2014-05-08 19:12:27

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
በመዝሙረ ዳዊት ሲነበብ እንደሰማነው “ጌታ ይመክረኛል በልቤ ውስጥም ይናገረኛል” ይላል፣ ይህም የመንፈስ ቅዱስ ሌላ ስጦታ ነው፣ የምክር ስጦታ ነው፣ ዛሬ ትኵረታችንን ስለዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆነ ስለ ምክር እንናገራለን፣ የምክር ስጦታ ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊ ነው፣ በሕይወት ዘመናችን በተለይ ደግሞ ታላቅ ጥንቃቄ ለሚያስፈልጋቸው ውሳኔዎችና ተግባሮች የጥበበኞችና የወዳጆቻችን ምክር እንዴት እንደሚያስፈልገን እናውቃለን፣ በመንፈስ ቅዱስ የምክር ስጦታም በቀጥታ በመንፈሱ ልባችንን የሚያበራልንና እንዴት መናገርና መሆን እንዳለብን እንዲሁም መከተል ያለብንን ጐዳና የሚያሳየን እግዚአብሔር ራሱ ነው፣ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በሕይወታችን እንዴት ይሠራል? እንዴትስ ልንሰማውና ልንከተለው እንችላለን? ብለን የጠየቅን እንደሆነ፤
    መንፈስ ቅዱስን በተቀበልንበትና በልባችና ባኖርንበት ጊዜ ድምጹን ለመስማት እና ሃሳቦቻችንን እና ዝንባሌዎቻችን በእግዚአብሔር መንገድ እንዲሚሰሩ ሊያደርጋቸው ይጀምራል፣ የመንፈሳችን ውሳጣዊ እንቅስቃሴም ለማንኛው ተግባራችን እንደ ምሳሌ እንዲሆነን እና ከእግዚአብሔርና ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ግኑንኘት እንዴት መሆን እንዳለበት እርሱን ለመከተል ወደ ኢየሱስ እንዲያተኵር ያደርገዋል፣ ስለዚህ በምክር ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ኅልናችን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያደርገውን ግኑኘት ልክ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር እንዳደረገውና በወንጌሉ እንዳስተማረን ለማድረግ ያስችለዋል፣ በዚህም መንገድ መንገስ ቅዱስ በመንፈሳችን እንድናድግና እንድንዳብር ያደርገናል እንዲሁም በማኅበረ ክርስትያን መሃከል ከዚሁ ስጦታ በሚፈልቀው በጥንቃቄና ታማኝነት እንድንመላለስ ያስችለናል፣ በወንጌል ተመልክቶ ያለው ጠንቃቃ መሆን የሚለው ቃል ራስን የመጠበቅና ተጠንቅቆ የመኖር ጉዳይ ሳይሆን ራስ ወዳድነት እንዳያጠቃንና እኔ ያልሁት ይሁን የሚል ጭፍን ሃሳብ እንዳያጠቃን በማኅበር ተባብሮ እንዴት መኖር እንድንችል ዘንድ የሚረዳን የሚያሳድገንና የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ይህንን የማደርግበትም ምክንያት እግዚአብሔር ከልጁ ኢየሱስ ጋር አንድ ሊያደርገን በፈቀደው ለእኛ ለሚጠቅም በጎ ነገር ማድረጉን በማወቅ ነው፣
    እንታድያ እንዴት አድርገን ነው ይህንን መዝገብ ልንይዘው የምንችለው? ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ታዛዦች ለመሆን እንዴት እንችላለን? ይህንን ስጦታ ጠንቅቆ ለመያዝና ለመጠቀም የሚረዳን መሠረታዊው ነገር ጸሎት ነው፣ ነገር ሁሌ በነበርንበት እንመለሳለን፣ እንዴት ይሁን? ሌላ መልስ የለም ጸሎት ጸሎት አሁንም ጸሎት ደጋግሞ መጸለይ ያስፈልጋል፣ ከሕጻንነት ጀምረን የተማርናቸውን ጸሎቶች መድገም አለብን፤ ጌታን እንለምነው፧ ጌታ ሆይ እርዳኝ ምከረኝ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምከረኝ፤ ብለን እንለምነው፣ ጸሎት ስናሳርግ መንፈስ ቅዱስ ያኔ መጥቶ እንዲረዳን ልባችንን ከፍተን እንጠባበቀዋለን ማለት ነው፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲመክረን የፈለግን እንደሆነ እኛ ሁላችን እንዲህ ነው ማድረግ ያለብን፣ ይህንን አትርሱት ሁሌ ጸሎት ማድረግ ከነጭራሽ ይህንን ነገር አትርሱት፣ በመንገድ ስንጓዝም ይሁን በአውቶቡስ ስንጓዝ በጸጥታ በልባችን የጸለይን እንደሆነ ማንም አያውቅም፤ ስለዚህ የዚህ ዓይነትና ሌሎች አጋጣሚዎች በመጠቀም ዘወትር እንድንጸልይ ይሁን፣ ለምን እንጸልያለን ያልን እንደሆነ ደግሞ መንፈስ ቅድስ የምክር ስጦታን እንዲሰጠን እንጸልይ፣ ቀስ በቀስ በእግዚአብሔር ጋር በመወያየትና ቃሉን በማዳመጥ በብዙ አጥሮች የተከለለ የሰው ልጆች አስተሳሰብን ጥለን ጌታን ጌታ ሆይ ፈቃድህ የትኛው ይሆን ብለን ለመጠየቅ እንችላለን፣ ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነው