2014-05-10 14:55:55

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጳጳሳት በቫቲካን የበጎ ፈቃድ ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ :


RealAudioMP3 የኢትዮ/ ኤርትራ ብፁዓን ጳጳሳት እዚህ ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድሊሚና የበጎ ፈቃድ ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሄደዋል። ብጹዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳቱ ሐሙስ እና ዓርብ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተዋ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሁለቱ ሀገራት ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ ማህበራዊ ፍትሐዊነት እንዲኖር በሀገሮቻቸው የሚያሳዩት ጥረት የሚመሰገን እንደሆነ አመልክተዋል።

በማያያዝ እምነት ክርስትና ኢትዮ/ኤርትራ ከክርስትና አጥቢያ ጀምሮ በእለት የተመሰረተ እንደሆነ እና ነባር ክርስትና መሆኑ አስገንዝበዋል ።

በቀንድ አፍሪቃ ድርቅ ተከትሎ የሚከሰት ርሃብ እና የሚታዩ ግጭቶች እረዳለሁ ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ ሁኔታው አሳሳንቢ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያናቱ ለችግር ሰለባ የሆነ ህዝብ ከሰብአውያን ድርጅቶች በመተባበር የሚሰጡት ሰብእዠዊ ርዳታ የሚበረታታ መሆኑ አመልክተዋል።

በማያያዝ በተለያየ ምክንያት ከቀንድ አፍሪቃ ከሰሜናዊ አፍሪቃ ተንስተው በመዲተራንይሃን ባሕር በኩል ኤውሮጳ ለመግባት ባሕር ውስጥ ሰጥመው የሚቀሩ ወጣቶች ዘክረው አሳዛኝ ሁኔታ መሆኑ አስገንዝበዋል ።

ብጹዓን ጳጳሳቱ ለህንጸተ ካህናት ትኩረት እንዲሰጡ እንደ አባት እንዲከባከብዋቸው
ለእምእመናን ቀጣይ ትምህርተ ክርስቶስ እና ቃለ ሰናየ እንዲሰጡ ቅድስነታቸው አሳስበዋል።

ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕረሲዳንት የሁለቱ ሀገራት ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብጹዕ አቡነ ብርሃነ የሱስ ሱራፊኤል ስለዚሁ ጉብኝት ማብራርያ እንዲሰጡን ጠይቀናል ። የድምጹ ምልክት ነክተው ይከታተሉ ፡









All the contents on this site are copyrighted ©.