2014-06-11 18:34:19

ፍርኃተ እግዚአብሔር; የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አላችሁ ሰላም! ዛሬ የምነጋገርበት የፍርኃተ እግዚአብሔር ስጦታ የሰባቱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የመጨረሻው ክፍል ይሆናል፣ ይህ ስጦታ ከእግዚአብሔር መፍራትን አያመልክትም፣ እግዚአብሔር የሚያፈቅረን የእያንዳንዳችን ደኅንነት የሚፈልቅ ዘወትር ይቅር የሚለን አባት መሆኑን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእርሱ እንድንፈራ ምክንያት ሊሆነን የሚችል ምንም የለም፣ የፍርኃተ እግዚአብሔር ስጦታ በእግዚአብሔርና በፍቅሩ ፊት ምንኛ ያህል ትናንሽ መሆናችንና ለእኛ የበለጠ የሚሆነው ደግሞ በትሕትናና አክብሮት በተሞላመት መተማመን ሁሉ በእጆቹ በመተው መሆኑን ይገልጥልናል፣ ስለዚህ ፍርኃተ እግዚአብሔር ማለት ሁለመናችን እጅግ በሚያፈቅረን በእግዚአብሔር አባታችን መተው ማለት ነው፣
    መንፈስ ቅዱስ በልባችን ማደሪያ ካገኘ በኋላ መጽናናትን ሰላም ይሞለዋል፣ ትናንሽ መሆናችን እንድናውቅ አድርጎን እንዳለነው በዚሁ ዝንባሌ ኢየሱስ በወንጌሉ አደራ እንደሚለን የሚያስጨንቁን ነገሮችንና መጠባበቆቻችን በእግዚአብሔር እንድንተው የፍቅሩ ሙቀትና መከላከል የሸፈነን ሆኖ የሚሰማንና በዚሁ ተደግፈን ልክ አንድ ሕጻን በአባቱ እቅፍ እንደሚሰማው ይሆናል፣ መንፈስ ቅዱስ በልቦቻችን ውስጥ የሚያደርገው ይህ ነው፣ በአባታችን እጆች እንደታቀፉ ሕጻናት ሆነን እንዲሰማን ያደርጋል፣ በዚህም ፍርኃተ እግዚአብሔር የታዛዥነት ባህርይ በውስጣችን በማስረጽ ይህንን ተረድተን ምስጋና እንድናቀርብ በማድረግ ልባችንን በተስፋ ይሞላዋል፣ እንደእውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ልንረዳ አንችልም በዚህም እኛ ብቻችን የደስታና የዘለዓለማዊ ሕይወት ዋስትና ልናረጋግጥ እንደማንችል እንገነዘባለን፣ የተወሰንን መሆናችንና ድኃዎች መሆናችንን በተገነዘብንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያጽናናል ያለን አንዲት ብቻ መንገድም ኢየሱስ በአባቱ እጆች እቅፍ እንዲመራን መፍቀት ምንኛ ያህል አስፈላጊ መሆኑን ያስረደናል፣
    ለዚህም ነው የዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እጅግ እንደሚያስፈልገን፣ ፍርኃተ እግዚአብሔር ሁሉ ነገር ከጸጋ እንደሚመጣና እውነተኛ ኃይላችን ደግሞ ጌታ ኢየሱስን በመከተልና እግዚአብሔር አባታችን በጎነቱና ምሕረቱን በእኛ ላይ እንዲያፈስ በመፍቀድ ብቻ መሆኑን ያረጋግጥልናል፣ የእግዚአብሔር በጎነትና ምሕረት በውስጣችን እንዲያድሩ ልባችንን መክፈት አለብን፣ መንፈስ ቅዱስ በፍርኃተ እግዚአብሔር ስጦታው የሚያደርገውም ይህ ነው፤ ልቦችን ይከፍታል፣ ወደር በሌለበት ፍቅር የተወደድን ልጆች ስለሆንን የእግዚአብሔር አባታችን ይቅር ባይነት ምሕረት በጎነትና ፍቅር በውስጣችን እስኪያድሩ ልቦቻችን እንክፈት፣
    በፍርኃተ እግዚአብሔር ከተገዛን እግዚብሔርን በትህትና እና በየዋሕነት ትዕዛዛቱን መቀበል እንችላለን። ትዕዛዛቱን መቀበል ማለት አማራጭ የሌለው በተስፋ ቢስነት ማጉረምረም ሳይሆን ግን የአባቱን ፍቅርና እንክብካቤ የሚያውቅ በአባቱ ፍቅር የተደነቀና ደስ የተሰኘ ልጅ ሆነን ነው የምናገለግለው። ስለዚህ ፍርሃተ እግዚብሔር እኛን አይነ አፋርና ፈሪ ክርስቲያኖች አይደለም የሚያደርገን ግን በኛ ውስጥ ድፍረትንና ሃይልን ይሞላል። ይህ ስጦታ ለኛ ክርስቲያኖች እርግጠኛና ደስተኞ ክርስቲያኖች ያደርገናል እንጂ በፍርሃት ለእግዚብሔር እንድንገዛ ሳይሆን ግን እግዚብሔር በፍቅርና በቸርነቱ ስለሚገዛን ነው። ይሕም በጣም ያማረና ድንቅ ነው። እስቲ በአባትነት ፍቅሩ እኛን ለሚያፈቅረን አባታችን እራሳችንን እንስጠው፣

