳደረገ ይገልጣል፣ የአንድ ከቅዱስ ቍርባን የተወለደ ክርስትያን እውነተኛ ጥሪም እንዲሁ ነው፣ በኢየሱስ ሥጋ መካፈል በውስጣችን አንድ አዲስ ለውጥ ያ በቅዱስ ቍርባን የተፈተተውን ኢየሱስን እስከ መምሰል የሚያደርስ ኃይል አለው፣ “መሥዋዕተ ቅዳሴ በምናሳርግበትና በክርስቶስ ሥጋ በምንመገብበት ጊዜ ዘወትር ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን ተገኝተው ይሰራሉ ልቦቻችንን ያለሰልሳሉ ጠባያችን እንደወንጌሉ ት እዛዝ እንዲሆንም ውሳጣዊ ዝንባሌዎቻችን ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ያደርገናል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ለቃለ እግዚአብሔር እንድንታዘዝና በመካከላችን ወንድማማችነት እንዲኖር ክርስትናችንን ለመመስከር ብርታት እንዲሁም የፍቅር ብርሃንና ተስፋ ለቈረጡ ተስፋ ለመስጠትና ለተገለሉት ለመቀበል ችሎታ ይሰጠናል፣ ቅዱስ ቍርባንን ልባችንን ይመግባል ክፍት እንዲሆንም ያደርገዋል፣ ምንም እንኳ እንደሰው ልጆች ፍቅራችን የተወሰነ ቢሆንም እንደእግዚአብሔር አድርገን ለማፍቀር ይረደናል፣
“የእግዚአብሔር ፍቅር መለክያ ምን ይሆን? አለገደብ ማፍቀር ሲባል ምን ማለት ይሆን? ያልን እንደሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር መለክያ የለውም፣ ሁሉ በሙላት ፍቅር ነው፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ሊለካ አይቻልም፣ በዚህም ለማያፈቅረንን ሳይቀር ልናፈቅር እንችላለን፣ ይህ ግን ቀላል አይደለም፣ ነገር ከእግዚአብሔር ወገን ከሆንን እንደ እግዚአብሔር የማያፈቅረንን ሳይቀር ማፍቀር አለብን፣ ሲሉ በቅዱስ ቍርባን መሳተፍ ሕይወታችንን እንደሚለውጥ ገልጠዋል፣
ሌላው የቅዱስ ቍርባን ጉዳይ የመፈትፈቱ ጉዳይ የመቈረሱ ጉዳይ ሲሆን ይህ ስለፍቅር የተቈራረሰው እንጀራ መጥፎ ነገርን በመልካም ነገር ምሕረት በማድረግ በመከፋፈልና በመቀበል ይቋወማል፣ እንዲህ በማድረግም ገዛ ራስን ለሌሎች በመስጠት የሚገኘውን ደስታ እንድናጣጥም ይረዳናል፣ ብለዋል፣
ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ሕይወታችን የመሥዋዕት ስጦታ ይሆናል፡ ኢየሱስን መምሰል ደግሞ ይህ ነው፣ ሁለት ነገሮች ላይ ማትኰር እወዳለሁ፣ የመጀመርያው የእግዚአብሔር ፍቅር መለኪያ የሌለው ሲሆን ወሰንየለሽ ወይንም ገደብየለሽ ነው፣ ይህንን ተከትሎ ደግሞ፤ሕይወታችን ኢየሱስን በቅዱስ ቍርባን በመቀበል የኢየሱስ ሕይወት እንደነበረው ሕይወታችንም ስጦታ ትሆናለች፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎት በኋላ በዓለም ውስጥ ስለሚፈጸመው ጭቅናና የሰው ማሰቃየት ጥፋቶችን ለማስታወስ እፊታችን ሮብ ሰኔ 26 ቀን የሚዘከረው ዓለም አቀፍ ቀንን አመልክተው እንዲህ ብለዋል፣
“በዚሁ አጋጣሚ ማንኛው የሰው ልጅ ማሰቃየት እኰንናለሁ ክርስትያኖችንም ይህ ከዓለም የሚጠፋበትና በዚሁ ለተጐዱና ቤተሰቦቻቸውን እንዲደግፉ አደራ እላለሁ፣ የሰው ልጆችን ማሰቃየት ታላቅ ኃጢአት ነው፣ እጅግ ከባድ ኃጢአት ነው፣ ሲሉ በተለያዩ የሰው ልጅ ሕይወት ዘርፎች የሚፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶች እንዲወገዱ ጥሪ አቅርበዋል፣









All the contents on this site are copyrighted ©.