2014-05-15 17:36:20

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ባለፉት ቀናት ስለ ሶስት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ማለትም ስለ የጥበብ የማስተዋል እና የምክር ተመልክተናል፣ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር በሕይወታችን ስለሚሠራው ሌላ ስጦታ እንመለከታለን፣ በድካማችን ጊዜ እግዚአብሔር ራሱ ሊረዳን ይመጣል ይህንንም ጽናት በተሰኘው ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ሃብት ስጦታ ያደርገዋል፣
    የዚህ ስጦታ አስፈላጊነትና ትርጉም ለመረዳት የሚረዳን በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ የነገረን አንድ ምሳሌ አለ፣ ዘሪ ሊዘራ ወጣ ይላል፤ ከተዘራው ዘር የሚበቀለው ሁሉም አይደለም ሆኖም ግን ያ የበቀለው ፍሬ ይሰጣል፣ በመንገድ ላይ የወደቀው ዘር የሰማይ ወፎች ይለቅሙታል፣ ያ በጨምጫማ ቦታ የወደቀው ወዲያዉኑ ይበቅላል ነገር ሥር ስላልሰደደ ትንሽ ድርቅ ባጋጠመበት ወዲያውኑ ጠውልጎ ይደርቃል፣ በእሾህ መካከል የወደቀውም በእሾሁ ታንቆ ፍሬ ሳይሰጥ ይቀራል፣ ያ በመልካም መሬት የወደቀ ዘር ብቻ ነው ሊያድግና ፍሬ ሊሰጥ የሚችለው (ማር 4፡3-9/ ማቴ 13፡3-9/ ሉቃ 8፡4-8 ተመልከቱ)፣ ኢየሱስ እንደሚገልጠው ይህ ገበሬ ወይንም ዘሪ እግዚአብሔር አብ ራሱ ሆኖ የቃሉ ዘር በለጋስነት ይዘራል፣ ሆኖም ያ ዘር አብዛኛውን ግዜ በልበ ደንዳነታችን ተቋውሞ ያጋጥመዋል፤ እሺ ብለን የተቀበልነው ብንሆንም ምንም ፍሬ ሳላፈራ መክኖ የመቅረት አደጋ ያንዣብበዋል፣ ጽናት በተሰኘው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ግን መንፈስ ቅዱስ የልባችን መሬትን ነጻ አድርጎ በደንብ ያዘጋቸዋል ከመጠራጠርና ዕንቅፋት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ አንድጽቶ የጌታ ቃል ለመቀበልና በሚገባ መንገድ በደስታ እተግባር ላይ ለመዋል እንድንችል ያደርገናል፣ ይህ የጽናት ስጦታ ለእኛ ታላቅ እርዳታ ነው፤ ኃይል ይሰጠናል እንዲሁም ከብዙ መሰናክሎች ነጻ ያደርገናል፣
    አንዳንዴ በሕይወት እጅግ ከባድ ችግሮችና አስጨናቂ ጊዜዎች ያጋጥሙናል በዚህ ጊዜ ነው የጽናት ስጦታ ከምናስበው በላይ ሲሰራ ይታያል፣ አብነታዊ በሆነ መንገድ ሲሰራ ይታያል፣ ይህ የሚሆነው ሰዎች እጅግ ከባድ እና ስቃይ የበዛበት ችግር አጋጥሞዋቸው ሕይወታቸውና የውዶቻቸው ሕይወትን በሚያጨልምበት ጊዜ ነው፣ ቤተ ክርስትያን የብዙ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ሕይወታቸውን እንኳ መስዋዕት በማድረግ ለጌታና ለወንጌሉ ታማኝ የሆኑ አማኞች ምስክርነት ያሸብርቅባታል፣ ዛሬም ቢሆን ሰማዕትነትን በጽናት የሚቀበሉ ብዙ ክርስትያኖች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በታላቅ ታማኝነትና ጽናት እምነታቸውን የሚመሰክሩ ጥቂት አይደሉም፣ የሚከፈለው ዋጋ እጅግ ታላቅ መሆኑን እያወቁ ነው ይህንን ጀግንነት የሚፈጽሙት፣ እኛም - እኛ ሁላችን - ከባድ ፍጻሜዎችና ብዙ ስቃይ የተቀበሉ ሰዎች እናውቃለን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዕለታዊ ኑሮአቸውን ለመምራት ቤተሰብን ወደ ፊት ለመራመድ ልጆቻቸውን ለማስተማር ከባድ ሕይወት እየኖሩ ያሉ የዘመናችን ወንዶችና ሴቶች ያሰብን እንደሆነ ታላቅ መሥዋዕት ነው እየከፈሉት ያሉት እንዲህ ለማድረግ የቻሉበት ምክንያትም መንፈስ ቅዱስ የሚረዳቸው የጽናት ስጦታ ስላደላቸው ነው፣ እንዲሁም እኛ የማናውቃቸው ነገር ግን ሕይወትን ወደፊት ለማራመድ ቤተሰቦቻቸውን ሥራዎቻቸውን እምነታቸውን በብርቱ ጽናት የሚጋፈጡ በዚህም ለቤተ ክርስትያንችንና ለሕዝባችን ክብር የሚሰጡም አሉ፣ እነኚህ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በመካከላችን ትደብቀው የሚኖሩ ቅዱሳን ናቸው የየዕለቱ ቅዱሳን ናቸው፤ በየዕለቱ በሚያደርጉት ሌሎችን ለመርዳት እንዲሁም አባቶቻቸውን እናቶቻቸውን ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸው እንዲሁም ለሌሎች ለመርዳት በሚያሳዩት ብርታት ያስተምሩናል፣ የዚህ ዓይነት ሰዎች ብዙ አሎን፣ እግዚአብሔርን ስለነዚሁ ድብቅ ቅዱሳን ነገር ግን ወደ ፊት የሚያራምዳቸው መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ይዘው ስላሉ ክርስትያኖች እናመስግነው፣ ስለዚሁ ሰዎች ማሰብ ጥቂት ሊረዳን ይችላል፤ እነርሱ ይህንን ካደረጉ! እነርሱ ይህንን ማድረግ ከቻሉ እኔስ ለምን እንደዛ አላደርግም? ጌታን የጽናት ስጦታ እንዲለግስልን እንለምነው፣ ሲሉ አስተምረዋል፣

ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን “በየዕለቱ ከወንጌል ትንሽ ክፍል እናንብብ፣ እንዲህ በማድረግም መሠረታውያን የሆኑ የፍቅርና የይቅር ባይነት ሕይወት ለመኖር እንማራለን” ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.