2014-06-10 16:32:02

የር.ሊ.ጳ የንግሥተ ሰማያት ጉባኤ አስተምህሮ;


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተፈሥሒ ንግሥተ ሰማይ ሃሌሉያ የሚለው ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለተ ታላቅ በዓል ጰራቅሊጦስን የሚመለከት ትምህርትና ማምሻውን ላካሄዱት የእስራኤልና የፍልስጥ ኤም መሪዎች የሰላም ጸሎት በሚመለከት ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲሰጠን በጸሎት እንድንረዳቸው አደራ ብለዋል፣
የእስራኤል ፕረሲደንት ፐረዝና የፍልስጥኤም ፕረሲደንት ዓባስ በኢኩመኒካዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሜዎስ አንደኛ ተሸኝተው ቅዱስ አባታችን ባቀረቡት ዕድሜ ለአገሮቻቸው ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ ለማግኘት ሰላም ማምሻውን በቫቲካን ጸሎት አሳርገዋል፣ ቅዱስነታቸው በእኩለ ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር እንዲህ ብለዋል፣
“ለዚሁ ግንኙነት በግልም ይሁን በኅበረት ለጸለዩት ሁሉ ለማመስገን እወዳለሁ፤ እንዲሁም ዛሬ ማታ በምናደርገው ጸሎት በመንፈስ ከእኛ ጋር አብራችሁ ለመጸለይ የወሰናችሁን አመሰግናለሁ፣” ሲሉ ልባዊ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ዕለቱ በዓለ ጰራቅሊጦስ መሆኑን በማስታወስ በዚሁ ዕለት በጽርሓ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት ዕለት ነው፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በሚደርስበት ሁሉ ማንኛው ነገር እንደገና ይወለዳል እንዲሁም ይታደሳል፣
“የጰንጠቆስጦ ፍጻሜ የቤተ ክርስትያን ልደትንና በይፋ መገለጥዋን ያመለክታል፣ በዚሁ ፍጻሜ ሁለት ነገሮች ጐልተው ይታያሉ፤ ቤተ ክርስትያን ሁሉንም ያልታሰበ አስደሳች ነገሮች በመፍጠርና ሁኔታዎችን በማገማጠል ታስደንቀናለች፣ እንዲህ በመሆኑም ከኢየሱስ ሞት በኋላ ከሐዋርያት የሚጠበቅ ምንም አልነበረም፤ ምክንያቱም ትርጉም የሌላቸው ትንሽ ቡድን ሆነው መምህራቸው ከሞተ በኋላም እጓለማውታዎች ሆነው እንደተሸነፉ ይታዩ ነበር፣ ነገር ግን ሁኔታው እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ ተቀያየረ፣
“ሐዋርያት ከሰማያት ኃይል ይለብሳሉ በብርታትም መናገር ይጀምራሉ፣ መለስ ብለን ሁኔታውን ያየን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ከመውረዱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በፍርሃት ተውጠው ተደብቀው ነበር ነገር ግን አሁን በብርታትና በኃይል ይናገራሉ የመንፈስ ቅዱስ ነጻነትም ይለብሳሉ፣ ምናልባት በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሰዎች አንድ ሐዋርያቱ ተደብቀው የነበሩት ግርግር ላለመፍጠር ነበር ለማለት ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ጌታ ወደ መላው ዓለም እንዲሄዱ ገፍቶ ያወጣቸዋል፣
“የጴንጠቆስጠ ቤተ ክርስትያን ሌሎችን ላለመጕዳት እጅዋን የምትሰጥ ወይንም ከሁሉም ነጻ የሆነች ንጽሕት ለመሆን የምትጥር አይደለችም፣ የቍንጅና ሽልማት ሆና ለመቅረት የተፈጠረች አይደለችም፣ ወደ ውጭ ወጥታ ሰዎችን ለማግኘትና በአደራ የተሰጣትን መል እክት ለመስበክ የማትፈራ፤ መል እክቱ የሚበጥብጥና ሰላም የሚነሳም ይሁን፤ ይህ ራብሻ የኅልና ጉዳይ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ ችግር ሊያመጣ ይችላል እስከ በሰማዕትነት ሞትን ሊያስከትል ይችላል፣
ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምሮ አንድና ዓለም አቀፍ ሆና ነው የተወለደችው፣
“ማንነትዋ ግልጽ ነው ነገር ግን ዓለምን ለመቀበል ክፍት ናት ለመቀበል እንጂ ለመያዝ አይደለም ለዚህም ነጻ ትተወዋለች ነገር ግን እዚህ አደባባይ እንደምናያቸው ምሶሶዎች እንዳንዱ ታቅፈዋለች ሁለቱ እጆችዋ ለማቀፍ ክፍት ናቸው፣ ነገር ግን ይዛው ለመቅረት እጆችዋን አታጥፍም፣








All the contents on this site are copyrighted ©.