እዚ ላይ እንድንጠነቀቅ የምፈልገው የእግዚብሔር ስጦታ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሌላው በኃጢአት እንዳንወድቅ ማስጠንቀቂያ ደውል ነው። አንድ ሰው በኃጢአት ከኖረ፦ ፈጣሪውን የሚሳደብ፤ ሌላውን የሚበዘብዝ አንባገነንና የሚያመልከው ገንዘብና ስልጣን በኩራትና ግብዝነት ከተሞላ ቅዱሱ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንድንጠነቀቅ ያደርጋል። እንድንጠነቀቅ፣ ምንም እንኳን ሃብት፤ ስልጣን ኩራት ቢሞላም ያ ደስታንና እርካታን አይሰጠውም። ማንም ሰው ይህንን አለም ትቶ ሲሄድ ያለውን ሃብትና ስልጣን ይዞ አይሄድም። ምንም ነገር ይዘን መሄድ አንችልም። ይዘን መሄድ የምንችለው እግዚአብሔር አባታችን የሰጠንን ፍቅር ብቻ ነው፣ እግዚብሔር በፍቅሩ ሲነካን እኛ በፍቅር የተቀበልነውና ለሌሎች ያደረግነውን ብቻ ነው ይዘን መሄድ የምንችለው። ስለዚህ በገንዘብ በስልጣን ኩራት አንመካ ምክንያቱም መልካም የሆነ ውጤት የላቸውምና ገንዘብና ስልጣን ደስታን አይሰጡምና። ለምሳሌ እነዚህ ባለስልጣኖች ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ በሙስና ሲደለሉ ማየቱ እነዚህ ሰዎች ይህንን አለም ትተው ሲሄዱ ደስተኞች ይሆናሉን፤ አይሆኑም የሠራው ስራ መልካም አይደለምና ልቡም ያውቃልና ወደ አምላኩ አይሄድም፣፣ በአሁን ወቅት እንደ ባርያ ሰዎች ሲሸጡ ና እንዲሁም እንደ ባርያ የሚያሰራቸው ሰዎች በእውነቱ የእግዚብሔር ፍቅር በነሱ ውስጥ አለን፤ እነዚ ሰዎች ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸውና ደስታ የሌላቸው ሰዎች ናቸው፣፣ ኣንዲሁም የጦር መሳሪያዎችን የሚያመርቱ! የጦር መሳሪያ በማምረት አንዱ ከሌላው ጋር የሚያዋጋ እቃ ማምረት ምን አይነት ስራ ነው ! እነዚህ ሞትን የሚሸጡና የሚያመርቱ የእግዚአብሔርን ቃል አያዳምጡም! ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲነካቸውና ይህ ሁሉ አልቆ ለእግዚብንሔር የሚሰጡት ማስረጃ ምንድር ነው፣ውዶቼ! ዳዊት በመዝሙር 34 ቁ 7-8 እንዲህ ያጸልየናል “የእግዚብሔር መልአክ ያሳድዳቸው በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛል” በማለት፤ የእግዚብሔርን ጸጋ የኛ የደካሞችን ጽምፅ እንዲሰማ እንለምነው ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲኖረንና በእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት እንድንመላለስ እንለምነው፣ አሜን








All the contents on this site are copyrighted ©.