2014-06-09 17:52:36

ር.ሊ.ጳ ፍራንሲስ ርእሰ ብሔር ፐረስ እና ፕረሲዳንት ዓባስ በቫቲካን የሰላም ልመና ጸሎት ፈጽመዋል፡


የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ እና የፓላስጢና ራስ ገዝ መሪ ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ ትናትና አምሻቸው ቫቲካን የገቡ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ደማቅ አቀባበል እድርጎውላቸዋል ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ወርሀ ግንቦት መጨረሻ ገደማ በአማን ዮርዳኖስ በቤተ ልሔም ፓለስጢና እና ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እስራኤል ሐዋርያዊ ዑደት ባካሄዱበት ግዜ ግንቦት 25 ቀን በቤተ ልሔም አዳባባይ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ሁለቱ ባለስልጣናት ወደ ቫቲካን እንዲ መጡ እና ክሳቸው ጋር አብረው በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲወርድ እንዲጸለዩ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ፐረስ እና ዓባስ ጥሪውን ተቀብለው መቀበላቸው ይታወሳል።ይህ ትንትና ምሽት ቫቲካን ውስጥ የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎሞዮ ቀዳማዊ ጨምሮ ቫቲካን ውስጥ የተካሄደው ግንኙነት
Invocation for Peace የሰላም ልመና ግንኙነት መሰየሙ ይታወቃል ።
ይሁን እና ርእሰ ብሔር ፐረስ እና የፓለስጢና ራስ ገዝ መሪ ፕረሲዳንት ዓባስ ቫቲካን እንደገቡ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር በተናጠል ከተወያዩ በኃላ በጋራ የሰላም ልመና ጸሎት ለማድረስ ወደ ቫቲኣን ጋርደን መናፈሻ ተጉዘዋል የሰላም ልመና ጸሎት አጋር የሆኑና ስለዚሁ ጉዳይ ከኢስጣምቡል ቫቲካን የገቡ የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎሞዮ ቀዳማዊ በዚሁ ሥርዓተ ጸሎት ተገኝተዋል።
የዚሁ የሰላም ልመና ጸሎት ተሳታፊዎች ይሄውም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ እና የፓለስጢና ራስ ገዝ መሪ ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ በየእምነታቸው ከጸለዩ በኃላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡ሰላምን ህያው ለማድረግ ከመጋጨት መቀራረብ ዓመጽን አስወግዶ ለውይይት ዝግጁ መሆን ፍጹም ቁራጥነትን ያሻል ብለዋል ። ሰላም ነማነጽ ከባድ ነው ሰላም አልባ መኖር ግን ስቃይ ነው ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ።
ርእሰ ብሔር ሺሞን ፕረስ ቅድስነትዎ ያዳረጉልኝ የሰላም ልመና ጸሎት ከልብ ተቀብየ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መጥቻለሁኝቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለእስርኤል ህዝብ የልብ ትርግታ ናት ። በጥንታዊ የእብራይስጥ ቋንቋ ኢየሩሳሌም የሚለውን ቃል ሰላም ተብሎ ይተረጐማል ። ኢየሩሳሌም እና ሰላም ምንጫቸው አንድ ነው ። ይሁን እና እና ሐላፊዎች ነን ለመጪው ትውልድ ሰላም ማስረበብ ይጠበቅብናል ብለዋል። ፕረሲዳንት ዓባስ ቅድስነትዎ እንደገና ከርስዎ ሲገናኝ እጅግ ደስ ይለኛል ላደረጉልኝ ጥሪ እና ከርእሰ ብሔር ሺሞን ፕረስ ጋር ቫቲካን ውስጥ እንድንገናኛ ማድረጋችሁ የሚደነቅ ነው።በቅርቡቅድስት ፓለስጢና በተለይ የሰማያት በር የሆነችው ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከተማችን መጐብኘትዎ እና የክልሉ ህዝቦች በሰላም እንዲኖሩ ያስተላለፉት ጥሪ አመስገናለሁ የፍልስጤም ህዝብ ሰላም የፈልጋል ብለው ብ ለዋል ።
ሰላም ነማነጽ ከባድ ነው ሰላም አልባ መኖር ግን ስቃይ ነው ፓፓ ፍራንሲስ
በመቀጠልም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲወርድ የተማለሉ አራቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያሪኩ እና ሁለቱ የፖሊቲካ ባለስልጣናት የሰላም ምልክት የሆነው የወይራ ችግኝ በቫቲካን መናፈሻ ከተከሉ በኃላ በጋራ ወደ የቫቲካን የሳይንስ አካዳሚ ቢሮ ተጉዘው በግል ተነጋግረዋል ።ከግማሽ ሚእተ ዘመን በላይ ያስቆጠረው የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት በሰው ዓቅም እና ብልሃት ሰላማዊ መፍትሔ ሊገኝለት አልቻለም እና ሰማይና ምድር የፈጠረ ከሃሌ ኩል እግዚአብሔር ሰላሙ እንዲሰጥ ልመና ምህላ እና ጸሎት ተደርጎለታል። ይህ በኢህ እንዳለ ሆኖ በቅርቡ ሐማስ የተባለ የፍልስጤም የፖሊቲካ ድርጅት እና ፍታሕ ልዩነታቸው አስወግደው የብሔራዊ አንድነት መንግስት መመስረታቸው እና እስራኤል ሐማስን ካካተተ መንግስት ለሰላም ድርድር እንድማትቀርብ እስራኤል ማስታወቅዋ ይታወሳል ። እስራኤል ሐማስን እንደ አሸባሪ እንደምትፈርጀው ይታወቃል።ይህ በዚህ እንዳለ ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ እና ማሕሙድ ዓባስ ዛሬ ረፋድ ላይ በተናጠል ከየጣልያን መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል ።የpax Christi የክርስቶስ ሰላም ማሕበር ብጹዕ አቡነ ጆቫኒ ጂዱቺ እንዳመለክቱት የሰላም ልመናው ከየፖሊቲካ እና ዲፕሎማሲ ጥረት ይበልጣል እና ትናትና የተካሄደው ግንኙነት መልካም እምርታ ነው ። ለዚህም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መመስገን እና መወደስ ይገባል ያልይ የፓክስ ክርስቲ የክርስቶስ ሰላም ማሕበር ፕረሲዳንቱ ፓፓ ፍርስንሲስ እንዳሉት ለሰላም ቁራጥነት ያሻል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለሰልም ህንጸት እባ በዓለም ማሕበራዊ ፍትሐዊነት እንዲነግስ የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ እንደሚገኙ ብጹዕ አቡነ ጆቫኒ ጁዲቺ በማያይዝ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.