2014-06-11 16:36:16

ግጭትና ጦርነት ባለበት ወቅትና ሁነት የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ለማጥፋት


RealAudioMP3 በለንደን ግጭትና ጦርነት ባለበት ወቅትና ሁነት የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ስለ ሚሆኑትና ስለ ሆኑት ማእከል በማድረግ ለመወያየት የተጠራው እ.ኤ.አ. ሰነ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ የግኑኝነት ድረ ገጽ ዘንድ ባለው @Pontifex በተሰየመው የግል አድራሻቸው አማካኝነት እ.ኤ.አ. ሰነ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. “ጦርነትና ግጭት ባለበት ወቅትና ሁነት ለወሲብ ዓመጽ ስለ ሚዳረጉትና ሰለባ ስለ ሆኑትና ጸረ ይኸንን ጸያፍ ተግባር ስለ ሚታገሉት ሁሉ እንጸልይ” የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ፣ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና ተፈናቃዮች ጉዳይ ለሚከታተለው የበላይ ድርገት ልኡክ የፊልም ተወናያን አንጀሊን ጆሊየ፣ የለንደን የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ዊሊያም ሁገ መሆናቸው ጠቅሰው፣ በዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ጉባኤ ከተለያዩ አንድ መቶ አገሮች የተወጣጡ ልኡካን፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ጆን ከርይ ሌሎች 900 የሥነ ግጭትና ጦርነት ሊቃውንት፣ የሥነ ወታደራዊና የሥነ ሕግ ሊቃውንት የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑት የሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጋች ዓለም አቀፍ ማኅበራት የሰብአዊ ማኅበራት የተለያዩ የሃይማኖት ተጠሪዎች እየተሳተፉ መሆናቸው ገልጠው፣ የለንደኑ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ጦርነትና ግጭት ባለበት ወቅትና ሁነት የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ አቢይ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር በማለት እ.ኤ.አ. ከ 1949 ዓ.ም. ጀምሮ በጀነቭ የሰብአዊ መብትና ክብር ሰነድ ዘንድ ሰፍሮ እንደሚገኝ ይኸንን ዳግም ለማሳሰብና ብሎም እ.ኤ.አ. ከ 1996 ዓ.ም. ወዲህ ከፍተኛ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ተብሎ መሰየሙ ለማስታወስ ጦርነትና ግጭት ባለበት ወቅትና ሁነት ታጣቂ ተዋጊ እንዲሁም የመንግሥት ወታደሮች የሚፈጽሙት ጸያፍ ተግባር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የታየ በዩጎስላቪያ ነበር ግዛት ክልል፣ በቦዝኒያ ኤርዘጎቪና በጠቅላላ ከ 20 እስከ 50 ሺሕ የሚገመቱት ሴቶች ታዳጊ ሕፃናት ሴቶች በቤታቸው እያሉ በባለ ቤታቸውና ወላጆቻቸው ፊት በጎዳናዎች ሳይቀር የዚህ አመጽ ሰለባ መሆናቸውና ይኽ ጸረ ሰብአዊ ተግባር አንዱ የጦር መሣሪያ ሆኖ በሩዋንዳ ዘር የማጥፋት ዓመጽ ተከስቶ በነበረበት ወቅት በጠቅላላ 250 እስከ 500 ሺሕ የሚገመቱት ሴቶች ለዚህ ዘግናኝና ጸያፍ ኢሰብአዊ ተግባር መዳረጋቸው በማስታወስ፣ ይኽ ጸረ ሰብአዊ ተግባር አሁንም ጦርነትና ግጭት ባለበት ወቅትና ሁነት ተመላልሶ የሚከሰት መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ የሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጋች አምነስት ኢንተርናሽናል የተሰየመው ዓለም አቀፍ ድርጅት የሰጠው መግለጫ ጠቅሰው ከገለጡ በኋላ በሶሪይ በኮሎምቢያ በኢራቅ በቸቸኒያ በአፍጋኒስታን በሱዳን በቻድና በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ብዙ ሴቶችና ወንዶች ታዳጊ ሕፃናት የዚህ የጸረ ሰብአዊ ዓመጽ ሰለባ መሆናቸው የድርጅቱ ሰነድ በማስደገፍ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.