በምድርም ይሁን በማለት ጌታ ጸሎት ባስተማረን መንገድ የጌታ ፈቃድ ለእርሱ ደስ የሚለው የቱ ይሆን ለማወቅ መጸለይ ያስፈልጋል፣ እንዲህ በማድረግ ከጌታ ጋር ያለን ጥልቅ ግኑኝነት ያድጋል ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል “ሰውች ለፍርድ ሲያቀርቧችሁ የምትናገሩት በዚያን ሰዓት ስለሚሰጣችሁ እንዴት ወም ምን እንናገራለን ብላችሁ በማሰብ አትጨንቁ፣ ምክንያቱም በእናንተ አድሮ የሚናገር የሰማዩ አባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም” (ማቴ 10፤19-20) የሚለው ምን ያህል እውነት መሆኑን ልታጣጥሙና ልትገነዘቡ ነው፣ የሚመክረን መንፈስ ቅዱስ ነው ነገር ግን እኛ ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ መስጠት አለብን እንዲሁም ለጸሎት የሚሆን ጊዜ ይኑረን ምክንያቱም እርሱ በልባችን እንዲመጣና እንዲረዳን የምንጠይቀው በጸሎት ነውና፣
    እንደሌሎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የምክር ስጦታም ለመላው ማኅበረ ክርስትያን ለማገልገል የተሰጠ ነው፣ እርግጥ ነው ጌታ ጥልቅ በሆነ መንገድ በልቦቻችን ይናገረናል ነገር በወንድሞቻችን ድምጽና ምስክርነትም ይናገረናል፣ የእምነት ወንዶችና ሰዎች ማግኘት እውነተኛ ስጦታ ነው፤ እነኚህን ሰዎች ማግኘትና በተለይ ችግርና ብሶት ባጋጠመነ ጊዜ በልባችን ትንሽ የብርሃን ብልጭታ ሊያስድሩንና የጌታን ፈቃድ ለይቶ ለማወቅ ይረዱናል፣ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ! አንድ ጊዜ በሉኻን መካነ ንግደት በመንበረ ኑዛዜ የብዙ ንስሓዎች ስቀበል የሰዎቹ ወረፋ እጅግ ረዥም ነበር፤ በሰልፉ የሃገሩ ስብከቱ ጳጳስም ነበሩ እንዲሁም በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንድ ዘመናዊ አለባበስ የለበሰ ወጣትም ነበር፣ ወጣቱ ተራው ደርሶ ሊናዘዝ መጣ፣ ችግሩ እጅግ ከባድ ነበር፣ ልጁ ችግሩን ካወራ በኋላ እርስዎ በኔ ቦታ ቢሆኑ ምን ባደረጉ ነበር ብሎ ጠየቀኝ፣ ወደ ቤት ከተመለስኩ በኋላ ያጋጠመኝን ለእናቴ ነገርክዋት፣ እናቴም ወደ እመቤታችን ድንግል ሂድና የምታደርገውን እርሷ ትነግርሃለች አለችኝ፣ እንዲህ ነው የምክር ስጦታ ያለው፣ ከልጅዋ ችግር እንዴት እንደምትገላገል አታውቅም ነበር ነገር ትክክለኛውን መንገድ አሳየችው፣ ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሂድ እርሷም መንገዱን ታሳያሃለች! የምክር ስጦታ ይህ፣ ምናልባት እንዴት አድርጎ መንፈስ ቅዱስ በዚህች ሴት አማካኝነት ይናገራል ለማለት ትችል ይሆናል ነገር ግን ይህች ትሑትና ገር ሴት ለልጅዋ ከሁሉም ምክሮች የብለጠ ምክር ሰጠችሁ ምክንያቱም ያ በኑዛዜ ያገኘሁት ልጅ እኔ እመቤታችን ድንግል ማርያም ተመልከትሁ እርሷም ይህንና ይህ አድርግ አለችኝ ባለኝ ጊዜ መናገር አልቻልኩም፣ ሁሉንም እናትና ልጅ ጨርሹት እውነተኛው እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም፣ የምክር ስጦታ ይህ ነው፣ እናንተ ይህ የምክርስ ስጦታ ያላችሁ እናቶች ይህንን ስጦታ ለልጆቻችሁ ለምኑ፣ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፣ በአንድ የክርስትያን ማኅበረሰብ እንዲህ መሆን አለበት፣ አንዱ ሌላውን በሃይማኖት ጉዳይ መርዳት በመንፈስ ቅዱስ ማብራት ያስፈልጋል፣ እንዲህ በማድረግም ሕይወታችን ሁሌ በሚያፈቅረንና ለእኛ በጎ ነገር ምን መሆኑን ከእኛ አብልጦ በሚያውቀው በእግዚአብሔር እጆች ይሆናል፣

ውዶቼ የዳዊት መዝሙር ም ዕራፍ 16 “መልካም ምክር በመስጠት ስለሚመራኝ እግዚአብሔርን አመስግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ እንዲግሥጸኝ ኅሊናዬን ያነቃል፣ እግዚአብሔር ዘወትር ከእኔ ጋር እንደሆነ ዐውቃለሁ፤ በአጠገቤም ስለሆነ አልታወክም” (7-8) በማለት እንድንጸልይ ይጠራናል፣ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ይህንን እርግጠኝነት በልቦቻችን ውስጥ ይተምልን በዚህም በመጽናናቱና በሰላሙ እንሞላለን፣ ዘወትር የምክር ስጦታን ጠይቁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልን፣







All the contents on this site are copyrighted ©.