2014-05-22 18:48:54

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ዛሬ ስለ አንድ ሌላ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለመናገር እወዳለሁ፣ ይህ ስጦታ እውቀት ይባላል፣ ስለእውንቀት ሲነገር ሃሳባችን ወዲያውኑ የሰው ልጅ ነገሮችን በበለጠ ለማወቅ ያለው ችሎታ እና ተፈጥሮንና ህዋን የሚገዙ ሕጎችን ለማወቅ የሚያደርገው አሰሳ ላይ ይሄዳል፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን የዕውቀት ስጦታ ግን በሰው ልጅ እውቀት አከባቢ ብቻ አይቆምም! ልዩ ስጦታ በመሆኑም በፍጡር አማካንነት የእግዚአብሔር ታላቅነትና ፍቅር እንዲሁም ከሁሉም ፍጡር ጋር ያለውን ጥልቅ ግኑኝነት ለመረዳት ያስችለናል፣
፩. ዓይኖቻችን በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ስለእግዚአብሔር ለማስተንተን ሲከፈቱ የተፈጥሮ ቆንጆነትና የምንኖርበት ህዋ ታላቅነት ሲያዩ እያንዳንዱ ነገር ስለእግዚአብሔር እንደሚናገረን እንዲሁም ስለፍቅሩ እንደሚናገር ለመረዳት ያስችሉናል፣ ይህ ሁሉ በልባችን ታላቅ መደነቅ እንዲሁም ጥልቅ ምስጋና ለማቅረብ ያስችለናል፣ ይህ ስሜት አንድ የስነ ጥበብ ስራ በምናደንቅበት ግዜ እንደሚሰማን ነው፣ የእግዚአብሔር እጆች ሥራ የሆኑ ተፈጥሮን ስናደንቅ ደግሞ በምናየውና በእኛም ውስጥ ስለሚገኘው አስደናቂ ነገሮች ስንመለከት እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ስጦታ እንደሰጠን በመረዳት ይህም የእግዚአብሔር ወደር የለሽ ፍቅር ምልክት መሆኑን እንረዳለን፣
፪. በመጽሓፍ ቅዱስ መጀመርያ ላይ በሚገኘው በኦሪት ዘፍጥረት የተመለከትን እንደሆነ እግዚአብሔር ራሱ ስለፍጥረቱ ደስ እንዳለው ምንኛ መልካም እንደነበራ ደጋግሞ የእያንዳንዱ ፍጥረት መልካምነት ይገልጣል፣ በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ላይ “እግዚአብሔርም መልካም እንደ ሆነ አየ” (1፤12.18.21.25) ነገር እግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መልካምና ቆንጆ መሆኑን ካየ እኛም በዚሁ ዝንባሌ መሄድ አለብን፤ ፍጥረት ሁሉ መልካምና ቆንጆ መሆኑን ማየት፣ ይህ ነው የእውቀት ስጦታ፤ ይህንን መልካምነት እያይን ይህንን መልካምነት ስለሰጠን እግዚአብሔርን ማክበርና ማመስገን ነው፣ ትክክለኛ መንገዱም ይህ ነው፣ እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላ “መልካም እንደ ሆነ አየ” ከማለት “እጅግ መልካም እንደሆነ አየ” በማለት የሰው ልጅ መልካምነት ከሁሉ የበለጠ እንደነበረ ይገልጣል፣ ወደ እርሱ ያቀርበናል፣ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት እኛ ከሁሉ የበልጥን ከሁሉ የላቅን ነን፤ አዎ ከፍጥረት ሁሉ የበለጥን ነን፣ ምናልባት ከእናንተ መላእክትስ ብሎ የሚጠይቅ ካለ፤ መልሱ አይደለም ነው መላ እክት ከኛ በታች ናቸው እኛ ከመላእክት እንበልጣለን፣ በመዝሙር ዳዊት ላይ “አንተ እርሱን እንድታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ከፍጥረትም ሁሉ በላይ አደረግኸው” (8፡4-6) ይላል፣ ለዚህም ልናመሰግነው ይገባናል፣ የእውቀት ስጦታ ጠለቅ ባለ መንገድ ከጌታ ጋር እንድንወሃሃድ ያደርገናል በዚህም በእርሱ ጥርት ያለ አስተያየትና ፍርድ እንድንሳተፍ ያደርገናል፣ በሰው ልጅ ፍጥረት ማለት በወንድና ሴት ፍጥረት የዚህ ጠርዝ ለመረዳት እንችላለን፣ ይህ ታላቁ የፍቅር እቅድ ሆኖ በእያንዳንዳችን የታተመና እያንዳንዳችን እንደ ወንድምና እንደእኅት እንድንተዋወቅ ይረዳናል፣
ይህ ሁሉ ነው ለክርስቲያኖች የሰላም ምክንያት እነሱም በደስታ ለእግዚብሔር የሚመሰክሩት ቅዱስ ፍራንቼስኮና ሌሎችም ቅዱሳት በሙሉ ከተመለከትን ፈጣሪያቸውን ሲያመሰግኑ ፍቅሩን የሚገልጹት በምስጋናናን በዝማሬ የሚያወድሱት የፍጥረት መሠረቱን በማድነቅ ነው፣፣ በተመሳሳይ መንገድ ደግሞ የሳይንስ እውቀት ስጦታ ግን ከልክ ያለፈ ዘዴና አመለካከት እንዳንወድቅና እንዳንሳሳት ያስተምረናል።
የመጀመሪያው የተሳሳተ አመለካከት የተፈጥሮ ጌቶች ነን ብለን ካሰብን ነው፣፣ተፈጥሮ የግል ሃብት አይደለም እንደፈለግን ልናደርገው የምንችል ወይንም የአንዳንዶችንና የጥቂት ግለሰቦች ንብረት አይደለም። ተፈጥሮ ስጦታ ነው። ይህም ልዩ ያማረ የእግዚብሔር ስጦታ ነው። ሁላችንም በእንክብካቤ በአክብሮትና በምስጋና እንድንይዘውና እንድንጠቀምበት ነው።
ሁለተኛው የተሳሳተ አመለካከት ተፈጥሮን ለማቆም የሚደረገው ነው ይህ ሁሉም የሚጠብቀው መልስ መፍትሄ ይመስል በዚህ አመለካከት እንዳንወድቅም መንፈስ ቅዱስ በሳይንስ እውቀት ስጦታ አመለካከት ይረዳናል። እኔ ወደ መጀመሪያው የተሳሳተ አመለካከት መንገድ ተመልሰን እንድንመለከት እፈልጋለሁ። ተፈጥሮን በአደራነት ማስቀመጥና ተፈጥሮን እንደ ግል ንብረት መቆጣጠር የሚለውን ነው፣፣
ተፈጥሮን እንደ አደራ እቃ በእንክብካቤ መያዝ አለብን ። ተፈጥሮ እግዚአብሔር አባታችን ለኛ የሰጠን ስጦታ ነው። እኛ በእንክብካቤ መጠበቅ አለብን። እኛ ተፈጥሮን ሃብት ከመጠን በላይ ከተጠቀምን እናጠፋዋለን የእግዚብሔር የፍቅር ስጦታን ምልክት እናጠፋለን።
በገዛ እጃችን ተፈጥሮን እያጠፋን ለእግዚብሔር ይህ አያስደስተኝም ለኔ መልካም አይደለም እንደ ማለት ነው። ምንድነው የሚያስደስትህ ወይም የሚያስደስተን እኛ የምንፈልገው በውስጣችን ያለ ብቻ ነው እዚህ ላይ ነው ኃጢዓቱ ተመለከታችሁ! የተፈጥሮ አደራነት እግዚአብሔር በአደራነት እንድናስቀምጠው የሰጠን ስጦታ ነው እግዚብሔርም ለሰጠን ስጦታ እኛም የስጦታው ባለቤቶች ስላደረገን ማመስገን አለብን።