2014-06-04 17:47:33

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ሰላም! ዛሬ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ በሆነው የርኅራኄ ስጦታ እንመለከታለን፣ ይህ ስጦታ አብዛኛውን ጊዜ በትክክል ባለመረዳት ወይንም ጠለቅ ብሎ ባለመመልከት ዋነኛ ሥራውን ይዘነጋል፣ እንደእውነቱ ግን የማንነታችንና የክርስትና ሕይወታችን አንኳር ይነካል፣ስለዚህ ከሁሉ አስቀድመን ይህ ስጦታ ስለአንድ ሰው ያለን ርኅራኄ ወይንም ለጓደኛ የምታሳየው ርኅራኄ አለመሆኑ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የተገባን መሆናችንና ከእርሱ ጋር ጥልቅ ትስ ስር እንዳለን የሚያመልክት ነው፣ ይህ መተሳሰር ለመላው ሕይወታችን ትርጉም ይሰጠዋል ጽናት ሰጥቶም በአስቸጋሪና ፈተና በሞላባቸው ግዝያትም ሳይቀር ከእርሱ ጋር በአንድነት እንድንኖር ያደርገናል፣
    ይህ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን መተሳሰር እንደ ግዳጅ ወይንም እንደጫና አይደለም፣ ከውስጥ የሚፈልቅ መተሳሰር ነው፣ ልብ ለልብ በመገናኘት መኖርን ያመለክታል፣ በኢየሱስ የተሰጠን ሕይወታችንን የሚለውጥና በመልካም ፍላጎትና ደስታ የሚሞላን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ጓደኝነት ነው፣ ስለዚህ የርኅራኄ ስጦታ ከሁሉ አስቀድሞ በልባችን የምስጋናና የአምልኮ ፍላጎት ይቀስቅሳል፣ የሥርዓተ አምልኮአችንን የስግደታችን እውነተኛ ትጉምና ምክንያትም ይህ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር መኖሩንና ለእኛ ያለውን ፍቅር እንድንረዳ በሚያደርግበት ጊዜ ልባችን ይሞቃል እንደባህርያዊ ነገርም ለጸሎትና ለሥርዓተ አምልኮ ይገፋፋናል፣ ስለዚህ የርኅራኄ ተመሳሳዮች፤ የአንድ ልበ ትሑት ሰው ባህርያት የሆኑ፤ የእውነተኛ የእምነት መንፈስ፤ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን መተማመን፤ እንዲሁም በፍቅርና በየዋህነት የመጸለይ ችሎታ፤ ናቸው፣
    የርኅራኄ ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግኑኝነትና ውህደት እንደልጆቹ ለመኖር ሲረዳን በሌላ በኩል ደግሞ ፍቅሩን ለሌሎች እንድናስተላልፈውና እንደ እኅቶችና ወንድሞች ልናውቃቸው ይረዳናል፣ በዚህም በስሜታዊ ርኅሩኅነት ተገፍተን ሳይሆን በዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተነክተን በጐረቤቶቻችንና በየዕለቱ በምናገኛቸው ሰዎች ላይ ርኅራኄ እናሳያለን፣ ለምንድር ነው ስሜታዊ ርኅራኄ የምለው? ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ርኅራኄን ዓይንን ጨፍኖ የአንድ ስእል ገጽታ እንዲኖራቸው ስለሚታገሉ ነው፣ እንዲህ የማይሆን ነገር ነው፤ የባሰውኑ ደግሞ አስመሳይ ቅዱስ ሆኖ መመላለሱ፣ ስለዚህ ከሚደሰተው እንድንደሰት ከሚያለቅሰው እንድናለቅስ ብቸኛነት ወይንም ሓዘን ካጠቃቸው ጎን በመሆን እንዲሁም የተሳሳተውን በማረም በሓዘን ሰቆቃው ያለውን ማጽናናት ድሆችንና የተቸገሩትን መቀበልና መርዳት ነው፣ በርኅራኄ ስጦታና በትሕትና ታላቅ ግኑኝነት አለ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን የርኅራኄ ስጦታ ትሑታን ሰላማውያን ት ዕግስተኞች እና ከእግዚአብሔር ሰላም ያላቸው ሰዎች ያደርገናል፣ በትሕትናም ሌሎችን ለመርዳት ያስችለናል፣

ውዶቼ! ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮማውያን በጻፈው መልእክት “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።” (ሮማ 8፤14-15) ይለናል፣ በዚሁ የመንፈስ ስጦታ ፍርሃቶቻችን መጠራጠራችን ያለመረጋጋት መንፈሳችንና ትዕግሥት ማጣታችን ለማሸነፍና የእግዚአብሔርና የፍቅሩ ደስተኞች ምስክሮች እንድንሆን ያስችለን ዘንድ ጌታን እንለምነው፣ እግዚአብሔር በመንፈስ በማመልከና በትሕትናና መንፈስ ቅዱስ በደስታ በሚሰጥን በፈካ ፊት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን እናገልግል፣ መንፈስ ቅዱስ ለሁላችን ይህንን የርኅራኄ ስጦታ ይስጠን፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.