2014-06-11 16:30:30

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ኤጂዲዮ እንቅስቃሴ ለሐውጾተ ኖልዎ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 5 ሰዓት ሮማ በሚገኘው በካቶሊካዊው የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበርሰብ ሰብአዊ መንፈሳዊና ሕንጸት ከሚለገስላቸው ተረጅ የኅብረሰብ አባላት ጋር እንደሚገናኙ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ጭምር ማእከል የሆኑት ድኾች በሚያካሂዱት ኵላዊ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማእከል በማድረግ የሚኖሩት ተግባር መሆኑና፣ በተለያየ ማኅበራዊ ሰብአዊ ኤክኖሚያ ችግር ምክንያት ተነጥለው የሚኖሩት ጎዳና ተዳዳሪዎች በጠና ድኽነት ሥር የሚገኙት በቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር የሚረዱት ጋር በመሆን ድኾች ባጋጠማችቸ ድኽነት፣ ተገደው በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙትን ሁሉ ወንድሞች ጓደኞች ላለን እምነት መመዘኛ ለእነርሱ የሚለገስ ፍቅር ለክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያለን ፍቅር መመዘኛ መሆኑ በተለያየ ወቅት የሚሰጡት ስልጣናዊ ምዕዳን የሚያስተጋባ ሓውጾተ ኖልዎ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እሁድ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ አምስት ሰዓት በቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር መሥራች ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ ተሸኝተው በቅድስት ማርያም ዘትራስተቨረ አደባባይ ከሚገኙት ምእመናን ጋር ተገናኝተው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት እዳምጠው በተራቸው አጭር መልእክት ለግሰው፣ በቅድስት ማሪያም ዘትራስተቨረ ባዚሊካ በመግባት ጸሎት አሳርገው የምህረት እናት ቅዱስ ምስል ተሳልመውና ለክብሯ ጸሎት ደግመው እንዳበቁም የተለያዩ ምእመናን የሚሰጡት ጥልቅ የእምነት ምስክርነት አዳምጠው ሥልጣናዊ ምዕዳን ለግሰው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥጠው እንዳበቁም ወደ ቅዱስ ኤጂዲዮ የማኅበሩ ተቋም ዘንድ በመሄድ ከዚህ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር መንፈሳዊነት ከሚከተሉ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት የዘርአ ክህነ ተማሪዎች የማኅበሩ ያመራር አካላት ጋር እንደሚገናኙ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.