የምናመሰግነውም እሱ የሰጠንን ስጦታ በእንክብካቤ ተፈጥሮን በመያዝ ነው። በእንክብካቤ የምንይዘው ምክንያቱም ተፈጥሮን በጥንቃቄ ካልያዝነው ተፈጥሮ ያጠፋናል። ኤ ምን የሚለውን ቃል አትርሱ! አንድ ግዜ ወደ ገጠር ሄጄ አንድ ሰው ያለኝን ላጫውታችሁ! ይህ ሰው አበባ በጣም ስለሚወድ ምን አለኝ እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠን ቆንጆ ስጦታዎች ተንከባክበን እንያዛቸው የተፈጥሮ መልካም ነገሮች ለኛ ስጦታ እስከሆኑ ድረስ እኛም በደንብ እንከባከባቸው! ሁሉንም ማውደም ማጥፋት የለብንም በአደራ ማስቀመጥ አለብን። ምክንቱም አባቴ እርሶ እግዚአብሔር ሁሌ ይቅር እንደሚል ያውቃሉ አዎን አውቃለሁኝ እውነት ነው ግን እኛ ሰዎች ወንዶችና ሴቶች አንዳንዴ ነው ይቅር የምንለው አዎን አንዳንዶች ይቅር አይሉም ግን ተፈጥሮ አንተ በአደራ በደንብ ካልተከባከብክውና ካልጠበኸው ማንንም አይምርም ያጠፋሃል። ይህ በደንብ እንድናስብበትና ለመንፈስ ቅድሱ መጠየቅ ያለብን ስጦታ ሳይንስ በደንብ በመረዳት ተፈጥሮ ከሁሉም የሚበልጥ እግዚአብሔር የሰጠን ስጦታ መሆኑን መረዳት ነው። እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ሁሉ መልካም ነው መልካም ነው ብሎ ለሚወደው ለሰው ልጅ የሰጠው ስጦታ ነው። አመሰግናለሁኝ፣
ከትምህርቱ በኋላ ምእመናኑን በተለያዩ ቋንቋዎች ካመሰገኑ በኋላ “ሃሳቤና ቀልቤ ገና በውኃ ማጥለቅለቅ ለተጐዱት ብዙ ሕይወትና ንብረት በመውደምና ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ከሚሰቃዩ የቦስንያ ሄርዘጎቪና እና የሰርብያ ሕዝብ አልተለየም፣ ሁኔታው ገና እንዳልተሻሻለና እየተባባሰ መሆኑ ነው ስለዚህ ገና በጸሎት እንድረዳቸው አሳስባለሁ፣ ለነዚሁ ወንድሞቻችን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አጋርነትና ተጨባጭ ድጋፍ እንዳይለያቸው አደራ፣ ሁላችን በኅብረት ለዚህ ሕዝብ እንጸልይ በማለት በአደባባዩ ከነበረው ሕዝብ ጋር በጣልያንኛ ቋንቋ ሰላም ላንቺ ኦ ማርያም የሚለውን ጸሎት አሳረጉ፣በመጨረሻም እፊታችን ቅዳሜ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልከተው እንዲህ ብለዋል፣ “እፊታችን ቅዳሜ በኢየሱስ ምድር በሆነችው በቅድስት መሬት ሐዋርያዊ ጉዞ አደርጋለሁኝ፣ ይህ ጉዞ የእምነት ጉዞ ነው፣ የመጀመርያው ምክንያት በር.ሊ.ጳ ጳውሎስ ስድስተኛና ፓትርያርክ አተናጎራ አንደኛ የተደረገው ታሪካዊ ግኑኘት ሓምሳኛ ዓመት ለማስታወስ ከወንድሜ በርጠለሜዎስ አንደኛ እንድገናኝ ይህ ማለትም ጴጥሮስን እንድርያስ እንደገና ይገናኛሉ ማለት ነው ይህም እጅግ ጥሩ ነው፣ ሁለተኛው ምክንያት ለዛች በብዙ ስቃይ ስር ለምትገኝ ሰላም እንድታገኝ ለመጸለይ ነው፣ ለዚሁ ጉዞ እንድትጽልዩ እጠይቃለሁ፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.